የኢትዮጵያ ደራስያን በፊደል ማውጫ
 
Members Login
Your Email/Username
Password:
 

New member? Sign up!

Forgot password?

 
ጦማር
 
የልብ ወለድ ሥነጽሑፍ ጉዞ
ሥነ ጽሑፍ ጠቅላላ ዓላማው ማስደሰት ነው። ይህንንም ጉልህ አላማ የሚፈጽመው ሁሉን አቀፍ የሕይወት ኂስ በማቅረብ ነው። ሥነ ጽሑፍ ጉልህ ዓላማውን ለመፈጸም ጥራትና ወጥነት እንዲኖረው ያስፈልጋል።" በኑኀ ዘመን ፥ በቀን ብዛት የማይነቅዝና የማይሻግት" መሆን አለበት። አለበለዚያ አጉል ጒህና ወይም ብስና እንጂ ሥነ ጽሑፍ ሊሆን አይችልም።
 
አጭር ልብ ወለድ
 
ቱሉ ፎርሣ
ቱሉን ማን የማያውቅ አለ ? እናንተ አታውቁትም እንዴ ? ቱሉ ይኼ ማካሮኒ ፋብሪካ የሚሠራው እኮ ነው፡፡ ኦ ! ቱሉን የማያውቅ ማን አለ ቱሉ ሠላሳ አንድ ዓመቱ ነው።ወይም ወደዚያ ግድም ነው። እና ቱሉ ቁመቱ ረጅም ነው። የቱሉ እጆች ትላልቅ ናቸው።የቱሉ ክንዶች ጠንካሮች ናቸው።የቱሉ መዳፎች ሸካራ ናቸው። ቱሉ ከማካሮኒ ፣ፓስታና ፓስቲኒ ፋብሪካ ውስጥ ወፍጮ ክፍል ነው የሚሠራው። ወፍጮ ክፍል ስድስት ዓመት ሠርቷል።

 


 

 

 
   
 
ሊነበቡ የሚገባቸው 10 ምርጥ የታሪክ መጻሕፍት
ሊነበቡ የሚገባቸው 10 ምርጥ ልቦለድ ድርሰቶች
ሊነበቡ የሚገባቸው 10 ምርጥ የግጥም መድብሎች
   

 

መጽሐፍ መፈለጊያ/Search Books
 
 
 
   
 
ተጨማሪ የምርምር ጽሑፎችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

በቅርቡ በገበያ ላይ የዋሉ አዳዲስ መጻሕፍት
ምርጥ አጫጭር ታሪኮች
ታከለ ወልደሀዋርያትን ከአብዛኛው ሰው የሚለየው ጠባይ ቢኖር ዛሬ ስለተሸነፈ ትግሉን ያለማቋረጡ ነው። ልጅ እያሱን ለኢትዮጵያ አይበጅም ብሎ ባመነበት ሰአት ልጅእያሱን ለማስወገድ በሙሉ ልቦናውና በሙሉ አቅሙ ታገለ። ...አሁን ደግሞ ተፈሪ ማለፍአለበት ነገር ግን ተፈሪን እጥላለሁ ማለት ኢትዮጵያን እስካልጎዳ ድረስ ብቻ ነው። ምክንያቱም ተፈሪ ያልፋል፣ታከለም ያልፋል፣ የምትዘልቀው ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ስለዚህም የታከለ አላማ እስከ ህይወቱ መጨረሻ ድረስ የሚከተለው ይሆናል።
ከመጽሐፉ የተወሰደ
ሕብረት ባጣ የኃላፊነት ሥራ ለሹመት፣ለመወደድ ሲባል በሚደረግ ሩጫ መካከል ሰሚ የሚያጡ ማህበራዊ ችግሮች እየተደመሩ የሕዝብ እሮሮና ጩኸቶች እየበረከቱ፣ በደሎች እየወፈሩን እየሰፉ፣ እድገታቸውም ተመንድጎ እየወጣ መመለሻና መቃኛ ከሌለው ችግር ውስጥ ተዘፍቀው ይቀራሉ። ጦሳቸውም ከትውልድ እስከ ትውልድ ተላላፊ በሽታ ይሆናል።
አገርን ለመምራት የታደሉና የተመረጡ መሪዎችና ሹሞች አልሚነትና አጥፊነታቸውን ሕዝብን መስተዋታቸው አድርገው እራሳቸውን መመልከት ቢችሉ፣ ሕዝብ በመስተዋትነቱ ከእምነት ስለማይርቅባቸው አገር መልጽጋ ፣ ፍትህና ርትዕ ነግሦ፣ የአገር መሬት ፍሬዋን ሰጥታ መክበሪያና መጠቀሚያ እንጂ መቀበሪያ ብቻሆና ዜጎቿን አታስተናግድም።
ስለ መጽሐፉ የቀረበውን ሙሉ ቅኝት ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
 
         

በቅርቡ በድጋሚ የታተሙ ቀደምት መጻሕፍት
ስለ መንግስቱ ለማ አንዳንድ ሰዎች በጣም የተሳሳተ አመለካከት አላቸው፤ ወግ-አጥባቂና ትምክህተኛ ይመስላቸዋል። ግን አልነበረም።... ዘረኝነት የሚባል ነገር በተለይ ሲያልፍም አይነካው። በአስተሳሰቡ ከጊዜ የቀደመ ... የዛሬና የነገ ሰው ነው። እርግጥ ለባህል መጠበቅ አጥብቆ ይቆረቆራል።
         

አንባብያን ቢያነቧቸው የሚመከሩ መጻሕፍት
ከመጽሐፉ የተወሰደ
“ሰው ሀብታም ሆነ ደሀ ልዩነቱ የሚታየው በዝቅተኛ የዕውቀት እና የእምነት ደረጃ እስካለ ድረስ ብቻ ነው። ወደ ላይ ከፍ ካሉ በኋላ ወደ ፍጹምነት ደረጃ ሲደርሱማ የሚያስቡለት የሚሰስቱለት ነገር አይሆንም። እዚህ ከፍታ ላይ ያለ ሰው ብዙ ቢኖረው አይተርፈውም። ስለሚያካፍል፤ ትንሽም ያለው አያንሰውም። ብዙ ስለማይፈልግ ነው። ወደዚህ ዓለም ይዞት የመጣው፣ ሲሔድም የሚያከትለው አንዳች ነገር አለመኖሩን ያውቃልና ነው”
ሀገር፣መንደር፣ቤት ንብረቱን ትቶ ወደ ሩቅ የሄደ ሰው ባይተዋር ይባላል። ይህ ስያሜ በኑሮ አድራሻ መለወጥ ብቻ ምክንያቱን የሚያገኝ አይደለም ።የመንፈስ ባይተዋርነትም አለ። ሰው ከነበረበት ቦታ ወደ ሌላ ሳይዘዋወርም ለአዲስ አስተሳተሰብ፣ ፈሊጥና የኑሮ መልክ ሊጋለጥ ይችላል።አንደኛው እስኪያይል ወይም ሁለቱም እስኪዋሐዱ ድረስ የወትሮው እና የአሁኑ በህሊና ውስጥ የባላንጣዎች ተቃርኖ ይፈጥራሉ። እንዲህ ያለ ሰውነት ሲታገል ይቆይና ሲሰለቸው የቸልተኝነት የግዴለሽነት ኢንዲፈረንቲዝም መንፈስ ይሰፍንበታል። ይህ በተለይ የሚገለጸው በሥነ ምግባር መስክ ነው። ሥለታም የነበረው ሥነ ምግባራዊ በሕሊናው ይሰንፋል። የሚመቹ፣ የማይቆረቁሩ፣ የማይጋጩ እንደ ዘዴኝነት፣ ጮሌነት፣ ብልሃተኝነት ያሉ የማይጨበጡ የቀልጣፋ ሰውነት ጠባዮች ያይላል። " አስመሳይ፤ አድር ባይ እንደ እምነቱ የማይኖር እንደ ኑሮው የማያምን የሕሊናውን ብኩርና ለምስር ንፍሮ የለወጠ" ሌላም ሌላም እንደ አለንጋ የሚጋረፉ ተግሣጾች ወቅታዊነታቸውን የሚያገኙት በዚህ ሳቢያ ይመስለናል። "የሞራል ድቀት" የሚባለው ይህ ሳይሆን ይቀራልን? የመነሳቱ፣ የመቆሙ ከራሱ ጋር ተስማምቶ ሚዛን ጠብቆ የመራመዱ ነገርስ እንዴት ይሆን? ቅን ሕሊና የማያልፈው ጥያቄ ነው።
An eighteen-year old girl sets out to meet a young man who she had never met before and is swept away by a series of events that transformed her life in a way she could have never imagined. Tower in the sky is the story of love, revolution, hopes, dreams, violence, terror, trust, betrayal, tragedy, disillusionment, self-transformation and the triumphal power of the human spirit. The book vividly depicts a moment in Ethiopia’s history when the country convulsed with violence unleashed by a bloodthirsty military government that massacred an untold number of people, especially the young and plunged the country into darkness. It is also the story of thousands of young people who stood up against one of the most brutal dictatorships in history and fought for equality, freedom, social justice, and dignity.
         
         
50 አመት ያለፋቸው እንዲሁም የደራሲያን መልካም ፈቃድ የተሰጠባቸው ለአንባብያን እንዲደርሱ በሶፍት ኮፒ የተገኙ።

የዐፄ ምኒሊክ ዘመን በወጣቱ አስኳላ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ አስመራ ፩፱፲፩፪።
ትልቁን የስዋስው መጽሐፍ መጻፍ ከመጀመራቸው በፊት መንደርደሪያ እንዲሆናቸው የጻፉት መጽሐፍ ነው።

የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት ነሃሴ 1987ዓ.ም የፀደቀው።
         
በየመጻሕፍት መደብሮች የሚገኙ አዳዲስ መጻሕፍት
         
         
የዚህ ድረ-ገጽ መሠረታዊ ይዘቶች የተቃኙት በ
<< ያሠርቱ ምእት ፥ የብርእ ምርት ( ከ፲፻ እስከ ፳፻ ) ድርሰት ክፍል ፩
ጳጉሜን ፫ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ.ም በብርሃነመስቀል ደጀኔ 'ና
ጌታሁን ሽብሩ >>
በተዘጋጀው ያልታተመ ጥናታዊ ጽሑፍ ነው።