[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
የኢትዮጵያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
አ
በ
ቨ
ገ
ደ
ጀ
ሀ
ወ
ዘ
ዠ
ሐ
ኀ
ጠ
ጨ
የ
ከ
ኸ
ለ
መ
ነ
ኘ
ሠ
ዐ
ፈ
ጸ
ፀ
ቀ
ረ
ሰ
ሸ
ተ
ቸ
ጰ
ፐ
ወደ ዋና ገጽ
መብዐጽዮን ዐምዱ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መንበረ ወልዴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መሐመድ ይማም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1920 - 1988]
መንግስቱ ገዳሙ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መንግሥቱ ገዳሙ በሲዳሞ ክፍለሀገር ተወልደው ከብት ሲጠብቁ ያደጉ የባላገር ልጅ ናቸው፡፡ በልጅነታቸው እባብ ነድፎዋቸው ለስድስት ሳምንታት ኀሊናቸውን ስተው ከሰነበቱ በኋላ ከሞት ተርፈዋል፡፡ ዕድሜያቸው ከፍ ሲል በወታደርነት ተቀጥረው ሠርተዋል።
ከወታደር ዓለም ወጥተው ፖስታ፣ ቴሌፎንና ቴሌግራፍ ሚኒስቴር ውስጥ ተቀጠሩ፡፡ በሥራቸው ጎበዝ ስለነበሩ በዕድገት ወደ ድሬደዋ ተዛወሩ፡፡ ባሕል አስከብራለሁ እያሉ በርኖስ እየለበሱ ቢሮ በመገባታቸው የሚታወቁት መንግሥቱ ገዳሙ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ከገቡ በኋላ “ሞገደኛ ጋዜጠኛ” የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በጋዜጣ የጀመሩት ጽሑፍ ደራሲ እንዲሆኑ ስለገፋፋቸው ሳይሆን አይቀርም ብዙ “ቤሳ” መጻሕፍት ጽፈዋል፡፡ የጻፉትን መጻሕፍ ይዘት ባብዛኛው አያስታውሱም፡፡ ካሳተሟቸው መጻሕፍት መካከል “ሶማሌው” በ፲፱፶፯ ዓ.ም. “መሰላል” በ፲፱፶፱ ዓ.ም. እና “አሳማና ድመት” በ፲፱፶፱ ዓ.ም. ተጠቃሾች ሲሆኑ ሌሎች ኢ ልብወለድ መጻሕፍትም በተለያዩ ጊዜዎች አሳትመዋል፡፡
የመንግሥቱ ገዳሙ ባህርይ አፈንጋጭ የሚሉት ዓይነት ነው፡፡ ሞገደኛው ጋዜጠኛ መንግሥቱ በተወለዱ በ48 ዓመታቸው ሐምሌ 18 ቀን በ፲፱፷፰ ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
መንግሥቱ ገዳሙ በሲዳሞ ክፍለሀገር ተወልደው ከብት ሲጠብቁ ያደጉ የባላገር ልጅ ናቸው፡፡ በልጅነታቸው እባብ ነድፎዋቸው ለስድስት ሳምንታት ኀሊናቸውን ስተው ከሰነበቱ በኋላ ከሞት ተርፈዋል፡፡ ዕድሜያቸው ከፍ ሲል በወታደርነት ተቀጥረው ሠርተዋል።
ም/መቶ አለቃ መለሰልኝ አንለይ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሊቀ ሊቃውንት መሐሪ ተረፈ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መሸሻ ግዛው
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መንግስቱ መኮንን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መክብብ ደስታ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መኮንን ወርቅ አገኘሁ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1891 - 1971]
ብላታ መርስዔ ሐዘን ወልደ ቂርቆስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መርስዔ ኀዘን ወልደቂርቆስ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጅሩ ቆላ ውስጥ እምባጮ መግደላዊት በሚባል አካባቢ በ፲፰፻፺፩ ዓ.ም. ተወለዱ። ትምህርት የጀመሩት በልጅነታቸው ሲሆን በጊዜው ዳዊት ደግመዋል፡፡ ከዚያም የዜማ ትምህርት በመጀመር ጾመ ድጓና ድጓ አስኪደዋል፡፡ ቀጥሎም ቅኔ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ ፲፱፻፭ ዓ.ም. የመጀመሪያ ሥራቸውን የወንበር ፀሐፊ በመሆን እየሠሩ አገልግለዋል፡፡ የመጻሕፍተ ሐዲሳትን፣ የዮሐንስ አፈወርቅን ትርጓሜ፣ እንዲሁም የመቅድመ ወንጌልን ትርጓሜ ትምህትን አጠናቀዋል፡፡ እኝህ ታላቅ ሰው ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ሲመሠረት የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ፣ ቀጥለውም የተፈሪ መኮንን ት/ቤት የግዕዝና የአማርኛ አስተማሪ በመሆን ሠርተዋል፡፡ እንዲሁም ከ፲፱፴፫ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ፲፱፷፫ ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በልዩ ልዩ ኃላፊነቶችና በዲሬክተር ማዕረግ ሠርተዋል፡፡ ሥነ ጽሑፍንና ታሪክን በተመለከተ አሥራ ሦስት መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡ ሰባት መጻሕፍትን ተርጉመዋል፡፡ የተለያዩ ጽሑፎችን አሰባስበው አዘጋጅተዋል፡፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ሥራዎችን ከሊቃውንት ጋር በመሆን አዘጋጅተዋል፡፡ የአማርኛ ስዋስው መጽሐፍ ባለመዘጋጀቱ ተማሪዎች ተገቢውን የቋንቋ ትምህርት ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን በማየትም በ፲፱፴፭ ዓ.ም. “የአማርኛ ስዋስው” የተባለ መጽሐፍ አዘጋጅተው በማቅረብ ችግሩ እንዲቃለል አድርገዋል። መርስዔ ኀዘን በላቀ የሥነ ጽሑፍ ሥራቸው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሽልማት ድርጅት ተሸላሚ ናቸው፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
መርስዔ ኀዘን ወልደቂርቆስ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጅሩ ቆላ ውስጥ እምባጮ መግደላዊት በሚባል አካባቢ በ፲፰፻፺፩ ዓ.ም. ተወለዱ።
መንክር መኮንን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መላከ ኃይሉ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መስፍን ሀብተማርያም ሞገስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መስፍን ሀ/ማርያም የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፴፮ ዓ.ም. በምሥራቅ ሸዋ ሞጆ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞጆ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃን በአንቦ ማዕርገ ሕይወት ት/ቤት አጠናቅቀዋል። የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአ.አ. ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ በቢ.ኤ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ በተጨማሪም ከብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ካናዳ በፈጠራ ድርሰቶች አጻጻፍ ኤም.ኤ. ዲግሪ ኤም.ኤፍ.ኤ ተቀብለዋል፡፡
“የቡና ቤት ሥዕሎችና ሌሎች ወጎች”፣ “ዓውዳመት”፣ “አዜብና ሌሎችም አጫጭር ልቦለዶች”፣ “የሌሊት ድምጾች” የሚሉ ልቦለድ ሥራዎችንና የወግ ጽሑፎችን ለንባብ አብቅተዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
መስፍን ሀ/ማርያም የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፴፮ ዓ.ም. በምሥራቅ ሸዋ ሞጆ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞጆ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃን በአንቦ ማዕርገ ሕይወት ት/ቤት አጠናቅቀዋል።
መኮንን ዘውዴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መስፍን ዓለማየሁ ጠይቃቸው
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መስፍን ዓለማየሁ በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ጅጅጋ ከተማ መስከረም ፳፮ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ09#9 ዓ.ም.፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ09%1 ዓ.ም. አጠናቀቁ።
መስፍን ዓለማየሁ “የቴዎድሮስ ዕንባ”፣ “የቬኑሱ ነጋዴ”፣ የተሰኙ ተውኔቶችን “የሽዋስቲካ ምሥጢር”፣ “ካፖርቱ”፣“የመጨረሻዋ ቅጠል”፣ “ሽማግሌውና ባሕሩ”፣ በመባል የሚታወቁ ልቦለድ የትርጉም መጻሕፍት አሳትመው ለአንባብያን አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ግጥሞች፣ አጫጭር ልቦለዶች፣ በጋዜጦች፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ለሕዝብ አቅርበዋል፡፡
መስፍን ዓለማየሁ በሕይወት ዘመናቸው በቀድሞዋ ሶቪየት ኀብረት በሞስኮ 12ኛው የወጣቶች ፌስቲቫል በተከበረበት ወቅት በሶቭየት ደራስያን ማኀበር አዳራሽ በተካሄዱ የሥነ ጽሑፍ - ጉባኤዎች ላይ ማኀበራችንን ወክለው ተገኝተዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
መስፍን ዓለማየሁ በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ጅጅጋ ከተማ መስከረም ፳፮ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ09#9 ዓ.ም.፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ09%1 ዓ.ም. አጠናቀቁ።
[1883 - 1953]
ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው በሰሜን ሸዋ በተጉለት አውራጃ አዲስጌ በምትባል ቦታ በ በ1983 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በዳግማዊ ምኒልክ፣ በንግሥት ዘውዲቱ እና በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥታት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሀገራቸውን አገልግለዋል።
በሕይወት ዘመናቸው ከ2ዐ በላይ መጻሕፍት በመድረስ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ዕድገት የጎላ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ከሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸው ውስጥ የታተመው “አርሙኝ” የተባለው መጽሐፋቸው በብዙዎች ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ የሕይወት ታሪካቸውን ባጭሩ፣ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት የጻፏሕውን ድርሰቶችን ስለማይጮው ጦርነትና የዓለም ፖለቲካ በማካተት የጻፉት ነው፡፡ “የድሆች ከተማ” በ1933፣ “ሐሳብና ሰው” በ1933፣ “ሣልሳዊ ዳዊት” በ1933 “የፍቅር ጮራ” በ1939፣ ከጻፏቸው መጽሐፍት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው በሰሜን ሸዋ በተጉለት አውራጃ አዲስጌ በምትባል ቦታ በ በ1983 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በዳግማዊ ምኒልክ፣ በንግሥት ዘውዲቱ እና በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥታት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሀገራቸውን አገልግለዋል።
ዲ/ን መልአኩ አስማማው
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሙሉ ሰው ምትኩ አዣዥ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሙሐመድ ታጁቲን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አባ ሚካኤል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሚሊዮን ነቅንቅ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ማርቆስ ዳውድ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1928 - 2004]
ማሞ ውድነህ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ማሞ ውድነህ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. በቀድሞ አጠራር በወሎ ክፍለ ሀገር በዋግ አውራጃ በዳህና ወረዳ አምደወርቅ ከተማ ተወለዱ፡፡ በቤተክህነት ትምህርት ዳዊት እስከመድገም ደርሰዋል፡፡ ከ፲፱፵ ዓ.ም. ጀምሮ በደሴ በንጉሥ ሚካኤል ትምህርት ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ትምህርት ቤቶች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተምረዋል፡፡
በመጀመሪያ በመምህርነት ቀጥሎም በውጭ ሀገር ኤምባሲዎች ሠርተዋል፡፡ በማስታወቂያ ሚኒስቴር በፖሊስ ሠራዊትና በቀድሞ ኤርትራ ክፍለ ሀገር በፕሬስ የሥራ ክፍሎች ውስጥ ሠርተዋል፡፡ ከ፲፱፹፭ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ፲፱፺፯ ዓ.ም. ድረስ የደራስያን ማህበርን በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል፡፡ ልብ ወለድ፣ አጫጭር ድርሰት፣ ግጥምና ቅኔ፣ የቲያትር መጻሕፍትን በመድረስና በመተርጎም ይታወቃሉ፡፡ ካሳተሟቸው 5ዐ ያህል መጻሕፍት መካከል ሁለተኛው የዓለም ጦርነት፣ የሴቷን ፈተና፣ ከወንጀለኞች አንዱ፣ ቬኒት ሙሶሎኒ፣ ዘጠና ደቂቃ በኢንተቤ እና ዕቁብተኞቹ ይገኛሉ፡፡ በቅርቡም "የደረስኩበት" በሚል ርዕስ ግለ ታሪካቸውን የተመለከተ 5ዐኛው መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጽ አሳትመዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ማሞ ውድነህ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. በቀድሞ አጠራር በወሎ ክፍለ ሀገር በዋግ አውራጃ በዳህና ወረዳ አምደወርቅ ከተማ ተወለዱ፡፡ በቤተክህነት ትምህርት ዳዊት እስከመድገም ደርሰዋል፡፡ ከ፲፱፵ ዓ.ም. ጀምሮ በደሴ በንጉሥ ሚካኤል ትምህርት ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ሜሪ ጃዕፋር ሰይድ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሜሪ ጃዕፋር በቀድሞው ኢሊባቡር ጠ/ግዛት ጎሬ ከተማ ጥቅምት ፭ ቀን ፲፱፵፰ ዓ.ም. ተወለዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአቡነ ሚካኤል ት/ቤት ጎሬ፣ የሁለተኛ ደረጃን በቀዳማዊ ኃ.ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ጎሬ፣ አሥመራና ተፈሪ መኮንነ አጠቃላይ ት/ቤት አ.አ. አጠናቅቀዋል፡፡ ከአ.አ. ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡
ሜሪ ጃዕፋር ከ11 በላይ የሕጻናት መጻሕፍት፤ ከስድስት በላይ ሥዕላዊ መግለጫ ያላቸውን መጻሕፍትን ያሳተሙ ሲሆን ካቀረቧቸው የሕጻናት መጻሕፍት መካከል፣ “የፋጡማ ሕልም”፣ “ከወንጪ መልስ”፣ “ኢልሞሌ ይመለስ ይሆን?”፣ “ቦላቦ” “ሚጢ ሚጢጢ”፣ “ሰላሜ”፣ “የጦጢት መላ” ወዘተ… ይገኙባቸዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ሜሪ ጃዕፋር በቀድሞው ኢሊባቡር ጠ/ግዛት ጎሬ ከተማ ጥቅምት ፭ ቀን ፲፱፵፰ ዓ.ም. ተወለዱ።
ምክረ ሥላሴ ገብረ አማኑኤል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሞገስ ክፍሌ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መጻሕፍት ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ
ይጫኑ
ተመዝግበው ከሆነ እዚህ
ይጫኑ
[
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ቋንቋ
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
]
[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com