ስለኢትዮጵያ፡ደራሲያን።

ዋና ገጽ | ጦማር
+ - Font Size  
 
 

ስለኢትዮጵያ፡ደራሲያን።

  


   ጽሑፉ ፡ የፕሮፌሰር ፡ ታምራት ፡ አማኑኤል ፡ ነው። ፕሮፌሰር ፡ ታምራት ፡ ከዛሬ ፡ ኻያዐምስት ፡ ዓመታት ፡ በፊት ፡ በትምርትና ፡ ሥነጥበብ ፡ ሚኒስቴር ፡ አማካሪ ፡ ኾነው ይሠሩ ፡ ነበር።ነገር ፡ ግን ፡ በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ፕሮፌሰር ፡ በመባል ፡ ፈንታ ፡ ሊቀማእምራን ፡ ይባሉ ፡ ነበር። 

   ትዝ ፡ እንደሚለኝ ፡ ባ፲፱፻፴፮ ፡ ዓ.ም ፡ በቱርክ ፡ አ ገር ፡ የሚገኝ ፡ አካዳሚ ፡ ይኹን ፡ ወይም ፡ የደራሲያን ፡ ማኅበር ፡ ስለኢትዮጵያ ፡ ሥነጽሑፍና ፡ ስለኢትዮጵያዊያን ፡  ደራሲያን ፡ ጠይቆ ፡ ስለነበረ ፡ ጥያቄውን ፡ የመለሱት ፡ ሊቀ ማእምራን ፡ ታምራት ፡ አማኑኤል ፡ ነበሩ። 

   በዚህ ፡ ምክንያት ፡ ስለኢትዮጵያ ፡ ሥነጽሑፍና ፡  ስለኢትዮጵያዊያን ፡ ደራሲያን ፡ ከብዙ ፡ በጥቂቱ ፡ የምታመ ለክተውን ፡ ይህችን ፡ ጽሑፍ ፡ ሊቀማእምራኑ ፡ በዐማርኛ ፡ አዘጋጅተው ፡ አቀረቡ።ነገር ፡ ግን ፡ ጠያቂው ፡ የውጪአገር ፡ ድርጅት ፡ በመኾኑ ፡ መጠን ፡ መግለጫውም ፡ በውጭ ፡ ቋንቋ ፡ መዘጋጀት ፡ ነበረበት። ስለዚህ ፡ ጽሑፊቱ በእንግሊዝኛ ፡ እንድትተረጐም ፡ በዚያን ፡ ዘመን ፡ እኔ ፡ ጽሑፎችን ፡ በማረም ፡ ሥራ ፡ አገለግልበት ፡ ወደነበረው ፡ ክፍል ፡ ተላከች።የፕሮፌሰሩ ፡ ዐማርኛ ፡ ጽሑፍም ፡ በዚያን ጊዜ ፡ እንግሊዝኛ ፡ ተርጓሚ ፡ ለነበሩት ፡ ለአቶ ፡ እንግዳ ፡  ጽጌሐና ፡ ጥቂት ፡ ከባድ ፡ ኾኖ ፡ የዐማርኛውን ፡ አስተሳሰብ በእንግሊዝኛ ፡ አስተካክለው ፡ ለመግለጥ ፡ አስቸጋሪ ፡ ስለ ኾነባቸው ፡ በማስረዳቱ ፡ ሥራ ፡ እንድረዳቸው ፡ ታዝዤ ፡  ዐብረን ፡ ከሠራን ፡ በኋላ ፡ እንግሊዝኛው ፡ ሲላክ ፡ ይህ ፡  ዐማርኛው ፡ ግን ፡ እኛው ፡ ዘንድ ፡ ቀረ።

   የጽሑፉ ፡ አሰካክና ፡ አገላለጥ፣የታሪኩም ፡ አቀራ ረብና ፡ ውበት ፡ ደስ ፡ ስለሚለኝ ፡ ጽሑፉን ፡ ዐልፎ ፡ ዐልፎ እመለከተው ፡ ነበር። ነፍሳቸውን ፡ ይማርና ፡ በሕይወት ፡  ቢኖሩ ፡ ኖሮ ፡ ከዚህም ፡ የተሻለ ፡ ጽሑፍ ፡ ለአገራቸው ፡  ሕዝብ ፡ እንዲያበረክቱ ፡ ማሳሰብ ፡ ይቻል ፡ ነበር ፡ ይኾናል። ባለመኖራቸው ፡ አልተቻለም። ካኹን ፡ ቀድሞም ፡ ‘ማህአ ትማ ፡ ጋንዲ’ ፡ ከሚባለው ፡ በቀር ፡ በስማቸው ፡ ታትሞ ፡  የወጣ ፡ ሌላ ፡ ጽሑፍ ፡ መኖሩን ፡ አላውቅም።

    ይህችም ፡ ጽሑፍ ፡ በመጽሐፍነት ፡ ለመውጣት የሚያበቃት ፡ መጠን ፡ ባይኖራትም ፡ በኾነው ፡ መንገድ ፡  ቁምነገር ፡ ላይ ፡ ብትውል ፡ ያንኑ ፡ ያኽል ፡ ለስማቸው ፡  መጠሪያ ፡ ልትኾን ፡ ትችል ፡ ነበር ፡ እያልኹ ፡ በማሰላስል በት ፡ ጊዜ ፡ በቀዳማዊ ፡ ኀይለሥላሴ ፡ ዩኒቨርስቲ ፡ ለሚገኘ ው ፡ ለኢትዮጵያ ፡ ቋንቋዎችና ፡ ሥነጽሑፍ ፡ ክፍል ፡ ብት ቀርብ ፡ ለምርምርና ፡ ለጥናት ፡ ትረዳለች፣በመጽሔትም ታትማ ፡ ትወጣና ፡ ለፕሮፌሰሩ ፡ ዝክረ ፡ ስም ፡ ትኾናለች በሚል ፡ አስተሳሰብ ፡ ከሥራ ፡ ጓደኛዬ ፡ ካቶ ፡ አሰፋ ፡ ገብረ ማሪያም ፡ ጋር ፡ ከተመካከርንበት ፡ በኋላ ፡ በዚሁ ፡ ተግባር ላይ ፡ እንድትውልላቸው ፡ የኒህን ፡ ታላቅ ፡ ምሁር ፡ ስምና ሥራ ፡ የምታስታውስውን ፡ ይህችን ፡ በ፳፩ ፡ ገጽ ፡ የተጻፈች ትንሽ ፡ ጽሑፍ ፡ ለዚሁ ፡ ድርጅት ፡ አቀረብኋት። 


                                                             ከበደ ፡ ደስታ ፲፱፻፷፩ ዓ.ም
ethioreaders.com
 
ይህን ጽሁፍ ወዳጆችዎ ፌስቡክ ገጽዎ ላይ ለማስነበብ:  
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
 
 
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
*
   
 
     
     
ፊደልን ከkeyboard ማመሳሰያ።
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com