የኢትዮዽያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
 
30 ውጤት ተገኝቷል
   
ርቱዐ ኢምላክ
ከመጽሐፉ የተወሰደ
"ፍቅርን ከድርሳናት የሚማሩቱ ቢኾን ሰሎሞን ለፍፅምት ሱላማጢስ ያወረደው ቅኔ: ያዜመው ስባሕታየ ስባሔ ለኹሉ በበቃ ነበር። ውነቱ ግን እንዲያ አይዶለም።"

ከመጽሐፉ የተወሰደ
"ፍቅርን ከድርሳናት የሚማሩቱ ቢኾን ሰሎሞን ለፍፅምት ሱላማጢስ ያወረደው ቅኔ: ያዜመው ስባሕታየ ስባሔ ለኹሉ በበቃ ነበር። ውነቱ ግን እንዲያ አይዶለም።"

ጌታቸው ሀይሌ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከግእዝ ወደአማርኛ ከመለሷቸው ጥንታዊ የስነጽሁፍ ቅርሶች አንዱ።
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከግእዝ ወደአማርኛ ከመለሷቸው ጥንታዊ የስነጽሁፍ ቅርሶች አንዱ።
 
ይልማ ወረደ ይህ መጽሐፍ የሳይንስ ፍቅር ላላቸው ብቻ አይደለም። ማንኛውም አንባቢ ቢያነበው በቀላሉ ሊረዳው በሚችል ቀለል ባለ አማርኛ ቋንቋ የተጻፈ ነው። መጽሐፉን ማንበብ ስለ አቶሚክ ኢነርጂ መሰረታዊ የሆነውን እውቀት ያስጨብጣል። ታሪኩ የአቶሚክ ኢነርጂን ግኝት ከአጀማመሩ እስካሁን መጽሐፉ እስከተጻፈበት ጊዜ ድረስ ያለፈበትን ውጣ ውረድና በአሁኑ ጊዜ የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ያስረዳናል። መጽሐፉ ለአቶሚክ ኢነርጂ መገኘት ከፍተኛውን አስተዋጽዎ ያበረከቱትን ተመራማሪዎች የቅብብሎሽ የሥራ ውጤት እንዲሁም የህይወት ጉዞን ይዳስሳል። ከዚህ ታሪክ ውስጥ የሁለት ጊዜ ኖቤል ተሸላሚዋ የፖላንዶ ሜሪ ኩሪ እና የባለቤቷ ፒየር የህይወት ታሪክን ስናነብ እጅግ እንመሰጣለን። የሽማግሌው ኒልስ ቦር፣ የወጣቱ ረዳት ተመራማሪ እንዲሁም የመጀመሪያውን የአቶሚክ ኤነርጂ የማመንጨት ሙከራውን በተሳካ መንገድ ሎስ አላሞስ ላይ በሐላፊነት የመራው በትውልድ ጣሊያናዊ የሆነው የኤነሪኮ ፈርሚን ታሪክ እናገኛለን። ፈርሚን ተመራማሪዎቹ የአቶሚክ ኢነርጂ አባት ይሉታል። የአቶሚክ ኤነርጂው ምርምር እንዲቀጥል ወደአሜሪካ ተሰዶ በነበረበት ጊዜ ያደረጋቸው ከፍተኛ አስተዋጽዎች ለማንኛውም አንባቢ ትምህር ሰጪና አስተማሪ ናቸው። ብዙዎቻችን የአቶሚክ ኤነርጂ ግኝትን ከታዋቂው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ጋር እናቆራኘዋለን ከዚህ መጽሐፍ የአልበርታንስታይንን ለአቶሚክ ኢነርጂ መገኘት ያበረከተውን ትክክለኛ አስተዋጽዎ ምን እንደነበር እናነባለን። ይህን መጽሐፍ ወጣት ተማሪዎች ሊያነቡት ይገባል፤ ምክንያቱም እንዲህ ነው ያለጥርጥር ልባቸውን ለሳይንስ ፍቅር ይከፍተዋልና። መቼም አንዴ ማንበብ ከጀመሩት የማያስቀምጡት፣ከተቀመጡበት በአንድ ትንፋሽ ካልጨረሱ ብድግ የማይሉበት መጽሐፍ ነው።
ይህ መጽሐፍ የሳይንስ ፍቅር ላላቸው ብቻ አይደለም። ማንኛውም አንባቢ ቢያነበው በቀላሉ ሊረዳው በሚችል ቀለል ባለ አማርኛ ቋንቋ የተጻፈ ነው። መጽሐፉን ማንበብ ስለ አቶሚክ ኢነርጂ መሰረታዊ የሆነውን እውቀት ያስጨብጣል። ታሪኩ የአቶሚክ ኢነርጂን ግኝት ከአጀማመሩ እስካሁን መጽሐፉ እስከተጻፈበት ጊዜ ድረስ ያለፈበትን ውጣ ውረድና በአሁኑ ጊዜ የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ያስረዳናል። መጽሐፉ ለአቶሚክ ኢነርጂ መገኘት ከፍተኛውን አስተዋጽዎ ያበረከቱትን ተመራማሪዎች የቅብብሎሽ የሥራ ውጤት እንዲሁም የህይወት ጉዞን ይዳስሳል። ከዚህ ታሪክ ውስጥ የሁለት ጊዜ ኖቤል ተሸላሚዋ የፖላንዶ ሜሪ ኩሪ እና የባለቤቷ ፒየር የህይወት ታሪክን ስናነብ እጅግ እንመሰጣለን። የሽማግሌው ኒልስ ቦር፣ የወጣቱ ረዳት ተመራማሪ እንዲሁም የመጀመሪያውን የአቶሚክ ኤነርጂ የማመንጨት ሙከራውን በተሳካ መንገድ ሎስ አላሞስ ላይ በሐላፊነት የመራው በትውልድ ጣሊያናዊ የሆነው የኤነሪኮ ፈርሚን ታሪክ እናገኛለን። ፈርሚን ተመራማሪዎቹ የአቶሚክ ኢነርጂ አባት ይሉታል። የአቶሚክ ኤነርጂው ምርምር እንዲቀጥል ወደአሜሪካ ተሰዶ በነበረበት ጊዜ ያደረጋቸው ከፍተኛ አስተዋጽዎች ለማንኛውም አንባቢ ትምህር ሰጪና አስተማሪ ናቸው። ብዙዎቻችን የአቶሚክ ኤነርጂ ግኝትን ከታዋቂው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ጋር እናቆራኘዋለን ከዚህ መጽሐፍ የአልበርታንስታይንን ለአቶሚክ ኢነርጂ መገኘት ያበረከተውን ትክክለኛ አስተዋጽዎ ምን እንደነበር እናነባለን። ይህን መጽሐፍ ወጣት ተማሪዎች ሊያነቡት ይገባል፤ ምክንያቱም እንዲህ ነው ያለጥርጥር ልባቸውን ለሳይንስ ፍቅር ይከፍተዋልና። መቼም አንዴ ማንበብ ከጀመሩት የማያስቀምጡት፣ከተቀመጡበት በአንድ ትንፋሽ ካልጨረሱ ብድግ የማይሉበት መጽሐፍ ነው።
 
ሲራክ ኅሩይ ወልደሥላሴ ኢትዮጵያዊ መስፍን ከተድላና ደስታ ከሞላበት ከአባቱ ግዛት ሰብሮ ወጥቶ። አለምን እየዞረ ደስታን ከሀገር ሀገር የሚፈልግበት ታሪክ ነው።
ኢትዮጵያዊ መስፍን ከተድላና ደስታ ከሞላበት ከአባቱ ግዛት ሰብሮ ወጥቶ። አለምን እየዞረ ደስታን ከሀገር ሀገር የሚፈልግበት ታሪክ ነው።
 
ሣህለስላሴ ብርሃነማርያም የታዋቂው እንግሊዛዊ ደራሲ ቻርልስ ዲከንስ A tale of two cities ድርሰት ትርጉም ናት።
የታዋቂው እንግሊዛዊ ደራሲ ቻርልስ ዲከንስ A tale of two cities ድርሰት ትርጉም ናት።

ለማ ፈይሳ የታወቀው በትውልድ ህንዳዊ የሆው የጆርጅ ኦረዌይል ምርጥ ድርሰት።
የታወቀው በትውልድ ህንዳዊ የሆው የጆርጅ ኦረዌይል ምርጥ ድርሰት።
 
ጌታቸው ሀይሌ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከግእዝ ወደአማርኛ ከመለሷቸው ጥንታዊ የስነጽሁፍ ቅርሶች አንዱ።
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከግእዝ ወደአማርኛ ከመለሷቸው ጥንታዊ የስነጽሁፍ ቅርሶች አንዱ።
 
ጌታቸው ሀይሌ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከግእዝ ወደአማርኛ ከመለሷቸው ጥንታዊ የስነጽሁፍ ቅርሶች አንዱ።
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከግእዝ ወደአማርኛ ከመለሷቸው ጥንታዊ የስነጽሁፍ ቅርሶች አንዱ።
 
ካሳ ገብረህይወት ካሳ ገብረህይወት ከፋንቱ ሳህሌ ጋር በመሆን የሩሰያው ደራሲ የፋይደር ዶስቶቭስኪ ምርጥ ስራዎች እንዱ የሆነውን Crime and Punishment ትረጉም።
ካሳ ገብረህይወት ከፋንቱ ሳህሌ ጋር በመሆን የሩሰያው ደራሲ የፋይደር ዶስቶቭስኪ ምርጥ ስራዎች እንዱ የሆነውን Crime and Punishment ትረጉም።
 
ፋንቱ ሳህሌ ፋንቱ ሳህሌ ከካሳ ገብረህይወት ጋር በመሆን የሩሰያው ደራሲ የፋይደር ዶስቶቭስኪ ምርጥ ስራዎች እንዱ የሆነውን Crime and Punishment ትረጉም።
ፋንቱ ሳህሌ ከካሳ ገብረህይወት ጋር በመሆን የሩሰያው ደራሲ የፋይደር ዶስቶቭስኪ ምርጥ ስራዎች እንዱ የሆነውን Crime and Punishment ትረጉም።

ተጫነ ጆብሬ መኰንን የሃበሻ ጀብዱ የማይጨው ጦርነት ከዝግጅቱ እስከ መጨረሻ ፍልሚያው በነበሩ ኢትዮጵያን በግንባር ተገኝተው ይደግፉ በነበሩት ቼኮዝላቫኪያዊው አዶልፍ ፓርለሳክ የአይን እማኝነት የተጻፈ ነው ። የጦርነቱን አመጣጥና ዝግጅት እያስቃኘ የሃበሻን ወደር የለሽ ጀግንነት፣ አምላኩን ወዳጅ፣ ሀገሩንና ሃይማኖቱን አጥብቆ አክባሪ ታማኝ እና ለክብሩ ሟች እንደሆነ የሚመሰክር መጽሐፍ ነው።

ከመጽሐፉ የተወሰደ ስለደራሲው ማስታወሻ።
የቼክ ሪፐብሊኩ ተወላጅ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ አዶልፍ ፓርለሳክ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ አገሮችን የጎበኙ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ1935 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በመምጣት ከንጉሠ ነገሥቱ ፊት ቀርበው የኢትዮጵያን መኰንንነት ማእረግ ከተሾሙ በኋላ የሰሜኑ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ለነበሩት ራስ ካሣ ኃይሉ የጦር አማካሪ በመሆን አገልግለዋል። በዚሁ ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጎን ሆነው ታግለዋል። መጽሐፉ ፣ ሃበሽስካ ኦዴሳ Habešskà Odyssea -የሃበሻ ጀብዱ፣ የዚያን የገበሬ ጦር ጀግንነት ለመዘከር የጻፉት ነው።
የሃበሻ ጀብዱ የማይጨው ጦርነት ከዝግጅቱ እስከ መጨረሻ ፍልሚያው በነበሩ ኢትዮጵያን በግንባር ተገኝተው ይደግፉ በነበሩት ቼኮዝላቫኪያዊው አዶልፍ ፓርለሳክ የአይን እማኝነት የተጻፈ ነው ። የጦርነቱን አመጣጥና ዝግጅት እያስቃኘ የሃበሻን ወደር የለሽ ጀግንነት፣ አምላኩን ወዳጅ፣ ሀገሩንና ሃይማኖቱን አጥብቆ አክባሪ ታማኝ እና ለክብሩ ሟች እንደሆነ የሚመሰክር መጽሐፍ ነው።

ከመጽሐፉ የተወሰደ ስለደራሲው ማስታወሻ።
የቼክ ሪፐብሊኩ ተወላጅ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ አዶልፍ ፓርለሳክ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ አገሮችን የጎበኙ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ1935 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በመምጣት ከንጉሠ ነገሥቱ ፊት ቀርበው የኢትዮጵያን መኰንንነት ማእረግ ከተሾሙ በኋላ የሰሜኑ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ለነበሩት ራስ ካሣ ኃይሉ የጦር አማካሪ በመሆን አገልግለዋል። በዚሁ ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጎን ሆነው ታግለዋል። መጽሐፉ ፣ ሃበሽስካ ኦዴሳ Habešskà Odyssea -የሃበሻ ጀብዱ፣ የዚያን የገበሬ ጦር ጀግንነት ለመዘከር የጻፉት ነው።
 
ገብረ ጊዮርጊስ ትርፌ የመናኝ:ጉዞ።
ከዮሐንስ:ቡንያን:የተጻፈ።
፲፰፻፺፪:ዓ:ም: የክርስቲያን:መንገድ:ተብሎ:
በገብረ:ጊዮርጊስ:ትርፌ:በአማርኛ:ቋንቋ:የተተጎመ።
፲፱፻፶፩ :ዓ:ም:እንደገና:ታርሞ:ታተመ።
በአርቲስቲክ: ማተሚያ:ቤት:አዲስ:አበባ።
የመናኝ:ጉዞ።
ከዮሐንስ:ቡንያን:የተጻፈ።
፲፰፻፺፪:ዓ:ም: የክርስቲያን:መንገድ:ተብሎ:
በገብረ:ጊዮርጊስ:ትርፌ:በአማርኛ:ቋንቋ:የተተጎመ።
፲፱፻፶፩ :ዓ:ም:እንደገና:ታርሞ:ታተመ።
በአርቲስቲክ: ማተሚያ:ቤት:አዲስ:አበባ።
 
ኣምባቸው ከበደ ከእንጦጦ እስከ ባሮ በምንሊክ ዘመነ መንግስት በሩሲያዊው እስክንድር ቡላቶቪች በሩሲያ ቋንቋ ተጽፎ በዶር. ኣምባቸው ከበደ ወደ አማርኛ የተመለሰ በጊዜው የነበረውን የደቡብ ኢትዮጵያ ምድራዊ አቀማመጥን ጨምሮ የሕዝቡን አኗኗር እንዲሁም ባሕልና እምነት የሚተርክ መጽሐፍ ነው።

ከገፅ 110 ከመጽሐፉ የተወሰደ
"በነገራችን ላይ ኦሮሞዎች አንድ አስደናቂ የሆነ ልማድ አላቸው። ይህን ያህል ጠላቶች ገድያለሁ ብሎ መናገር ነውር ስለሆነ የኦሮሞ ወንድ በሕይወት እያለ ይህን ጀግንነት ፈፅሜያለሁ ብሎ አይፎክርም የሓበሾች ልማድ ግን የተገላቢጦሽ ነው። ሰውየው ከሞተ በኋላ ግን የሟቹ ወንድሞች ወይም ደገኞች፤ ሰውየው መቼ፣ የትና በምን ዓይነት ሁኔታ ምን ዓይነት ጀብዱዎች እንደፈጸመ የመዘርዘር ግዴታ አለባቸው።"

ከገፅ 150 የተወሰደ
"ሸማውን ኣፍንጫው ድረስ ተከናንቦ ዙሪያውን በንቀት እየቃኘ የተቀመጠ ወይም ቀስ ብሎ እየተጎማለለ የሚሄድ ሃበሻ የሚሰማው ኩራት ኩራት አይደለም። ሌላው ታናሽ ከታላቁ ጋር በሚያወራበት ጊዜ በሸማው ጫፍ አፉን መሸፈን አለበት።
ከእንጦጦ እስከ ባሮ በምንሊክ ዘመነ መንግስት በሩሲያዊው እስክንድር ቡላቶቪች በሩሲያ ቋንቋ ተጽፎ በዶር. ኣምባቸው ከበደ ወደ አማርኛ የተመለሰ በጊዜው የነበረውን የደቡብ ኢትዮጵያ ምድራዊ አቀማመጥን ጨምሮ የሕዝቡን አኗኗር እንዲሁም ባሕልና እምነት የሚተርክ መጽሐፍ ነው።

ከገፅ 110 ከመጽሐፉ የተወሰደ
"በነገራችን ላይ ኦሮሞዎች አንድ አስደናቂ የሆነ ልማድ አላቸው። ይህን ያህል ጠላቶች ገድያለሁ ብሎ መናገር ነውር ስለሆነ የኦሮሞ ወንድ በሕይወት እያለ ይህን ጀግንነት ፈፅሜያለሁ ብሎ አይፎክርም የሓበሾች ልማድ ግን የተገላቢጦሽ ነው። ሰውየው ከሞተ በኋላ ግን የሟቹ ወንድሞች ወይም ደገኞች፤ ሰውየው መቼ፣ የትና በምን ዓይነት ሁኔታ ምን ዓይነት ጀብዱዎች እንደፈጸመ የመዘርዘር ግዴታ አለባቸው።"

ከገፅ 150 የተወሰደ
"ሸማውን ኣፍንጫው ድረስ ተከናንቦ ዙሪያውን በንቀት እየቃኘ የተቀመጠ ወይም ቀስ ብሎ እየተጎማለለ የሚሄድ ሃበሻ የሚሰማው ኩራት ኩራት አይደለም። ሌላው ታናሽ ከታላቁ ጋር በሚያወራበት ጊዜ በሸማው ጫፍ አፉን መሸፈን አለበት።
 
ዋቅጅራ ጐባ ባለ ቅኔው ፥ ፈላስፋውና ሰዓሊው ካህሊል ጅብራን ፥ ብዙ ነቢያትን ባፈራች ቀበሌ ፥በሊባኖን ተራራ አቅራቢያ ተወለደ። በዐረብኛ ቋንቋ የተጻፉ ድርሰቶቹን በቅርብ የሚያውቁ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዐረብኛ ተናጋሪዎች የዘመኑ ታላቅ ሰው መሆኑን አምነዋል። የቅኔ ድርሰቶቹ ከኻያ በሚበልጡ ቋንቋዎች ተተርጉመዋል ።

"ነቢዩ" ዘ ፕሮፌት የተባለ መጽሐፉን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የጻፈው ሲሆን ፤ እጅግ የሚመስጥ በመሆኑ ተሸልሞበታል። በብዙ ቋንቋዎችም የተተረጎመ ነው።

የልብንና የአእምሮን ጥልቅ ምሥጢሮች የሚገልጽ ይህ መጽሐፍ ፤ ከኢትዮጵያውያን አንባቢዎች እነዳያመልጥ በብርቱ ስለፈለግሁ ፤ በአማርኛ ቋንቋ ተርጉሜ አቅርቤአለሁ።
ባለ ቅኔው ፥ ፈላስፋውና ሰዓሊው ካህሊል ጅብራን ፥ ብዙ ነቢያትን ባፈራች ቀበሌ ፥በሊባኖን ተራራ አቅራቢያ ተወለደ። በዐረብኛ ቋንቋ የተጻፉ ድርሰቶቹን በቅርብ የሚያውቁ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዐረብኛ ተናጋሪዎች የዘመኑ ታላቅ ሰው መሆኑን አምነዋል። የቅኔ ድርሰቶቹ ከኻያ በሚበልጡ ቋንቋዎች ተተርጉመዋል ።

"ነቢዩ" ዘ ፕሮፌት የተባለ መጽሐፉን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የጻፈው ሲሆን ፤ እጅግ የሚመስጥ በመሆኑ ተሸልሞበታል። በብዙ ቋንቋዎችም የተተረጎመ ነው።

የልብንና የአእምሮን ጥልቅ ምሥጢሮች የሚገልጽ ይህ መጽሐፍ ፤ ከኢትዮጵያውያን አንባቢዎች እነዳያመልጥ በብርቱ ስለፈለግሁ ፤ በአማርኛ ቋንቋ ተርጉሜ አቅርቤአለሁ።
   
መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
 
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com