የኢትዮዽያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
 
252 ውጤት ተገኝቷል
   
ብርሃኑ ድንቄ ከመፀሃፉ የተወሰደ
"ብርሃኑ ፣ አንድን ህዝብ ማስተዳደር የበጎችን መንጋ እንደመጠበቅ ቀላል አይደለም ። እግዚአብሄር ሲያስችለን ብቻ የሚቻለንን እናደርጋለን።"
ከመፀሃፉ የተወሰደ
"ብርሃኑ ፣ አንድን ህዝብ ማስተዳደር የበጎችን መንጋ እንደመጠበቅ ቀላል አይደለም ። እግዚአብሄር ሲያስችለን ብቻ የሚቻለንን እናደርጋለን።"
 
ተክለሐዋርያት ተክለማርያም የአፄ ኀይለሥላሴን ዘመን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው እንደመስታዎት አጉልቶ የሚያሳይ ድንቅ መጽሐፍ።
የአፄ ኀይለሥላሴን ዘመን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው እንደመስታዎት አጉልቶ የሚያሳይ ድንቅ መጽሐፍ።
 
ተክለጻድቅ መኩሪያ ስለ የአስራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን የግራኝ አሕመድ ወረራን በጥልቀት የተፃፈ የታሪክ መዘክር።
ስለ የአስራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን የግራኝ አሕመድ ወረራን በጥልቀት የተፃፈ የታሪክ መዘክር።
 
አባ ባሕርይ የኦሮሞን ታሪክ የያዘ የታሪክ መዘክር።
የኦሮሞን ታሪክ የያዘ የታሪክ መዘክር።
 
ኅሩይ ወልደሥላሴ ግሩም የሆነ የኢትዮዽያ ታሪክን የሚገልፅ መጸሐፍ ነው።
ግሩም የሆነ የኢትዮዽያ ታሪክን የሚገልፅ መጸሐፍ ነው።

ተክለጻድቅ መኩሪያ ስለታላቁ ንጉስ አፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ የነበራቸውን ታላቅ ራይ ለአንድነት ያደረጉትን ታላላቅ ክንውኖችና አስተዋፅዎችን የከተበ ትልቅ የታሪክ መጸሐፍ።
ስለታላቁ ንጉስ አፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ የነበራቸውን ታላቅ ራይ ለአንድነት ያደረጉትን ታላላቅ ክንውኖችና አስተዋፅዎችን የከተበ ትልቅ የታሪክ መጸሐፍ።
 
ተክለጻድቅ መኩሪያ አፄ ዮሐንስ ለኢትዮጵያ አንድነት ያደረጉትን ታላላቅ ክንውኖችና አስተዋፅዎችን የከፈሉትን ታላቅ መስዋትነት የከተበ ትልቅ የታሪክ መጸሐፍ።
አፄ ዮሐንስ ለኢትዮጵያ አንድነት ያደረጉትን ታላላቅ ክንውኖችና አስተዋፅዎችን የከፈሉትን ታላቅ መስዋትነት የከተበ ትልቅ የታሪክ መጸሐፍ።
 
ተክለጻድቅ መኩሪያ ስለታላቁ ንጉስ አፄ ምኒልክ ለኢትዮጵያ አንድነት ክብርና ብልፅግና ስልጣኔ እምነት ያደረጉትን ታቅ ክንውኖችና አስተዋፅዎችን የከተበ ትልቅ የታሪክ መጸሐፍ።
ስለታላቁ ንጉስ አፄ ምኒልክ ለኢትዮጵያ አንድነት ክብርና ብልፅግና ስልጣኔ እምነት ያደረጉትን ታቅ ክንውኖችና አስተዋፅዎችን የከተበ ትልቅ የታሪክ መጸሐፍ።
 
ጳውሎስ ኞኞ እምዬ ምኒልክ ስልጣኔን ወደ አገርውስጥ ለማስገባት ያደረጉትን ጥረጥና አስገራሚ ውጤቶች በስፋት የዳሰሰ የታሪክ መጸሐፍ።
እምዬ ምኒልክ ስልጣኔን ወደ አገርውስጥ ለማስገባት ያደረጉትን ጥረጥና አስገራሚ ውጤቶች በስፋት የዳሰሰ የታሪክ መጸሐፍ።
 
ጳውሎስ ኞኞ ስለታላቁ ንጉስ አፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮዽያ የነበራቸውን ታላቅ ራዕይ ለኢትዮጵያ አንድነት ያደረጉትን ታላላቅ ተጋድሎና አርአያነት የከተበ የታሪክ መጸሐፍ።
ስለታላቁ ንጉስ አፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮዽያ የነበራቸውን ታላቅ ራዕይ ለኢትዮጵያ አንድነት ያደረጉትን ታላላቅ ተጋድሎና አርአያነት የከተበ የታሪክ መጸሐፍ።

ጳውሎስ ኞኞ የአምስት አመቱን የኢጣለያ ወረራ ግዜ የተደረጉ የኢትዮጵያውያን ጀግንነት የአርበኝነት ታላቅ ተጋድሎና መስዋእትነት ታሪክ የሚተርክ ታላቅ የታረክ መጸሐፍ ነው።
የአምስት አመቱን የኢጣለያ ወረራ ግዜ የተደረጉ የኢትዮጵያውያን ጀግንነት የአርበኝነት ታላቅ ተጋድሎና መስዋእትነት ታሪክ የሚተርክ ታላቅ የታረክ መጸሐፍ ነው።
 
ባሕሩ ዘውዴ የመቶ አመት የኢትዮጵያን ታሪክ በስፋት የዳሰሰ ድንቅ የታሪክ መጸሐፍ።
የመቶ አመት የኢትዮጵያን ታሪክ በስፋት የዳሰሰ ድንቅ የታሪክ መጸሐፍ።
 
ብርሃኑ ድንቄ በአጭሩ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚዳስስ ግሩም የሆነ መጸሐፍ።
በአጭሩ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚዳስስ ግሩም የሆነ መጸሐፍ።
 
ገብረሕይወት ባይከዳኝ የዐፄ ምኒሊክ ዘመን በወጣቱ አስኳላ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ አስመራ ፩፱፲፩፪።
የዐፄ ምኒሊክ ዘመን በወጣቱ አስኳላ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ አስመራ ፩፱፲፩፪።
 
ኃይለ ሥላሴ ራስ መኮንን የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ግለ ታሪክ በራሳቸው አንደበትና ብእር የተፃፈ።
የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ግለ ታሪክ በራሳቸው አንደበትና ብእር የተፃፈ።

መንግስቱ ለማ መጽሐፈ ትዝታ ዘ አለቃ ለማ፤ ከአፄ ዮሃንስ ግዜ ጀምሮ የነበረውን የኢትዮጵያ የቤተክርስትያን ሊቃውንት ታሪክ በሊቁ አለቃ ለማ አንደበት ይተርካል። መቸም ቢሆን የኢትዮጵያን ሊቃውንት ታሪክ ማንበብ ያስደስታል። ነገርግን እንደዚህ በግሩም ሁኔታ የነበራቸውን የእውቀት ርቀት፣ ለእውቀት የሚሰጡት ክብርና ሞገስ፣ የእርስ በርስ አክብሮት ማርማር በሚል በሊቁ አለቃ ለማ አንደበት ሲተረክ ከማንበብ በላይ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ምን የላቀ ንባብ ቢያገኝ ሊያስደስተው የሚችል ነገር እነዳለ አላውቅም። የነአቡነ አሮን የፃድቃን ህይወት። የነ አፄ ዮሃንስ ሀይማኖታዊ ቀናይነት። የዐፄ ቴዎድሮስ የዜማ ፍቅር። ብቻ የኢትዮጵያን ታላቅነት ሁሉም ይረዳል ነገር ግን የታላቅነትዋን ሚስጥር መሰረት የሆኑትን ሊቃውንት ታሪክ ብዙዎቻችን አናውቅም፤ እኛ የምናውቀው የነገስታቱን ታሪክ ብቻ ነው፣ ከነገስታቱ ጀርባ እነዚህ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ፋኖስ ሆነው ኢትዮዽያን ይመሯት ነበር።
መጽሐፈ ትዝታ ዘ አለቃ ለማ፤ ከአፄ ዮሃንስ ግዜ ጀምሮ የነበረውን የኢትዮጵያ የቤተክርስትያን ሊቃውንት ታሪክ በሊቁ አለቃ ለማ አንደበት ይተርካል። መቸም ቢሆን የኢትዮጵያን ሊቃውንት ታሪክ ማንበብ ያስደስታል። ነገርግን እንደዚህ በግሩም ሁኔታ የነበራቸውን የእውቀት ርቀት፣ ለእውቀት የሚሰጡት ክብርና ሞገስ፣ የእርስ በርስ አክብሮት ማርማር በሚል በሊቁ አለቃ ለማ አንደበት ሲተረክ ከማንበብ በላይ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ምን የላቀ ንባብ ቢያገኝ ሊያስደስተው የሚችል ነገር እነዳለ አላውቅም። የነአቡነ አሮን የፃድቃን ህይወት። የነ አፄ ዮሃንስ ሀይማኖታዊ ቀናይነት። የዐፄ ቴዎድሮስ የዜማ ፍቅር። ብቻ የኢትዮጵያን ታላቅነት ሁሉም ይረዳል ነገር ግን የታላቅነትዋን ሚስጥር መሰረት የሆኑትን ሊቃውንት ታሪክ ብዙዎቻችን አናውቅም፤ እኛ የምናውቀው የነገስታቱን ታሪክ ብቻ ነው፣ ከነገስታቱ ጀርባ እነዚህ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ፋኖስ ሆነው ኢትዮዽያን ይመሯት ነበር።
 
አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ Afework Gebreyesus ደራሲ.አፈወርቅ ገብረየሲስ የምኒሊክ አማካሪ ሆነው በቅርበት ኢያውቁት ን የዘመኑን የህዝብ አስተዳደር እንዴት እንደነበር በተለይም ቀድመው ንጉስ ዩነበሪትን አጤ ዮሐንስ ዘመን ዩታዪ የህዝብ አስተዳደር ችግር እንደማመጣ ጠሮያ በመጠቀም ለምኒሊክ ቸስተደሰፈር ን በማሞካሸት የጣፉት ነው። መትሀፉ ብዙ ቁም ነገሮችን የያዘ ቢሆንም ስለአጤ ዮሐንስ የሚያቀርበውን የማነጣጠሮያ ሀተታ በጎዜው በነበሩ ምሁራን ትችትን ቸስነሰቨቷአል።
ደራሲ.አፈወርቅ ገብረየሲስ የምኒሊክ አማካሪ ሆነው በቅርበት ኢያውቁት ን የዘመኑን የህዝብ አስተዳደር እንዴት እንደነበር በተለይም ቀድመው ንጉስ ዩነበሪትን አጤ ዮሐንስ ዘመን ዩታዪ የህዝብ አስተዳደር ችግር እንደማመጣ ጠሮያ በመጠቀም ለምኒሊክ ቸስተደሰፈር ን በማሞካሸት የጣፉት ነው። መትሀፉ ብዙ ቁም ነገሮችን የያዘ ቢሆንም ስለአጤ ዮሐንስ የሚያቀርበውን የማነጣጠሮያ ሀተታ በጎዜው በነበሩ ምሁራን ትችትን ቸስነሰቨቷአል።

ማህተመሥላሴ ወልደመስቀል ከ1900 እስከ 1935 ዓ.ም የነበረውን የኢትዮጵያ አስተዳደር ስርአት ወግና ደንብ በሚገባ የሚያብራራ መጽሐፍ።
ከ1900 እስከ 1935 ዓ.ም የነበረውን የኢትዮጵያ አስተዳደር ስርአት ወግና ደንብ በሚገባ የሚያብራራ መጽሐፍ።
 
ታምራት አማኑኤል

ጽሑፉ ፡ የፕሮፌሰር ፡ ታምራት ፡ አማኑኤል ፡ ነው። ፕሮፌሰር ፡ ታምራት ፡ ከዛሬ ፡ ኻያዐምስት ፡ ዓመታት ፡ በፊት ፡ በትምርትና ፡ ሥነጥበብ ፡ ሚኒስቴር ፡ አማካሪ ፡ ኾነው ይሠሩ ፡ ነበር።ነገር ፡ ግን ፡ በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ፕሮፌሰር ፡ በመባል ፡ ፈንታ ፡ ሊቀማእምራን ፡ ይባሉ ፡ ነበር።

ትዝ ፡ እንደሚለኝ ፡ ባ፲፱፻፴፮ ፡ ዓ.ም ፡ በቱርክ ፡ አ ገር ፡ የሚገኝ ፡ አካዳሚ ፡ ይኹን ፡ ወይም ፡ የደራሲያን ፡ ማኅበር ፡ ስለኢትዮጵያ ፡ ሥነጽሑፍና ፡ ስለኢትዮጵያዊያን ፡ ደራሲያን ፡ ጠይቆ ፡ ስለነበረ ፡ ጥያቄውን ፡ የመለሱት ፡ ሊቀ ማእምራን ፡ ታምራት ፡ አማኑኤል ፡ ነበሩ።

በዚህ ፡ ምክንያት ፡ ስለኢትዮጵያ ፡ ሥነጽሑፍና ፡ ስለኢትዮጵያዊያን ፡ ደራሲያን ፡ ከብዙ ፡ በጥቂቱ ፡ የምታመ ለክተውን ፡ ይህችን ፡ ጽሑፍ ፡ ሊቀማእምራኑ ፡ በዐማርኛ ፡ አዘጋጅተው ፡ አቀረቡ።ነገር ፡ ግን ፡ ጠያቂው ፡ የውጪአገር ፡ ድርጅት ፡ በመኾኑ ፡ መጠን ፡ መግለጫውም ፡ በውጭ ፡ ቋንቋ ፡ መዘጋጀት ፡ ነበረበት። ስለዚህ ፡ ጽሑፊቱ በእንግሊዝኛ ፡ እንድትተረጐም ፡ በዚያን ፡ ዘመን ፡ እኔ ፡ ጽሑፎችን ፡ በማረም ፡ ሥራ ፡ አገለግልበት ፡ ወደነበረው ፡ ክፍል ፡ ተላከች።የፕሮፌሰሩ ፡ ዐማርኛ ፡ ጽሑፍም ፡ በዚያን ጊዜ ፡ እንግሊዝኛ ፡ ተርጓሚ ፡ ለነበሩት ፡ ለአቶ ፡ እንግዳ ፡ ጽጌሐና ፡ ጥቂት ፡ ከባድ ፡ ኾኖ ፡ የዐማርኛውን ፡ አስተሳሰብ በእንግሊዝኛ ፡ አስተካክለው ፡ ለመግለጥ ፡ አስቸጋሪ ፡ ስለ ኾነባቸው ፡ በማስረዳቱ ፡ ሥራ ፡ እንድረዳቸው ፡ ታዝዤ ፡ ዐብረን ፡ ከሠራን ፡ በኋላ ፡ እንግሊዝኛው ፡ ሲላክ ፡ ይህ ፡ ዐማርኛው ፡ ግን ፡ እኛው ፡ ዘንድ ፡ ቀረ።

የጽሑፉ ፡ አሰካክና ፡ አገላለጥ፣የታሪኩም ፡ አቀራ ረብና ፡ ውበት ፡ ደስ ፡ ስለሚለኝ ፡ ጽሑፉን ፡ ዐልፎ ፡ ዐልፎ እመለከተው ፡ ነበር። ነፍሳቸውን ፡ ይማርና ፡ በሕይወት ፡ ቢኖሩ ፡ ኖሮ ፡ ከዚህም ፡ የተሻለ ፡ ጽሑፍ ፡ ለአገራቸው ፡ ሕዝብ ፡ እንዲያበረክቱ ፡ ማሳሰብ ፡ ይቻል ፡ ነበር ፡ ይኾናል። ባለመኖራቸው ፡ አልተቻለም። ካኹን ፡ ቀድሞም ፡ ‘ማህአ ትማ ፡ ጋንዲ’ ፡ ከሚባለው ፡ በቀር ፡ በስማቸው ፡ ታትሞ ፡ የወጣ ፡ ሌላ ፡ ጽሑፍ ፡ መኖሩን ፡ አላውቅም።

ይህችም ፡ ጽሑፍ ፡ በመጽሐፍነት ፡ ለመውጣት የሚያበቃት ፡ መጠን ፡ ባይኖራትም ፡ በኾነው ፡ መንገድ ፡ ቁምነገር ፡ ላይ ፡ ብትውል ፡ ያንኑ ፡ ያኽል ፡ ለስማቸው ፡ መጠሪያ ፡ ልትኾን ፡ ትችል ፡ ነበር ፡ እያልኹ ፡ በማሰላስል በት ፡ ጊዜ ፡ በቀዳማዊ ፡ ኀይለሥላሴ ፡ ዩኒቨርስቲ ፡ ለሚገኘ ው ፡ ለኢትዮጵያ ፡ ቋንቋዎችና ፡ ሥነጽሑፍ ፡ ክፍል ፡ ብት ቀርብ ፡ ለምርምርና ፡ ለጥናት ፡ ትረዳለች፣በመጽሔትም ታትማ ፡ ትወጣና ፡ ለፕሮፌሰሩ ፡ ዝክረ ፡ ስም ፡ ትኾናለች በሚል ፡ አስተሳሰብ ፡ ከሥራ ፡ ጓደኛዬ ፡ ካቶ ፡ አሰፋ ፡ ገብረ ማሪያም ፡ ጋር ፡ ከተመካከርንበት ፡ በኋላ ፡ በዚሁ ፡ ተግባር ላይ ፡ እንድትውልላቸው ፡ የኒህን ፡ ታላቅ ፡ ምሁር ፡ ስምና ሥራ ፡ የምታስታውስውን ፡ ይህችን ፡ በ፳፩ ፡ ገጽ ፡ የተጻፈች ትንሽ ፡ ጽሑፍ ፡ ለዚሁ ፡ ድርጅት ፡ አቀረብኋት።

ከበደ ፡ ደስታ ፲፱፻፷፩ ዓ.ም

ስለኢትዮጵያ ፡ ደራሲያን። ሙሉ ጽሑፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ከበደ ተሰማ የዚህ : የታሪክ : ማስታወሻ : ረቂቅ : የጻፍሁት : በ፲፱፻፴ : ዓ.ም : ኢየሩሳሌም : ላይ : በስደት : ሳለሁ : ነበር፤ የኢትዮጵያ : የነጻነት :ጮራ : በፈነጠቀበት : ጊዜ : ቀዳሚ : መልክተኛ : ሆኜ : በሱዳን : በኩል : ወደ : ኢትዮጵያ : በገባሁ : ጊዜ : ረቂቁ : ከጓዝ : ጋር : ቋራ : ላይ : ቀርቶ : ነበርና : ጠፋብኝ። ቢሆንም፤ ታሪኩ : በአእምሮዬ : ውስጥ : ተቀርጾ : ሁል : ጊዜ : ትዝ : ይለን : ስለነበር : በ፲፱፻፴፱:ዓ.ም : የዚህን : ማስታወሻ : ረቂቅ : በድጋሚ : ጻፍኩት።
የዚህ : የታሪክ : ማስታወሻ : ረቂቅ : የጻፍሁት : በ፲፱፻፴ : ዓ.ም : ኢየሩሳሌም : ላይ : በስደት : ሳለሁ : ነበር፤ የኢትዮጵያ : የነጻነት :ጮራ : በፈነጠቀበት : ጊዜ : ቀዳሚ : መልክተኛ : ሆኜ : በሱዳን : በኩል : ወደ : ኢትዮጵያ : በገባሁ : ጊዜ : ረቂቁ : ከጓዝ : ጋር : ቋራ : ላይ : ቀርቶ : ነበርና : ጠፋብኝ። ቢሆንም፤ ታሪኩ : በአእምሮዬ : ውስጥ : ተቀርጾ : ሁል : ጊዜ : ትዝ : ይለን : ስለነበር : በ፲፱፻፴፱:ዓ.ም : የዚህን : ማስታወሻ : ረቂቅ : በድጋሚ : ጻፍኩት።

መርስዔ ሐዘን ወልደ ቂርቆስ መርሰዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ አንድ ለእናቱ ለኢትዮጵያ አንተ ቀጥቀጥትከ አርእስቲሁ ለዕበድ፤ወወሀብኮሙ ለዋስዎሙ ለዘሕዝበ ኢትዮጵያ ውሉድ።
ክቡር ብላታ መርስዔ ሐዘን ወልደ ቂርቆስ ለኢትዮጵያ የሰጡትን ልባዊ አገልግሎትና እሳቸውንም በአካል የሚያውቅ ሰው በየምእት ዓመት አንድ ጊዜ የሚታዩ የዕውቀትና የጥበብ ሰዎች ካሉ ክቡርነታቸው አንዱ መሆናቸውን አይጠራጠርም።...
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

... መጽሐፉ በ1896 ዓ.ም. እስከ 1922 ዓ.ም ያለውን ዘመን የታሪክ መረጃዎች የመዘገበ በቋሚ ምስክርነት የቀረበ በመሆኑ ለቄየው ፣ ላሁኑና ለመጪው ትውልድ ግንዛቤና ትምህርት እንደሚሰጥ አምናለሁ።...
-ደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴ

...እነሆ ባንድ ቅፅ ተጠቃለው ለኅትመት የበቁት የብላታ መርስዔ ኀዘን ትዝታዎች የሀገራችንን የሐያኛው መቶ ዓመት መጀመሪያ ዐሠርት ዓመታት በዝርዝር ለማወቅ ለሚሻ አንባቢ ትልቅ የታሪክ ድግስ ይዘው ቀርበዋል። ለታሪክ ተማሪዎችና ለተመራማሪዎችም ካጠገባቸው ሊለይ የማይችል የሰነድ ስንቅ ነው።...
- ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ
መርሰዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ አንድ ለእናቱ ለኢትዮጵያ አንተ ቀጥቀጥትከ አርእስቲሁ ለዕበድ፤ወወሀብኮሙ ለዋስዎሙ ለዘሕዝበ ኢትዮጵያ ውሉድ።
ክቡር ብላታ መርስዔ ሐዘን ወልደ ቂርቆስ ለኢትዮጵያ የሰጡትን ልባዊ አገልግሎትና እሳቸውንም በአካል የሚያውቅ ሰው በየምእት ዓመት አንድ ጊዜ የሚታዩ የዕውቀትና የጥበብ ሰዎች ካሉ ክቡርነታቸው አንዱ መሆናቸውን አይጠራጠርም።...
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

... መጽሐፉ በ1896 ዓ.ም. እስከ 1922 ዓ.ም ያለውን ዘመን የታሪክ መረጃዎች የመዘገበ በቋሚ ምስክርነት የቀረበ በመሆኑ ለቄየው ፣ ላሁኑና ለመጪው ትውልድ ግንዛቤና ትምህርት እንደሚሰጥ አምናለሁ።...
-ደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴ

...እነሆ ባንድ ቅፅ ተጠቃለው ለኅትመት የበቁት የብላታ መርስዔ ኀዘን ትዝታዎች የሀገራችንን የሐያኛው መቶ ዓመት መጀመሪያ ዐሠርት ዓመታት በዝርዝር ለማወቅ ለሚሻ አንባቢ ትልቅ የታሪክ ድግስ ይዘው ቀርበዋል። ለታሪክ ተማሪዎችና ለተመራማሪዎችም ካጠገባቸው ሊለይ የማይችል የሰነድ ስንቅ ነው።...
- ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ
 
ዘውዴ ረታ በተቃራኒው ግን ከልዑል ራስ ካሣ መማር እንችላለን ። በሕገ መንግሥት አርቃቂው ኮሚቴ ውስጥ የጦፈ ልዩነት የነበረ ቢሆንም፣ የልዩነት ነጥቦቹ ከጽህፈት ሚኒስቴር በመጡ ቃል ተቀባዮች ሰፍሮ ለንጉሰ ነገስቱ እንዲተላለፍ ሊቀ መንበሩ ራስ ካሣ ስብሰባውን ሲያሳርጉ “ሁላችንም ከልባችን የሚቻለንን ማድረጋችንና መድከማችን የሚካድ አይደለም ። በስብሰባችን ላይ ስንነጋገር፣ አለመስማማትና አለመጣጣም ደርሶብናል። ይህ መቼም የአገር ጉዳይ የሆነ ሥራ ሲሠራ የሚያስከትለው ችግር ነው። በዚህም የተነሳ በአንዳንድ ጉዳይ በሐሳብ መከፋፈላችን ለጊዜው በመካከላችን ቅሬታ ያሳደረ መስሎ ቢታይም፣ ወዳጅና ጠላት አድርጎ የሚለያየን መሆን የለበትም። ይህን ሳንስማማ የቀረንበትን ነገር ንጉሠ ነገሥቱ መርምረው ውሳኔ በሚሰጡበት ዕለት፣ ጉዳያችን ይዘጋል” ይሉናል። ለኔ ትውልድ እጅግ ባዕድ በሆነ ሆደ ሰፊነት ያነጋግሩናል። የኔ ትውልድና የቀድሞዎቹ ታላላቆች ሳንተዋወቅ ተጨካክነናል።
ስለ መጽሐፉ የቀረበውን ሙሉ ቅኝት ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በተቃራኒው ግን ከልዑል ራስ ካሣ መማር እንችላለን ። በሕገ መንግሥት አርቃቂው ኮሚቴ ውስጥ የጦፈ ልዩነት የነበረ ቢሆንም፣ የልዩነት ነጥቦቹ ከጽህፈት ሚኒስቴር በመጡ ቃል ተቀባዮች ሰፍሮ ለንጉሰ ነገስቱ እንዲተላለፍ ሊቀ መንበሩ ራስ ካሣ ስብሰባውን ሲያሳርጉ “ሁላችንም ከልባችን የሚቻለንን ማድረጋችንና መድከማችን የሚካድ አይደለም ። በስብሰባችን ላይ ስንነጋገር፣ አለመስማማትና አለመጣጣም ደርሶብናል። ይህ መቼም የአገር ጉዳይ የሆነ ሥራ ሲሠራ የሚያስከትለው ችግር ነው። በዚህም የተነሳ በአንዳንድ ጉዳይ በሐሳብ መከፋፈላችን ለጊዜው በመካከላችን ቅሬታ ያሳደረ መስሎ ቢታይም፣ ወዳጅና ጠላት አድርጎ የሚለያየን መሆን የለበትም። ይህን ሳንስማማ የቀረንበትን ነገር ንጉሠ ነገሥቱ መርምረው ውሳኔ በሚሰጡበት ዕለት፣ ጉዳያችን ይዘጋል” ይሉናል። ለኔ ትውልድ እጅግ ባዕድ በሆነ ሆደ ሰፊነት ያነጋግሩናል። የኔ ትውልድና የቀድሞዎቹ ታላላቆች ሳንተዋወቅ ተጨካክነናል።
ስለ መጽሐፉ የቀረበውን ሙሉ ቅኝት ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
 
ማሞ ውድነህ ለዶጋሊ ድል መቶኛ አመት መታሰቢያ ። በደራሲ ማሞ ውድነህ የተዘጋጀ።
ለዶጋሊ ድል መቶኛ አመት መታሰቢያ ። በደራሲ ማሞ ውድነህ የተዘጋጀ።

| ወደፊት >> 
   
መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
 
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com