|
|
የሊቃውንት ጉባኤ |
|
|
|
|
|
የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር |
|
|
|
|
|
የኋላሸት ግርማ |
|
|
|
|
|
የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ና ምርምር ማእከል |
|
|
|
|
|
የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ |
|
|
|
|
|
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት |
|
|
|
|
|
የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር |
|
|
|
|
|
የሺጥላ ኮከብ |
|
|
|
|
|
ቀኝ/አ ያሬድ ገብረ ሚካኤል |
ቀኝ/አ ያሬድ ገብረሚካኤል ለስድስተኛው የግርማዊት እቴጌ መነን አስፋው የልደት መታሰቢያ በ፲፱፶ ዓ.ም.፣ “ግርማዊት እቴጌ መነን” በሚል ርዕስ መጽሐፍ አሳትመዋል። ስለእሳቸው ታሪክ ሙሉ መረጃ ባይገኝም በዚሁ ባሳተሙት መጽሐፍ ውስጥ ዕድገታቸው የትእንደነበር የሚጠቁም ሀሳብ ሰፍሯል፡፡ “. . . በመታደል በቤተ መንግሥትዎ ቅፅር ግቢ በመንበር ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ዘኒጋባ ሆኜ ትምህርቴን እየቀጠልሁ በምኖርበት ጊዜ . . .” በማለታቸው ዕድገታቸው ቤተመንግሥት አካባቢ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በተጨማሪም ስለ እንስሳት አገልግሎት ለሕፃናት በረከት የሚል ለማስተማሪያ ያገለገለ የግጥም መጽሐፍ ጽፈዋል፡፡
በእቴጌይቱ የሕይወት ታሪክ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ውስጥ ደራሲው ከ0928 ዓ.ም. በፊት የነበሩበትን ሁኔታ ለማስታወስ የተነሱት ፎቶ ይህ ነው፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ። |
ቀኝ/አ ያሬድ ገብረሚካኤል ለስድስተኛው የግርማዊት እቴጌ መነን አስፋው የልደት መታሰቢያ በ፲፱፶ ዓ.ም.፣ “ግርማዊት እቴጌ መነን” በሚል ርዕስ መጽሐፍ አሳትመዋል። |
|
|
|
|
|
ያዕቆብ ኃ/ማርያም |
|
|
|
|
|
ይልማ ሀብተየስ |
ይልማ ሀብተየስ በ፲፱፴ ዓ.ም. አዲስ አበባ ተወለዱ፡፡ ይልማ በሰባት ዓመት ዕድሜያቸው የቤተክርስቲያን ትምህርት ለመቅሰም ወደ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ሄዱ፡፡ እዛም ፊደል ቆጥረው መልዕክተ ዩሐንስና ዳዊት ደግመዋል፡፡ ከዛም በ1ዐ ዓመታቸው ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት በመግባት እስከ አምስተኛ ክፍል ተምረዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሥነ - ጽሑፍ ፍላጎት አልነበራቸውም።
ከዚህ በኋላ በ፲፱፵፰ ዓ.ም. ይልማ ከጓደኞቻቸው ጋር የላብራቶሪ ቴክኒሻንነት በቀድሞ አጠራሩ ፓስተር ኢኒስቲትዩት ተማሩ፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላም ራስ ደስታ ሆስፒታል በመግባት በላብራቶሪ ቴክኒሻንነት ማገልገል ጀመሩ፡፡ በሆስፒታሉ ውስጥ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህል ካገለገሉ በኋላ ጎንደር በሚገኘው የመግሥት ጤና ኮሌጅ በመግባት ከፍተኛ የላብራቶሪ ቴክኔሻንነት ትምህርታቸውን ተከታተሉ፡፡ ጎንደር እያሉ ነው የልብወለድ መጻሕፍትን የማንበብ ፍቅር ያደረባቸው፡፡ መኮንን እንዳልካቸው፣ ከበደ ሚካኤልንና በወቅቱ ታዋቂ የነበሩ ደራሲዎችን ያደንቁ ነበር፡፡ ከውጭም ጎርኪ፣ ዶስቶቪስኪ፣ ቶልስቶይ፣ ዲከንስ፣ ሄምንጊዌይን ያደንቃሉ፡፡
በወንጀል ክትትል ላይ ያተኮሩ ሥራዎችን በመጻፍ አድናቆትን ከአንባቢያን ያገኙት ይልማ፤ የመጀመሪያ መጽሐፋቸውን "ያልታደለች በሰው ሰርግ ተዳረች" በ፲፱፶፭ ዓ.ም.፣ ቀጥሎም "እትዬ ላድርስሽ" ን በ፲፱፶፮ ዓ.ም. አሳትመዋል፡፡ በ፲፱፶፯ ዓ.ም. "ለወጉ ለአርባ ስምንት ሰዓት ተዳሩ" የሚለውን አሳተሙ፡፡ በተከታታይ በወንጀል ላይ ያተኮሩ ልብ ወለዶች የጻፉ ሲሆን "ሌላው እጅ"፣ "ሦስተኛው ሰው"፣ "አጋጣሚ"፣ "እሱን ተይው" ተደናቂነትን ያተረፉ ሥራዎቻቸው ናቸው፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
|
ይልማ ሀብተየስ በ፲፱፴ ዓ.ም. አዲስ አበባ ተወለዱ፡፡ ይልማ በሰባት ዓመት ዕድሜያቸው የቤተክርስቲያን ትምህርት ለመቅሰም ወደ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ሄዱ፡፡ እዛም ፊደል ቆጥረው መልዕክተ ዩሐንስና ዳዊት ደግመዋል፡፡ ከዛም በ1ዐ ዓመታቸው ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት በመግባት እስከ አምስተኛ ክፍል ተምረዋል፡፡ በዚህ ወቅት የሥነ - ጽሑፍ ፍላጎት አልነበራቸውም። |
|
|
|
|
|
ደ/ር ይልማ ወረደ |
|
|
|
|
|
ይልማ ደሬሳ |
|
|
|
|
|
ይልማ ማናዬ |
|
|
|
|
|
ይላቅ ኃ/ማርያም |
|
|
|
|
|
አለቃ ይዅኖ አምላክ ገብረሥላሴ |
|
|
|
|
|
መምህር ይኄይስ ወርቄ |
|
|
|
|
|
ይድነቃቸው ተሰማ |
|
|
|
|
|
አባ ዮሐንስ ከማ |
|
|
|
|
|
ዮሃንስ ወልደ ማርያም |
|
|
|
|
|
ዮሐንስ አፈወርቅ |
|
|
|
|
|
ዮና ቦጋለ |
|
|
|
|
|
ዮሐንስ መሸሻ |
|
|
|
|
|
ዮሐንስ ሙሉጌታ |
|
|
|
|
|
[1897 - 1939] |
|
ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ |
" ኮከብ እምኮከብ ይኄይስ ክብሩ" የሚል የኖረ የግእዝ አባባል አለ:: አንዱ ኮከብ በብርሀኑ፤ በግዘፉ፤ መጠቅላላ ተፈጥሮው ከሌላው ኮከብ ይበልጣል:: እኔን የሚያስገርመኝ ይኽ አይደለም:: እንዳንድ ከዋክብት አሉ--በተለየ አጠራር ተወርዋሪ የምንላቸው:: በሌሊቱ ኅዋ ውስት ከአንዱ መአዘን ሰማይ ወደ ሌላው ተወርውረው ብልጭ ብለው ይጠፋሉ:: ይህ ሁሉ የሚሆነው በቀፅበት ነው::ያንን በጨለማው ግርማ የተዋጠውን ኅዋ በብርሃን ጎርፍ ሰንትቀው አጥለቅልቀውት ይጠፋሉ:: ተመልካችም ከመገረም በሚመነጭ ዝምታ ይዋጣል:: በኢትዮዽያም የሥነ ጽሑፍ ኅዋ ውስጥ ዮፍታሔ ንጉሤ አንድ ተወርዋሪ ኮከብ ነበር።
ብሩህ ነጸብራቁ፤
ውበቱና ድምጹ አንድነት ተሰማ
ተው አንድነት ቢበርቁ፤ የመያው
ቅለት ጠፍቶ፤ ምስጢሩን አካቶ፤
ተወርዋሪ ኮከብ በራሱ ነበልባል
በራሱ ነዲድ ተቃጥሎ የጠፋ፤
ተወርዋሪ ኮከብ በምናየው ሰማይ
ነበረ በይፋ።
አዎን፤ ነበረ። በዚያን ቅጽበት በሆነው የጽሁፍ ዘመን ዮፍታሔ፤ የኢትዮዽያን የስነጽሁፍ ኅዋ በቅኔ ፤ በግጥም ፤በመዝሙርና በተውኔት የብርሃን ጎርፍ ሰንጥቆ አጥለቅልቆት ጠፍቷል። ዛሬ የሚያሳዝነው የዚህ ተወርዋሪ ኮከብ ተጽእኖ በዘመናችን መጥፋቱ ነው።
ስለ ዮፍታሔ ንጉሴ በሕፃንነቴ እናት አባቴ ሲያወጉ፤ ሲወያዩ፤ አንዳንዴም ሲከራከሩ እሰማ ነበርበተለይ አባቴ ከዮፍታሔ ንጉሴ ተውኔቶችና መዝሙሮች በቃሉ የሚያስታውሳቸውን ስንኞች ሲያንጎራጉር እየሰማሁ የዮፍታሔ ፍቅር በሕፃን ልቦናዬና ስሜቴ ተሳለብኝ ። ያኔ ከሰማኋቸው ትዝ የሚሉኝ "አንተ ባ...ጎራዴ ግዛ" እና "ወላድ ኢትዮዽያ ለልጆቻ ብላ እጅግ ሳይትሩባት ሳይዘሯት አብቅላ" የተባሉት መዝሙሮች ናቸው። ሁለተኛው በጣም ጠሊቅ መዝሙር ነው። ጠሊቅነቱ የተገነዘብሁት ካደግሁ በኋላ ነው።
ያኔ መዝሙሩ ይመስጠኝ የነበረው በቃላቱ ጣእመ ዝማሬ ነበረ። የፊተኛውን መዝሙር ግጥሙን በሙሉ ላገኘው አልቻልሁም። የኋለኛው ግን "ብርሃንና ሰላም" ይባል በነበረው ጋዜታ በሙሉ ተጽፎ ስላገኘሁት ከዚህ ቀጥሎ ጽፌዋለሁ፤
ወላድ ኢትዮዽያ ለልጆቿብላ፤
እጅግ ሳይጥሩባት ሳይዘሯት አብቅላ፤
ስንዴውን ጠብቃ እንክርዳዱን ነቅላ፤
ስትመግበን አየን በፀሐይ አብስላ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናብ መንግሥታችን።
በመልካሙ ዘርእ ላይ እንክርዳቸ ሲዘራ፤
ታሳድገውና ከእንክርዳዱ ጋራ፤
ገለባ ሲቃጠል ገበሬ ሲያመራ፤
ታቃጥለዋልች እንክርዳዱን አብራ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።
አይዞህ የኛ ጌታ ነገርህን አትርሳ፤
አለስልሰህ ዝራ የስንዴውን ማሳ፤
የተዘራችው ዘርእ ፈርሳና በስብሳ ፤
ታፈራልቸ ፍሬ ሙታ ስትነሣ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።
በጊዜው የዘራ መልካም ዘር አትርፎ፤
ከበሮቹ ጋራ ማታ ከትላ አርፎ፤
ብርነት ታትቆ በቅን ተሰልፎ፤
በቸርነት ታጥቆ በቅን ተሰልፎ፤
ደግሞ ዘሩን ዘራ መክር አሳልፎ።
ምሳሌ ዘርእ አገራችን፤
ንጹሕ ዝናም መንግስታችን ።
ኋላም ትምህርት ቤት ከገባው በኋላ፣ በተለይም መሁለተኛ ደረጃ በነበርሁበት ጊዜ ፣ በብላታ መርስዔ ሐዘን ስዋስው ውስጥ የዮፍታሔ ቅኔዎች፣ ግጥሞችና መዝሙሮች አልፎ አልፎ ተጠቅሰው በማግኘቴ በቃሌ አትንቼ እንደ ዳዊት እደግማቸው ነበረ። መጀመሪያ ምናቤን የመታው ፤ ስሜቴን የነካው የዮፍታሔ የቋን ቋው ኀይልና ውበት ነበር።ኋላም ስለ ቅኔም ሆነ ስለግጥም አንዳንድ ነገር ከገረጫጨፍሁ በኋላ ያን መጀመሪያ ምናቤን የመታውን፣ ስሜቴን የነካውን የቋንቋ ኀይልና ውበት መመርመር ጀመርሁ። የዮፍታሄ ስንኞች መቀነባበር፤ የዘይቤው ወይንም የስለምኑ መተባበርና መዋሐድ ፤ በስተቅኔውም በኩል የሰምና ወርቁነ፤ የውስተ ወይራው፤ የሰም ለበሱ ፤ የኅብሩና የምርምሩ አካሄድ እስከ ዛሬ ከተነሱት ገጣሚዎች ሁሉ ዮፍታሔን የተለየ ያደርጉታል። የዮፍታሔ ርቀቱ ፤በኪነት ሥራው ሁሉ ከሀብተ ትንቢት ጋር የተሳላው የዘይቤው ወይንም የስለምን ስልቱ ልዝብ በመሆኑ አይኮሰልም፤ ወይንም ሌላ ሊቀዳው አይችልም። ወጥነቱ የተመሠረተው በዚህ ላይ ነው። ---ንጹሕ የኪነት ወጥነት ነው።
|
" ኮከብ እምኮከብ ይኄይስ ክብሩ" የሚል የኖረ የግእዝ አባባል አለ:: አንዱ ኮከብ በብርሀኑ፤ በግዘፉ፤ መጠቅላላ ተፈጥሮው ከሌላው ኮከብ ይበልጣል:: እኔን የሚያስገርመኝ ይኽ አይደለም:: እንዳንድ ከዋክብት አሉ--በተለየ አጠራር ተወርዋሪ የምንላቸው:: በሌሊቱ ኅዋ ውስት ከአንዱ መአዘን ሰማይ ወደ ሌላው ተወርውረው ብልጭ ብለው ይጠፋሉ:: ይህ ሁሉ የሚሆነው በቀፅበት ነው::ያንን በጨለማው ግርማ የተዋጠውን ኅዋ በብርሃን ጎርፍ ሰንትቀው አጥለቅልቀውት ይጠፋሉ:: ተመልካችም ከመገረም በሚመነጭ ዝምታ ይዋጣል:: በኢትዮዽያም የሥነ ጽሑፍ ኅዋ ውስጥ ዮፍታሔ ንጉሤ አንድ ተወርዋሪ ኮከብ ነበር። |
|
|
|
|
|
[1929 - 1967] |
|
ዮሐንስ አድማሱ |
|
|
|
|
|
[1935 - 2005] |
|
ደ/ር ዮናስ አድማሱ |
ዶ/ር ዮናስ አድማሱ በ1935 ዓ.ም አዲስ አበባ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ የቄስ ትምህርት ተከታትለዋል። የዘመናዊውን የመደበኛ ትምህርት የተቀላቀሉት እድሜያቸው ዘጠኝ አመት ሲሞላ ነበር፤ የመደበኛ ትምህርታቸውን በኮከበ ጽብሐ ትምህርት ቤት ተከታትለው እንደጨረሱ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በመቀጠል በ1959 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀበሉ። ለተጨማሪ ትምህርት ወደ አሜሪካን ሀገር ከመጓዛቸው በፊት እንደተመረቁ ወዲያውኑ በተማሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአስተማሪነት ተቀጥረው የማገልገል እድል አግኝተዋል። በአሜሪካን ሀገር ካሊፎርኒያ ዪኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ተከታትለው በሶሺዮ-ሊንጉስቲክስ Socio-Linguistics የኤምኤ/MA ዲግሪያቸውን ከካሊፎርኒያ የኒቨርሲቲ ሎስአንጀለስ ተቀብለዋል። በ1962 ዓ.ም. ትምህርታቸውን በመቀጠል በአፍሪካ ጥናት/African Studies Programme እንዲሁም የዶክትሬት/PhD ዲግሪያቸውን በComparative Literature ቀድመው ከተማሩበት ከካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ሎስአንጀለስ ዩኒቨርሲቲ ተቀብለዋል።
ዶ/ር ዮናስ አድማሱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለበርካታ አመታት በተለያየ የሃላፊነት ቦታ በመያዝ በአስተማሪነት፣በተመራማሪነት፣በአስተዳደር እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባል በመሆን ከዚች አለም በአጸደ ሕይወት እስከተለዩባት የካቲት 1,2005 ዓ.ም. ድረስ በቀናነትና በትጋት ሀገራቸውን አገልግለዋል። |
ዶ/ር ዮናስ አድማሱ በ1935 ዓ.ም አዲስ አበባ ተወለዱ። |
|
|
|
|