ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
አበራ ለማ
የደራሲው ሥራዎች
1.   ኩል ወይስ ጥላሸት(ግጥምና ቅኔ)
2.   አውጫጭኝ(ግጥምና ቅኔ)
3.   ሽበት(ግጥምና ቅኔ)
4.   የማለዳ ስንቅ(ግጥምና ቅኔ)
5.   ሕይወትና ሞት(ልብወለድ)
6.   የማለዳ ስንቅ(ልብወለድ)
7.   መቆያ(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
አበራ ለማ የተወለደው በ ፲፱፵፫ ዓ.ም. ፍቼ ሰላሌ ውስጥ ነው። እድገቱ ወሊሶንና አዲስ አበባን ያካትታል። ካገራችን ገጣሚያንና አጫጭር ልቦለድ ጸሓፊዎች አንዱ ነው። በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ጥናት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማዕርግ ተመራቂ ነው።

ሙያው ጋዜጠኘት ሲሆን፣ በማስታወቂያ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሬዲዮና ፕሬስ መምሪያዎች ሠርቷል። ከጦር ግምባር ጋዜጠኝነት እስከ የሕዝብ ማመላለሻ ኮርፖሬሽን የማስታወቂያና ሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት ኃላፊነት ዘልቋል። በተለያዩ የኪነጥበባት ዘርፎች ነቃሽ ሃያሲነትም ይታወቃል።

እስከ ሰማንያዎቹ አሠርት አጋማሽ ድረስ፥ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ዋና ጸሃፊ ሁኖ አገልግሏል። ዛሬ የኖርዌይ ነዋሪ ነው።

ኖርዌይ ደራስያን ማኅበር ብቸኛውና የመጀመሪያው ጥቁርና ባፍ መፍቻ ቋንቋው የሚጽፍ አባል ደራሲ ነው። በዚህ ማኅበር ውስጥ የዓለም አቀፍ ኮሚቴው የረዥም ዘመን አባል በመሆንም ይታወቃል።

ባለቅኔ ሎሬትጸጋዬ ገብረመድህንንና (2005 እ.ኤ.አ.) ስዊድናዊ/ኤርትራዊ የሆነውን የአሥመራውን እስረኛ ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅን (2009 እ.ኤ.አ.) ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ሽልማት እንዲሸለሙ በማድረጉም በሰፊው ይታወቃል።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com