ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
መንግስቱ ገዳሙ
[1920 - 1988]
የደራሲው ሥራዎች
1.   ሶማሌው(ልብወለድ)
2.   መሰላል(ልብወለድ)
3.   አሳማና ድመት(ልብወለድ)
4.   ሌላው እንደሚያይህ ጠባይና የሕይወት አቋቋም(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
መንግሥቱ ገዳሙ በሲዳሞ ክፍለሀገር ተወልደው ከብት ሲጠብቁ ያደጉ የባላገር ልጅ ናቸው፡፡ በልጅነታቸው እባብ ነድፎዋቸው ለስድስት ሳምንታት ኀሊናቸውን ስተው ከሰነበቱ በኋላ ከሞት ተርፈዋል፡፡ ዕድሜያቸው ከፍ ሲል በወታደርነት ተቀጥረው ሠርተዋል።

ከወታደር ዓለም ወጥተው ፖስታ፣ ቴሌፎንና ቴሌግራፍ ሚኒስቴር ውስጥ ተቀጠሩ፡፡ በሥራቸው ጎበዝ ስለነበሩ በዕድገት ወደ ድሬደዋ ተዛወሩ፡፡ ባሕል አስከብራለሁ እያሉ በርኖስ እየለበሱ ቢሮ በመገባታቸው የሚታወቁት መንግሥቱ ገዳሙ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ከገቡ በኋላ “ሞገደኛ ጋዜጠኛ” የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በጋዜጣ የጀመሩት ጽሑፍ ደራሲ እንዲሆኑ ስለገፋፋቸው ሳይሆን አይቀርም ብዙ “ቤሳ” መጻሕፍት ጽፈዋል፡፡ የጻፉትን መጻሕፍ ይዘት ባብዛኛው አያስታውሱም፡፡ ካሳተሟቸው መጻሕፍት መካከል “ሶማሌው” በ፲፱፶፯ ዓ.ም. “መሰላል” በ፲፱፶፱ ዓ.ም. እና “አሳማና ድመት” በ፲፱፶፱ ዓ.ም. ተጠቃሾች ሲሆኑ ሌሎች ኢ ልብወለድ መጻሕፍትም በተለያዩ ጊዜዎች አሳትመዋል፡፡

የመንግሥቱ ገዳሙ ባህርይ አፈንጋጭ የሚሉት ዓይነት ነው፡፡ ሞገደኛው ጋዜጠኛ መንግሥቱ በተወለዱ በ48 ዓመታቸው ሐምሌ 18 ቀን በ፲፱፷፰ ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com