ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ብርሃኑ ዘርይሁን
[1925 - 1979]
የደራሲው ሥራዎች
1.   የአብዮቱ መባቻ(ልብወለድ)
2.   የቴዎድሮስ ዕንባ(ልብወለድ)
3.   የበደል ፍጻሜ(ልብወለድ)
4.   የአብዮት ማግስት(ልብወለድ)
5.   ሞረሽ(ተውኔት)
6.   ጣጠኛው ተዋናይ(ተውኔት)
7.   አማኑኤል ደርሶ መልስ(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ብርሃኑ ዘርይሁን በ1925 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተክርስትያን ትምህርት ተምረዋል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጎንደር ይገኝ በነበረው በቀድሞው ቀዳማዊ ሃይለሥላሴ ትምህርትቤት አጠናቀቁ፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥተው በተግባረ እድ ትምህርት ቤት በሬዲዮ ቴክኒሺያንነት ሙያ ተመረቁ።

ሥራ የጀመሩትም በመምህርነት ነው። በወቅቱ በካርታ ሥራ ድርጅት ቴክኒሺያንነት ሙያ ሠርተዋል። ከዚያም የጦር ሚኒስቴር እየተባለ ይጠራ በነበረው የአሁኑ መከላከያ ሚኒስትር በአስተርጓሚነት አገልግሏል። ማስታወቂያ ሚኒስትር እንዲዛወሩ ከተደረገ በኋላ የኢትጵያ ድምጽ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆነዋል። ከሶስት አመት በኋላ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆነው የማይረሳ ተግባር አከናውነዋል።

ብርሃኑ ዘርይሁን የደረሱት ‹ሞረሽ› በ1972 ዓ.ም፤ ‹ጣጠኛው ተዋናይ›በ1975 ዓ.ም እና ‹አባደፋር› በ1977 ዓ.ም፤ የተባሉት ቴያትሮቻቸው ተወዳጅ ነበሩ።

ከጻፏቸው መጻሕፍት ውስጥም ‹የቴዎድሮሥ እንባ › በ1958 ዓ.ም፤ ‹የእንባ ደብዳቤዎች› በ1961 ዓ.ም እና የታንጉት ምሥጢር› በ1978 ዓ.ም፤ እንዲሁም ለረጅም ተከታታይ ጊዜያት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ሲተረኩ የነበሩት ‹የአብዮት ዋዜማ፤የአብት መባቻና የአብዮት ማግስት› የተሰኙት ማጸሐፍት ይገኙበታለል።

ብርሃኑ ዘርይሁን ለሐገራቸው የስነ ጽሁፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዎ አበርክተዋል። በቀዳሚዎቹ ዘመናት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበርን በሥራ አመራር አባልነት ካገለገሉት መካከል አንዱ ብርሃኑ ናቸው።

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com