ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
በአሉ ግርማ
[1930 - 1976]
የደራሲው ሥራዎች
1.   ኦሮማይ(ልብወለድ)
2.   ከአድማስ ባሻገር(ልብወለድ)
3.   የህሊና ደወል(ልብወለድ)
4.   የቀይ ኮከብ ጥሪ(ልብወለድ)
5.   ሐዲስ(ልብወለድ)
6.   ደራሲው(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
በዓሉ ግርማ በቀድሞ አጠራሩ በኢሊባቦር ክፍለ ሀገር ሱጴ በምትባል ሥፍራ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡

ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዘነበወርቅ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጀኔራል ዊንጌት አጠናቀዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በፖለቲካል ሳይንስና ኢንተርናሽናል ሪሌሽን የመጀመሪያ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

በዓሉ ግርማ በተለይ በልብ ወለድና በፈጠራ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ተወዳጅነትና ዝናን ያተረፉ ዕውቅ ደራሲ ነበሩ፡፡ ከጻፏቸው በርካታ ድርሰቶች መካከል በ፲፱፷፪ ዓ.ም. የታተመው "ከአድማስ ባሻገር" የተሰኘው መጽሐፋቸው በሩሲያ ቋንቋ ተተርጉሞ ለቀድሞዋ ሶቪየት ኀብረት አንባቢያን ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም በጋዜጠኝነት ሙያም ስማቸውን ያስጠሩ ነበሩ፡፡ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ፣ የመነን መጽሔት፣ የአዲስ ሪፖርተር መጽሔትና የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ሠርተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ብዙ ወጣት ጋዜጠኞችን ለማፍራት ጥረት አድርገዋል፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት ይታተም የነበረው አዲስ ሪፖርት የተባለውን መጽሔትም ደረጃው ከፍ እንዲልና በዓለም አቀፍ ደረጃም እንዲገመገም አድርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሬዲዮም በኃላፊነት ሠርተዋል፡፡ በዓሉ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ያበረከቱና ብዙ ሥራዎችን የሠሩ ደራሲ ናቸው፡፡ የመጨረሻው መጽሐፋቸው "ኦሮማይ" በወቅቱ በነበረው መንግሥት ሊደገፍ ባለመቻሉ በ፲፱፸፮ ዓ.ም. ለሕይወታቸው መጥፋት መንስኤ ሆኗል፡፡ በዓሉ ካሳተሟቸው መጽሐፍት መካከል "የሕሊና ደወል" "የቀይ ኮከብ ጥሪ" በ፲፱፷፮ ዓ.ም. እና "ሐዲስ" በ፲፱፸፪ ዓ.ም. ይገኙበታል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com