ውሃ ውሃ የሚያሰኝ ጉዞ

ዋና ገጽ | የኢትዮጵያ ታሪክና ሥነጽሑፍ የምርምር ሥራዎች /Researches on Ethiopian History and Literature/
+ - Font Size  
 
 

ውሃ ውሃ የሚያሰኝ ጉዞ


ብርሃነመስቀል ደጀኔ
  


**ይኽ የጉዞ ማስታወሻ (ኅዳር 1987 ዐ.ም) አስቀድሞውኑ የጉዞዬ ዋነኛ አንቂና ባለውለታዬ ጭምር ለኾነው ወዳጄ ልቤኢንጅነር ርእሶም ገብረእግዚአብሔር (1947-2005 ዐ.ም) መታሰቢያነት የቆመ ሲኾን፤በወቅቱም መጣጥፉ እርሱ በኃላፊነት ይሰራበት ለነበረው የውሃ ሥራዎች ዲዛይን ድርጅት (ተከዜ ፕሮጀክት) መጽሔት ላይ “ከበላይ-ከተከዜ ፕሮጀክት” በሚል ብርዕ ስም(ርእሶምን?! ለማመላከት) እንዲታተም አበርክቼው ሳይታተም የቀረ ጽሑፍ ነው፡፡ ተረኩን በዚኽ መንፈስ ኢንጅነር (ሃይድሮሎጂስት) እንዲተርከው ተወጥኖ የነበረ መኾኑንም ልብ ይሏል፡፡

እግዞኦ! ውሃ ውሃ የሚያሰኝ ጉዞ!!! ቀድሞ የኔን አጋጣሚ የተካፈለ ካለ ፥ ላይደነቅ ይችል ይኾናል፡፡ ይኹንና ያጋጠመኝ፥ ከመኪና ሆድ ሳይወጡ፥ ቀን ሙሉ ፈጅና ሳምንት በሌ፥ ተከታታይ ጉዞ ነበር፡፡ እንዲኽ ዓይነት ምድር ቆንጣጭና የትየለሌ ጉዘት ሳደርግ፥ ይኽ በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር፡፡ እና “አጀብ!” ያሰኘኝም ይኼው ነበር፡፡

በእርግጥ እንዳልዋሽ ያኽል፥ ከዚኽ ቀደም ረዥም ጉዞ ማድረጌን  ማበል አልፈልግም፡፡ ስለውሃ ኃይልና ልማት ጥበብ - ማለትም ሃይድሮሊክስ ለማጥናት ክፍለ አህጉራት አቆራርጦ የአየር በረራ ወደ ባሕር ማዶ አድርጌአለኹ፡፡ ግና ያ ሌላ፥ ይኼ ሌላ! የፊተኛው የጢየራ፥ይኼኛው በማኪና፡፡ እና በአገር ቤት ደረጃ - ክፍላተ ሀገር ዘለቅና ረዥም የመኪና ጉዞ ሳደርግ፥ ይኼየመጀመሪያዬ ነው ለማለት ነው፡፡

አስቀድሞ ግን “ይኽን ያኽል ማዳነቅ ከየት ተፈጠረብኽ?” የሚለኝ አይጠፋ ይኾናል፡፡ ቀልጠፍ ብዬ ልመልሰውና - ምናልባት ምናልባት - ያዲሳባ ልጅነቴ ሊኾን ይችላል፡፡ ከዚኽ ባለፈው ግን፥ ጉዞው በአጠቃላይ ከፈጠረብኝ ልዩ ስሜት በመነጨ መኾኑን አንባቢዬ በቅንነት እንዲረዳልኝእፈልጋለኹ፡፡ አኹንም “እንዴት?” ባይ ካለኝ፥ ያው እንዳልኩት ንክር አዲሳቤ ነኝ፡፡ እና በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች - እሱም በተመጠነ ርቀት - ካዲሳባ ቢሾፍቱ፥ በሰሜን ምዕራብ -ከደብረሊባኖስ፥ በሰሜን ምሥራቅ ደግሞ ከደብረብርሃን አልፌ ማላቅ ያራዳ ጉልት ነኝ፡፡ ያኹኑን ዕድል ልበለው - ሎተሪ ወይም አጋጣሚ ወይም የሥራ ግዴታ የፈጠረው - ጉዞዬ፥ ከፊል ደብረ ኢትዮጵያን ያካተተ ነበር፡፡ ማለትም ሰሜን ኢትዮጵያን - ከአዲስ አበባ - ባሕር ዳር - ጎንደር -አክሱም - አዲግራት - መቐለ - ደሴን አቆራርጦ፥ አገሩን “አጀብ!” እያሉ አዲሳባ ከች! ባጭሩ፥ ይኼው ገጠመኜ - ልጆቹ እንደሚሉቱ - “ወይ ታሪክ! ወይ ጂኦግራፊ!” ነው ያሰኘኝ፡፡ ሌላም፥ሌላም!!

ወይ ሰሜን ኢትዮጵያ !?! ይቅርታ! አስቀድሞ ራሴን ማስተዋወቅ ነበረብኝ መሰለኝ፡፡ አዎ! በመጀመሪያ፥ ያዲሳባ ልጅ ነኝ ብያለኹ፡፡ ኹለተኛ፥ ሠራተኛ - የውሃ ሀብት ልማት ሚኒስቴር ባልደረባ፡፡ የሥራ ክፍሌም በሸለቆዎች ጥናት ሥር ነው፡፡ በሙያዬ - መሀንዲስ - ከመሀንዲስም የውሀ መሀንዲስ ነኝ፡፡ ሥልጠናዬ በኹለት ዘርፍ ነው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪዬን በሲቪል ምህንድስና ያገኘኹ ሲኾን፥ ኹለተኛውን ደግሞ በውሃ ምህንድስና ነው፡፡ ባጭሩ፥ ሃይድሮሎጂስት ነኝ፡፡ ከዚኽ በስተቀረ፥ በዝንባሌዬ - ሙዚቃ ማድመጥ፥ንባብና ጥናታዊ ፊልሞች ማየት እወዳለኹ፡፡ ንፋስና እሳት በጣም የምፈራ ሲኾን፥ ሰው፥መሬትና ውሃ ደግሞ ባም በጣም እወዳለኹ፡፡ ራሴን ለማስተዋወቅ ያኽል፥ ይኼ በቂ ይመስለኛል፡፡

እና ያ በአድናቆት የተዋጥኩበት ጉዞ - ቀላል፥ አዛናኝና የሽርሽር ጉዞ አልነበረም፡፡ ለፕሮጀክት ጥናት፥ ሁለገብ የባለሙያዎች ቡድን ያሰባሰበ አድካሚ የሥራ ጉዞ ነበር፡፡ “እናስ?” የሚለኝ አይጠፋ ይኾናል፡፡ በጀ! ይኽቺ አጭር ማስታወሻ፥ ስለጉዞዬ የሥራ ራፖር እንዳይደለችና አንባቢዬንም በዚኽ መሰል ጉዳይ እንደማልደፍረው ይታወቅልኝ፡፡ ያው እንዲኽ ዐይነቱ ጉዳይ ከቅርብ አለቃዬ ጋር የሚያልቅ ነገር ነውና፡፡ ነገሬ ወዲኽ ነው፡፡ የጉዞው ድካም ከለቀቀኝ በኋላ፥ ጉዞው የፈጠረብኝን ልዩ ልዩ ትዝታ፥ ለአንባቢ የማካፈል ጉጉት አላስቀምጥ ስላለኝ ነው፡፡ እናስ? “የብቻ ትዝብቴን እነኾ!!” ለማለት ነው፡፡ እና እንደሥራ ከፊል ረቂቅ ሪፖርት ሳይኾን፥ በጎ ፈቃዳችኹ ኾኖ - እንደ አንድ ሀገረኛ ቱሪስት ይፋዊ ትዝብት አድርጋችኹ ቁጠሩልኝ፡፡

ምናልባት ግን አኹንም “ምነዋ እንደ ቱሪስት ትዝብት?!” የሚለኝም አይጠፋ ይኾናል፡፡ ብርቱ ጠያቂ ካለ ደግ ! አንደኛ፥ ሰሜን ኢትዮጵያን ገና እንዳዲስ እንግዳ በማየቴ፥ ራሴን ከቱሪስት እኩል ቆጠርኩት፡፡ ኹለተኛ፥ ከሃይድሮሊክስ ባለሙያነቴ፥ ከሥራ ግዳጄና ኃላፊነት ባሻገር -ማለትም አብሮኝ ከኼደው ቡድን ቅኝት መኻል፥ ይኽ የኔ የነጠላው ሰው ግለኛ ትዝብት በመኾኑ ነው፡፡ እይታና ቅኝቴም ቱሪስት አከል በመኾኑ ነው፡፡

እና አነሳሴ፥ ቢያንስ ቢያንስ ገና እንደ እንግዳ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ “በቱሪስት ዓይኔ” ስለቃኘዃቸው የሀገሬ ሰሜናዊ ክፍሎች ያደሩብኝን አንዳንድ ግለኛ ትዝብቶቼን ባካፍላችኹ አያጎዳም ብዬ ነው፡፡ “ምን አሳሰበኽ?” እባል ይኾን? እንጃ! ከኾነም፥ ይኸ ደግሞ አንድ ፊደል የቆጠረ፥ “የሠለጠነ” እና “የተማረ ሰው” የሚባል ሰው ኹላ አንድ አነስተኛ ተግባር ነው፡፡ እና እንኳን እኔ አንድ ነጠላው ዜጋ፥ የሀገሬ ተጓዥ ኹሉ፥ ሲኾንም ባለሙያ እንዲኽ ዓይነት የጉዞ “ሚምዋር” ቢኖረው አጥብቄ የምመኝ ሰው ነኝ፡፡ ይኼ ቢኾን ስለሀገራችን መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ፥ ስለተፈጥሮ ሀብት ይዞታችን፥ ሰለሕዝባችን ልዩ ልዩ የአኗኗር ደረጃ፥ ስለሀገራችን ዕድገት ኹኔታ ስንት ጠቃሚ የባለሙያ የልማት መረጃዎች እንለዋወጥ ነበር?! የሚል ጉጉቴ ብርቱ ነው፡፡ ባጭሩ፥ ይኽቺ ሙከራዬ፥ ከዚኹ ወሰን የለሽ ምኞቴ ወይም ቁጭቴ መኻል ቅንጣቲቱ ናት፡፡ ቢያንስ ፥ የዚኹኑ በጎ ምኞቴን አንዲት ጠጠር እንኳ ልወርውር ማለት ነው፡፡ እና አድናቆት ያነሣሣው ብርቱ ስሜት ካስጫረኝ በላይ፥ በአንድ ፊት (ምሁራዊ) የሞራል ግዴታም ጭምር ገፋፍቶ - እነኾ እርሳስ አስጨብጦኛልና ይልቅስ “ትዝብትኽ ምንድነው?” ብባል፡፡ እና “እጅኽ ከምን?” በሉኝ፡፡

ሙሉ ጽሑፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ብርሃነመስቀል ደጀኔ
 
ይህን ጽሑፍ ወዳጆችዎ ፌስቡክ ገጽዎ ላይ ለማስነበብ:  
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethioreaders.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Sisay Gebregziabher [95 days ago.]
 Dear ብርሃነመስቀል,
Thank you very much for sharing this wonderful, amazing, historical, memorable, magnificent memoir. I read it with great interest and it took me around to the northern part of Ethiopia through an imaginary abstract flying object. And above all you dedicated the memoir for Yaye, my lovely great brother who can’t be forgotten forever. You considered Yaye to be the story teller and I love that. You really expressed or acknowledge your love, great respect, appreciations and your indebtedness to him through your memoir. I always love to hear anything related to him and I always mention his name in my talks. This is a priceless great gift to me and I don’t have enough words to thank you. May God bless your heart and may the ETHIOPIA AMLAK bless you.

Nebyou Woubshet [95 days ago.]
 What a wonderful piece of writing, a lot of history, a lot of places, a lot of names discovered in a single piece of travelogue. I have learned a lot about my country, Not only that but I also amazed, enjoyed and admired the writing style the author exercised. The piece revealed the expressive power and the beauty of Amharic language. I wish I could read more write-ups like this coming from the Mr. Berhane. Thank you a lot.

Hailu [84 days ago.]
 I like as a research paper, It is full of important facts of the northern parts of Ethiopia. The facts stated with regard to Abay is a reference. Nice work.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
 
 
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
*
   
 
     
     
ፊደልን ከkeyboard ማመሳሰያ።
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com