[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
የኢትዮጵያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
አ
በ
ቨ
ገ
ደ
ጀ
ሀ
ወ
ዘ
ዠ
ሐ
ኀ
ጠ
ጨ
የ
ከ
ኸ
ለ
መ
ነ
ኘ
ሠ
ዐ
ፈ
ጸ
ፀ
ቀ
ረ
ሰ
ሸ
ተ
ቸ
ጰ
ፐ
ወደ ዋና ገጽ
[1555 - 1589]
ዐፄ ሠርፀ ድንግል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሠረቀ ብርሃን ገብረ እግዚ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሣህለስላሴ ብርሃነማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም በቀድሞው አጠራር ሸዋ ክፍለሀገር በሚባለው በጨቦና ጉራጌ ተወለዱ፡፡ የ1ዐኛ ክፍል ተማበ በነበሩበት ወቅት አባታቸው በመሞታቸው የቤተሰብ ኃላፊ ለመሆን ተገደዋል።
በብዛት የፍልስፍና እና የሥነ ጽሑፍ መጻሕፍትን ያነባሉ፡፡ ለሚጽፏቸው መጻሕፍት የፍልስፍና መሠረት እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡፡ ለዚህ ዓለም ያላቸውን አዎንታዊ አመለካከት ለአንባቢየቸው ለማሳየት ይፈልጋሉ፡፡
ሳህለሥላሴ ከሎስአንጀለስ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ ብዙም አልሠሩትም፡፡
በፕሮፌሰር ዎልፍ ሌስላው አማካኝነት የመጀመሪያውን መጽሐፍ "የሸንጋይ መንደር" በሚል ርዕስ ጽፈዋል፡፡ መጽሐፉ በእንግሊዝኛ ተተርጉሟል፡፡"ወጣት ይፍረደው፤ አፈርሳታ" እና ሌሎች ድርሰቶችን ጽፈዋል፡፡ የሁለት ከተሞች ወግ፣ መከረኞችና እምዩ ከትርጉም ሥራዎቻቸው መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም በቀድሞው አጠራር ሸዋ ክፍለሀገር በሚባለው በጨቦና ጉራጌ ተወለዱ፡፡ የ1ዐኛ ክፍል ተማበ በነበሩበት ወቅት አባታቸው በመሞታቸው የቤተሰብ ኃላፊ ለመሆን ተገደዋል።
ሥምረት አያሌው ታምሩ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1921 - 1995]
ዶ/ር ሥርግው ሀብለሥላሴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዶ/ር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ
ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፳፩ - ታህሣሥ ፳፱ ቀን ፲፱፻፺፭
ዶ/ር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ ከአባታቸው ከመሪጌታ ሐብለ ሥላሴ ዘውዴና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዘውዲቱ ደስታ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ. ም. አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ። ባገራችን ሥርአትና ባህል መሰረትም እድሜአቸው ለቀለም ትምህርት በደረሰ ጊዜ አዲስ አበባ በሚገኘው የልደታ ደብር ፊደል ቆጥረው ዳዊት ደግመዋል። ከዚያም በኋላ ዘመናዊ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አዲስ አበባ የቅድስት ሥላሴ ትምህርት ቤት አጠናቀቁ። በጊዜው ተመርጠው ከቀረቡት የኢትዮጵያ ተማሪዎች አንዱ ሆነው ግሪክ አገር ቆሮንጦስ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እዚያ ከሚገኘው መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ፲፱፻፵፩ ዓ. ም. ተላኩ። ይህንን ትምህርት አጠናቅቀው እዚያው ግሪክ አገር ባለው አቴና ዩኒቨርስቲ ገብተው ከአራት ዓመት በኋላ የባችለር ዲግሪያቸውን በቲዎሎጂ ጥናት ተቀበሉ። ከፍተኛ ትምህርታቸውን በመቀጠል ፲፱፻፶ እስከ ፲፱፻፶፪ ዓ. ም. ድረስ በጀርመን አገር በሚገኘው ቦን ዩኒቨርስቲ በጥንታዊ ታሪክ ምርምር የዶክትሬታቸውን ማእረግ ተቀበሉ። ከዚያም በኋላ አገራቸውን ለማገልገል ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከ ፲፱፻፸ ዓ. ም. ድረስ ለ፲፯ ዓመታት በጊዜው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጥንታዊና መካከለኛ ዘመን ስልጣኔና ታሪክ የመጀመሪያ ምሁር ሆነው ሠርተዋል። በተጨማሪም ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቲዎሎጂ አስተማሪ በመሆን አገልግለዋል። አገልግሎታቸውን በመምህርነት ብቻ ሳይወሰኑ ተመራማሪነታቸውንም አጣምሮ በተመለከተ እንደ London University ፤ በአሜሪካንም አገር እንደ Harvard University እና Princeton Univeristy ፤ በጀርመን አገር Heidlberg University፤ እንዲሁም በሆላንድ Lieden University በመሳሰሉት በዓለም በታወቁ ዩኒቨርስቲዎች በፌሎሽፕ እየተመረጡ በተለያየ ጊዜያት በከፍተኛ ደረጃ ልዩልዩ ጥናቶችን አከናውነዋል።
ዶ/ር ሥርግው በትምህርት ዓለም ካሳለፏቸው ዘመናት በላይ በመምህርነትና በምርምር እስከ ሕይወታቸው ፍጳሜ ድረስም ሠርተዋል። በዚህም መሠረት ለተማሪዎችና ለተመራማሪዎች እጅግ ጠቃሚ ሆነው የሚገኙ መጻሕፍትንና ስነጽሁፎችን አዘጋጅተው አሳትመዋል። ከድርሰቶቻቸው ውስጥ ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ብቻ ያህል፦
• በእንግሊዘኛ ቋንቋ ፲፱፻፷፩ ዓ. ም. የታተመው Bibliography of Ancient and Medieval Ethiopian History
• ፲፱፻፷፫ ዓ. ም. የታተመው Ancient and Medieval Ethiopian History to 1270
የተባሉት ይገኙበታል። እነኚህ ሁለት መጻሕፍቶች ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚገኙ እውቅ በሚባሉ ዩኒቨርስቲዎችና መጻሕፍት ቤቶች ቀርበው የኢትዮጵያን ታሪክ ለሚያጠኑ ሁሉ እንደ ዋና የምርምር ዶክሜንት reference document ሆነው እስከ ዛሬ ድረስ ይገኛሉ፤ ወደፊትም ማገልገላቸውን ይቀጥላሉ። እነዚህም መጻሕፍት ከታተሙ በኋላ ዶ/ር ሥርግው የፕሮፌሰርነት ማእረግን ለመሸለም በቅተዋል።
ዶ/ር ሥርግው በአማርኛ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበውን በ፲፬ ቅጽ የተተነተነውን ሰፊ የIትዮጵያ Oርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን መዝገበ ቃላት በአቀናባሪነት ያዘጋጁ ናቸው። ይህም ሥነጽሁፍ እስከ ዛሬ ድረስ ለቤተ ክህነት ሊቃውንት ተማሪዎችና ትልቅ አገልግሎትን በማበርከት ላይ ይገኛል። ከላይ ከተጠቀሱትም መጻሕፍት በተጨማሪ የኢትዮጵያን ጥንታዊ የሥነጽሁፍ አቀራረጽንና የመጻሕፍት አጠራረዝን የሚገልጽ Bookmaking in Ethiopia የተባለ መጽሐፍ አዘጋጅተው አቅርበዋል። በመጨረሻም በ፲፱፻፺፪ ዓ. ም. የአፄ ምንሊክን የሕይወት ታሪክ በተለይ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከውጪው ዓለም ጋር ኢትዮጵያን እንዴት እንዳገናኝዋት የሚያብራራ ብዙ ኢትዮጵያውን ያደነቁትን ድርሰትም አበርክተዋል። ከነዚህ መጻሕፍት በተጨማሪ ከሃያ ያላነሱ የኢትዮጵያንና የቤተ ክርስቲያንን ጥንታዊ ታሪክ የሚመለከቱ ልዩ ልዩ ሠፊ ስነጽሁፎች በበርካታ የዓለም ቋንቋዎች አዘጋጅተው አቅርበዋል።
በተጨማሪ ዶ/ር ሥርግው ለአገራቸው ካበረከቱአቸው ዋና ሥራዎች አንዱ ሆኖ የሚቆጠረው የIትዮጵያ ብራና መጻሕፍት ድርጅት መስራች ሆነው ያገለገሉበት ጊዜ ነበር። የዚህ ድርጅት የመጀመሪያ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ከ፲፱፻፷፮ እስክ ፲፱፻፸፩ ዓ. ም. በተለያዩ ገዳማትና አድባራት በመዘዋወር በብዙ መቶ የሚቆጠሩ የጥንት ጽሑፎች በማይክሮፊልም ተቀርፀው ለታሪክና ለሚቀጥሉት ትውልድ እንዲቆዩ ያደረጉ ሰው ናቸው።
ከወይዘሮ ሰላማዊት መኰንን ጋር ሐምሌ ፲፱፻፶፰ ዓ. ም. በታእካ ነገስት በዓታ ቤተ ክርስቲያን የሠርግ ስነ ስርዓታቸውን ፈፀሙ። ከዚህም ትዳር አምስት ልጆች ናዖድ፣ ብሌን፣ ፈቃደ ሥላሴ፣ ናብሊስና እሜንን አፍርተዋል። ከነዚህም ልጆች መካከል የሦስቱን ትዳር ለማየት በቅተው፤ ሦስት የልጅ ልጆች ሆሣእና፣ ልያና እምነትን ለማቀፍ ችለዋል። ዶ/ር ሥርግው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ታህሣሥ ፳፱ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ. ም. በሚዩኒክ ከተማ በጀርመን አገር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ምንጭ:
www.sergew.com
ዶ/ር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ
ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፳፩ - ታህሣሥ ፳፱ ቀን ፲፱፻፺፭
ዶ/ር ሥርግው ሐብለ ሥላሴ ከአባታቸው ከመሪጌታ ሐብለ ሥላሴ ዘውዴና ከእናታቸው ከወ/ሮ ዘውዲቱ ደስታ ሰኔ ፰ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ. ም. አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ።
ሥዩም ተፈራ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሥዩም ተፈራ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ሚኒልክ ት/ቤት አዲስ አበባ ከተማ ተከታትለዋል። ከአ.አ.ዩኒቨርሲቲም በቴአትር ሙያ ሥልጠና ወስደዋል፡፡
የሙሉ ጊዜ የመድረክ ተውኔቶችን፣ ሙዚቃዊ ድራማዎችን አዘጋጅተዋል፡፡ ከሥራዎቻቸው መካከል “ቤቱ”፣ “ሐሙስ”፣ “ዱላው”፣ የተሰኙ ቴአትሮች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በመዘጋጃ ቴአትር ቤትና በራስ ቴአትር አዘጋጅ፣ ጸሐፌ ተውኔትና ተዋናይ በመሆን አገልግለዋል፡፡ “ይፈለጋል”፣ በሚል ርዕስ በቀረበ ፊልም መሪ ተዋናይ ሆነው ሠርተዋል፡፡ “ሦስት ዕንባዎች”፣ በሚል ርዕስ የግጥም መድብል አሳትመዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ሥዩም ተፈራ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ሚኒልክ ት/ቤት አዲስ አበባ ከተማ ተከታትለዋል።
ሰርቅ ዳንኤል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሰይድ ሙሐመድ ሣዲቅና ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሰሎሞን ደሬሳ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
" ደራሲ ይደርሳል ፤ አንባቢ ያነባል ፤ ሃያሲ ይተቻል። ምንም ቢወታተብ የስነጽሑፍ ጣጣ ከእንዚህ ድንክዬ ዐረፍተ ነገሮች አያልፍም" ያለው ሰሎሞን ዴሬሣ በወለጋ ጩታ በተባለች መንደር በ1929 ወይም በ1930 ዓ.ም. ተወለደ። ራሱ እንደገለጸው የተወለደበትን ዓመትና ዕለት እቅጩን አያውቀውም። በጣሊያን ወረራ ጊዜ አራት አመት ሲሞላው ዘመዶቹ ወደ አዲስ አበባ አመጡት። ስለዚህ እራሱ እንደሚያምንበት አገሩ አዲሳባ ነው።
"ልጅነት"! ትምህርት አልገባ ብሎታል ተብሎ ያልገባበት ትምህርት እንዳልነበር የገለጸው ሰሎሞን ደሬሣ በ16 ዓመቱ በቀድሞው ቀ.ኃ.ሥ ዩኒቨርሲቲ ገባ። በዚሁ የ"ውምበርሲቲ" ቆይታው ከትምህርቱ ይልቅ የ" ልጅነት ጨዋታ" ያመዝንበት ስለነበር - መደበኛ ትምህርቱን አላጠናቀቀም። ይልቅ በወቅቱ ዩኒቨርሲቲ አብረውት ከነበሩት ልጆች ቤተመጻሕፍቱን እንደሰሎሞን ዴሬሣ የተጠቀመበት ተማሪ እንዳልነበር ይነገርለታል።
ሰሎሞን የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን አቋርጦ ለ3 ወራት ያህል በኢትዮዽያ ሬዲዮ በእንግሊዝኛ ዜና አንባቢነት ተቀጠረ። "በ"ልጅነቱ" የተነሣ ሥራ ላይ ከአለቃው መጋጨት የጀመረው ሰሎሞን እንዳጋጣሚ ፈረንሳይ ሀገር ነፃ ትምህርት ዕድል አገኘ።
ሰሎሞን ፓሪስ ሲደርስ 20 ዓመቱ ነበር። በቱሉዝ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ቀጠለ። ትምህርቱ በፈረንሳይኛ ቢሆንም እንዳልተቸገረ ይናገር የነበረው ሰሎሞን ከጥናቱ ይልቅ ቀልቡን የሳበው የሀገር ጉብኝት ነበር። አውሮፓን ሲዞር ከርሞ ለፈተና ይቀመጣል፤ ያልፋል።
ፓሪ! የአውሮፓ ታላላቅ ደራሲያን የሙዚቀኞችና የሠዓሊያን መናሃሪያ ነበረች። ሰሎሞን - ትዝታውን ነግሮን ነበር። "-- ፓሪስ ነፃ ክፍት ከተማ ስለነበርና ልጅ ስለነበርኩ ቁልፉን የከተማው ከንቲባ እንደሰጠኝ ነው ያየሁት። በኋላ ትልልቅ የሆኑ ፀሐፊዎች የሙዚቃ ሰዎች ሰዓሊዎች ነበሩ። እንዲያውም ለአንድ አቫንጋርድ የፈረንሳይ ጋለሪ ማንም ሳይሾመኝ ስእል አውቃለሁ ብዬ ገብቼ እንደ አማካሪ ሆኜ ያኔ የመረጥኳቸው ሠዓሊዎች አሁን በአለም የታወቁ አሉ። ...
" ከትቁር አሜሪካውያን ጋር በጣም በጣም ቅርብ ነበርኩኝ፤ በተለይ ከጃዝ ሙዚቀኞች ጋር። በብዛት የምሰማው ሙዚቃ የኢትዮፕያ ጃዝና ክላሲክ ሙዚቃ ነው። ከፈረንሣይ ፀሓፊዎች ጋርም ያለእድሜዬና ያለእውቀቴ እኩል ገብቼ ዋልኩኝ። በማንበብ ሳይሆን አብሮ በመዋል እንዳባቶች ሆነው አሳድገውኛል። ከፈረንሳይ፤ ከእንግሊዝ፤ ከአሜሪካን ፀሃፊዎች ወስጥ ሪቻርድ ራይት ለትንሽ አመለጠኝ ግን የእሱ ጓደኞች ከሚውሉበት ነበር የምውለው። እሱ እንደሞተ ነው ፓሪስ የደረስኩት። እንስተር ሃይምስ፥ ጀምስ ቦልድዊንና ስማቸውን ከማላስታውሳቸው ፀሐፊዎች ጋር አብሮ መዋል እኔጋም ፀሐፊ ያደረገኝ መስሎኝ ነበር። ያሳደጉኝ እነሱ እነጂ የፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲ አይደለም። በተጨማሪም ፓሪስ ከተማ አለች ከኢትዮዽያውያን ጓደኞቼ ጋር እየዋልኩኝ ወደ ሙዚየም፥ ቤተመጻሕፍት ፥ ቴአትር ቤት፥ ኮንሰርት እሄድ ነበር። ገንዘብ ብዙ አልነበረኝም። ከትሬንታ ላይ ሌሊት አትክልት እያወረድኩ ነበር የምኖረው። ግን አንድ ሳንቲም ኪሴ ሳይኖር እንደሚሊኒየር ልጅ ነው ፓሪስን የኖርኩባት። ከአዲስ አበባ ቀጥላ የትውልድ ከተማዬ የምትመስለኝ ፓሪስ ነች።"
ሰሎሞን ደሬሣ - ያኔ ነበር ከእውቁ ኢትዮዽያዊ ሠዓሊ እስክንድር በጎሲያን ጋር ፓሪስ የተገናኘው፤ ወዳጅነት የመሰረተው። እስክንድር አንዲት ጥቁር አሜሪካዊት አጭቶ ለሠርጉ ወደ አሜሪካ አላባማ ሲሄድ ሰሎሞን ሚዜው ነበር። የፈረንሣይ ትምህርቱን አቁዋርጦ አሜሪካ ገባ። ምናልባትም ከዚያን ጊዜ ወዲህ አውሮፓን ዳግመኛ አልረገጠም። ቢሆንም ፓሪስ ላይ በፈረንሣይኛ ግጥሞች ጽፏል፤ ጥቂቱም ታትመውለታል።
" ኪነጥበብ ለኪነጥበብነቱ " Art for Arts sake የሚለውን የጥበባት መርኄ ይከተላል የተባለው ሶሎሞን - በ1991 ዓ.ም " ዘበት እልፊቱ - ወለሎታት " የተሰኘች ሁለተኛ የግጥም መድበሉን በማበርከትም ለአማርኛ ዘመናዊ ሥነግጥም በተለይ የ" ነፃ ስንኝ "ወለሎ ስንኝ ወይንም የእንግሊዘኛውን Free Verse ዘዬ የመሰረተ በኩር ልጅ መሆኑን በተሰጥኦውና በብርታቱ አስመስክሯል። ነባሩን የኪነጥበብ አመለካከት ማኔላ ብቻ ሳይሆን አዲሱን የሥነግጥም አስተሳሰቡንም ገልጿል። " የወለሎ ውበቱ - የስሜቱ ግላዊነት፥ የስሜቱ ፍላት፥ የአገላለጹ ትባትና ብርቅዬነት፥ የአመጣጡ ድንገቴነትና የአጠፋፉ ቅፅበታዊነት ናቸው።" ሰሎሞን በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን አገር በሚኒያፖሊስ ይኖራል።
ምንጭ:
ብርሀነመስቀል ደጀኔ 2000ዓ.ም ብራና.ማ.ቤ ካሌንደር።
" ደራሲ ይደርሳል ፤ አንባቢ ያነባል ፤ ሃያሲ ይተቻል።
ሰሎሞን ተስፋ ማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሰይድ ኢብራሂም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሰይፉ ይነሡ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሰሎሞን ለማ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሰሎሞን ይርጋ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሰይፉ መታፈሪያ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሲሳይ ንጉሱ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አዲስ አበባ በ፲፱፶፩ ዓ.ም. የተወለዱት ሲሳይ ንጉሡ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በባልቻ አባነፍሶ፣ የሁለተኛ ደረጃን ደግሞ በአዲስ ከተማ አጠቃላይ ተከታትለዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ ከ፲፱፸፬-፲፱፸፯ ዓ.ም. ድረስ ተምረዋል።
በዩኒቨርሲቲ ሕይወት ዙሪያና በፍቅር ታሪክ ላይ በሚያተኩረው ሰመመን በሚባለው መጽፈሐፍቸው በብዙዎች ዘንድ የታወቁት ሲሳይ ንጉሡ፣ ጉዞው፣ ግርዶሽ፣ የቅናት ዛር የተባሉ ረጃጅም ልብወለዶች አሏቸው፡፡ ጉዞው የሚለውን ኖቬላ ጨምሮ ሌሎች አጫጭር ልብወለዶችን ጽፈዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ሥነ ጥበባትና መገናኛ ብዙኃን ሽልማት በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ ተሸላሚም ሆነዋል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት የደራሲያን ማኀበር ዋና ጸሐፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
አዲስ አበባ በ፲፱፶፩ ዓ.ም. የተወለዱት ሲሳይ ንጉሡ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በባልቻ አባነፍሶ፣ የሁለተኛ ደረጃን ደግሞ በአዲስ ከተማ አጠቃላይ ተከታትለዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ ከ፲፱፸፬-፲፱፸፯ ዓ.ም. ድረስ ተምረዋል።
[1903 - 1975]
ሲራክ ኅሩይ ወልደሥላሴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
የአባታቸውን የሥነ ጽሑፍ ሥራ በሥራ ላይ ያዋሉ፣ የአባታቸውን የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች በጥንቃቄ ይዘው የቆዩ፣ ከፊሎችን እንደገና ያሳተሙ ነበሩ፡፡ ከአለቃ ገብረሐና በኋላ እንደ ሲራክ ያሉ የሚያስቁ ቀልዶችን በሰፊው ያሠራጨና ያስተላለፈ ማንም ፀሐፊ የለም።
ሲራክ መጀመሪያ ግዕዝ ለመማር ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም ተላኩ፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ ከማሲዮኖች ት/ቤት ገቡ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለመማር ወደ ግብጽ አሌክሳንድርያ ኮሌጅ ሄዱ፡፡ ከኢጣሊያ ወረራ በኋላ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ እንግሊዝ ሀገር ተጓዙ፡፡ ሲራክ ፍልስፍና ለመማር ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ገቡ።
ዓፄ ኃይለሥላሴ በ1903 ዓ.ም. ከስደት ከተመለሱ በኋላ ሲራክ የሀገር ግዛት ሚኒስትር ፀሐፊ በመሆን ተሾሙ፡፡ ከዚያም ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተዛወሩ፡፡ በኋላም ወደ ሕንድ በአማካሪነት ተልከው አገለገሉ፡፡ በመንግሥት ሥራ ላይ እያገለገሉ ሳሉ ብዙ ሚኒስትሮች ስለሚቀበሉት ጉቦ፣ ሁኔታዎችን ማዘግየትና ማስተላለፍ ፖሊሲያቸውን አጥብቀው ይቃወሙ ነበር፡፡ ሲራክ እምቅ ዕውቀት እንዳላቸው ቢታወቅም ከንጉሱ ፖለቲከኞች ጋር ለመጫወት ያልፈለጉ ሀቀኛ ሰው ነበሩ፡፡ ንጉሡም ቢሆን ፖሊሲያቸውን እስካልለወጡ በሀገሪቱ አብዮት እንደሚነሳባቸው ነግረዋቸው ነበር፡፡ ያለአግባብ በሚፈጸሙ ጥፋቶች ላለመጠየቅ ከመንግሥት ሥራ ለቀው ወጡ፡፡
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከኢትዮጵያ ድንበር ውጭ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች እንግሊዝ ቆንስላ ውስጥ ከሚሠራና የእንግሊዝ የመረጃ አገልግሎት ሠራተኛ ከሆነ ሰው ጋር ተዋወቁ፡፡ በኋላም ወርሃዊ መጽሔት ያዘጋጅ ስለነበር ሲራክም አንዳንድ ጽሑፎችን በአማርኛ እየተረጎሙ ለማዘጋጀት ተቀጠሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ነበር በእንግሊዝ ቆንስላ ውስጥ በመረጃ አገልግሎት ቢሮ የሚሠራው ዎርዝ የተባለው ሰው ሲራክን የዶክተር ሳሙኤል ጆንሰንን “ራሴላስ” እንዲተረጉሙ አደረገ፡፡ ሲራክ ይህን መጽሐፍ “የአቢሲኒያው ልዑል” በማለት ተርጉመው አሳተሙ፡፡ እኝህ ሰው በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
የአባታቸውን የሥነ ጽሑፍ ሥራ በሥራ ላይ ያዋሉ፣ የአባታቸውን የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች በጥንቃቄ ይዘው የቆዩ፣ ከፊሎችን እንደገና ያሳተሙ ነበሩ፡፡ ከአለቃ ገብረሐና በኋላ እንደ ሲራክ ያሉ የሚያስቁ ቀልዶችን በሰፊው ያሠራጨና ያስተላለፈ ማንም ፀሐፊ የለም።
[1928 - 2004]
ስብሐትለአብ ገብረእግዚአብሔር
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ፋሺስት ኢጣሊያ ሀገራችንን በወረረበት 1927 ዓ.ም ገደማ ተፈጥረው የጥበቡን ከተማ በስራቸው ካስጌጡ ኢትዮዽያውያን መሃል አንዱ ደራሲ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ነው። ሚያዚያ 27/1928 አድዋ አውራጃ ርባ ገረድ ከምትባል ስፍራ ከአቶ ገብረ እግዚአብሔርና ወ/ሮ መዓዛ ተወልደመድህን ከተወለዱት 11 ልጆች 7ኛ ሆኖ የተወለደው ስብሐት አድጎ የአንድ የአጭር ልቦለዶች ስብስብና የሦስት መካከለኛ ልቦለዶች "አምስት ስድስት ሰባት"፣"ሌቱም አይነጋልኝ"፣"ትኩሳት"፣ "ሰባተኛው መልአክ" ደራሲ ብቻ ሳይሆን ከ30 ለበለጡ ዓመታት ጋዜጠኛም ነበሩ።
ጋዜጠኛው ስብሐት በ"አዲስ ዘመን" ጋዜጣ፣ "ሄራልድ" ጋዜጣ፣ "መነን" መጽሔት ፣ "Addis Reporter" ጋዜጣ፣ "የካቲት" መጽሔት፣ "ቁምነገር" መጽሔት፣ "ለዛ" መጽሔት፣ "አዲስ አድማስ" ጋዜጣ፣ "ሮዝ" መጽሔት ላይ ከአምደኛነት እስከ ዋና አዘጋጅነት መስራት ብቻ ሳይሆን በሚከተለው የአጻጻፍ ስልት የራሱን አንባቢያን መፍጠር ችሏል።
ስብሐት በተለይም ተፈጥሯዊነት ከሚጎላበት የአፃፃፍ ስልቱና ሕይወቱንም እንደሚጽፈው ለማኖር በሚያደርገው አኗኗር ደጋፊና ነቃፊ የፈጠረ አወዛጋቢ ሰው ነው። ይሁንና ስብሐት ገ/እግዚአብሄር ማንም ይደግፈውና ይንቀፈው ለማንም ይጣምና ይምረር የራሱን የሕይወት መንገድ አስምሮ በዚያ ላይ ሲጓዝ የነበረ ደራሲና ጋዜጠኛ ነው።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1952 ዓ.ም የባችለር ዲግሪውን ካገኘ በኋላ ለሁለት አመታት የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ሆኖ አገልግሏል። ምንም እንኳን ትምህርቱን ሳይጨርስ ቢመለስም ለከፍተኛ ትምህርት አሜሪካና ፈረንሳይ ሄዷል። ፈረንሳይ ትምህርቱን ባታስጨርሰውም "ትኩሳት"ንና "ሠባተኛው መልአክ"ን ሰጥታዋለች። ሆነም ቀረ ስብሐት በተለይም እሱ የህይወቱ ተልእኮ አድርጎ በያዘው ሥነ ጽሁፍ በየትም ደረጃ የተማረ ሰው ሊያበረክተው ከቢገባው በላይ ከፍ ያለውን ድርሻ ተወጥቷል ማለት ይቻላል። እንደ አፃፃፉ ሁሉ በአኗኗሩም ሕይወትን ከነብጉሯ መግለጽ ይወዳል። ስብሐትን ባህል፣ ይሉኝታና የሌሎች አስተሳሰብ ሳይሆን ህይወት ሊያውም የራሱን ህይወት ናት የምትመራው።ስለዚህም ይሆናል 70 ዓመት እድሜን ከዘለለ በኋላ ከአንዲት ወጣት ብን ያለ ፍቅር ውስጥ የገባው "እናም ተመቻችተናል" ያለው።
ምንጭ:
"አዲስ ጉዳይ" መጽሔት ቅጽ 6 ቁጥር 129 ዿጉሜን 2004 ዓ.ም ልዩ እትም።
ፋሺስት ኢጣሊያ ሀገራችንን በወረረበት 1927 ዓ.ም ገደማ ተፈጥረው የጥበቡን ከተማ በስራቸው ካስጌጡ ኢትዮዽያውያን መሃል አንዱ ደራሲ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ነው።
ስብሐት ለአብ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት የሥነ ጽሑፍ ሰው እንደሆኑ ይነገራል፡፡ በርካታ ጽሑፎችን በመጻፍ የሚታወቁት ወ/ሮ ስንዱ የተወለዱት ጥር 6 ቀን በ1908 ዓ.ም. ነበር።
እኒህ የብዕር ሰው ጀርመን ሀገር በመሄድ ተምረዋል፡፡ በወ/ሮ ስሂን ትምህርት ቤት አስተምረዋል፡፡ ወ/ሮ ስንዱ ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በሀገር ፍቅር ስሜት በመነሣሣት በርካታ ስሜት ቀስቃሽ ግጥሞችን ጽፈዋል፡፡ “የኢትዮጵያ ትግል፣ አድዋ፣ አፄ ቴዎድሮስ፣ የታጋዮች ስሜት ከግራዚያኒ ንግግር በኋላ፣ ኮከብህ ያውና ያበራል ገና፣ የየካቲት ቀኞች፣ ከማይጨው መልስ፣ የልቤ መጽሐፍ የታደለች ሕልም” የሚሉት ሥራዎቻቸው የገጣሚዋን የሀገር ፍቅር ስሜትና የሥነ ጽሑፍ ችሎታ የሚያሳዩ ናቸው፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሴት የሥነ ጽሑፍ ሰው እንደሆኑ ይነገራል፡፡ በርካታ ጽሑፎችን በመጻፍ የሚታወቁት ወ/ሮ ስንዱ የተወለዱት ጥር 6 ቀን በ1908 ዓ.ም. ነበር።
ሶስና አሸናፊ ረጋሣ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሶስና አሸናፊ ነሐሴ ፲፩ ቀን ፲፱፷፭ ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍሪካ አንድነት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመድኃኔዓለም ትምህርት ቤቶች ተከታትለዋል። ከእንጦጦ የቴክኒክና ሙያ ት/ቤት በጸሐፊነት ሙያ ተመርቀዋል፡፡ “ከራስ ሽሽት”፣ የተሰኘ ሥራ ያቀረቡ ሲሆን፣ “ዕጣ”፣ “የሕይወት ጠብታዎች”፣ “ክንፋም ሕልሞች”፣ “ያልተናበቡ ልቦች”፣ በተሰኙ መድብሎች ውስጥ ከሌሎች ደራስያን ጋር ጽሑፎቻቸውን አሳትመዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ሶስና አሸናፊ ነሐሴ ፲፩ ቀን ፲፱፷፭ ዓ.ም. አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍሪካ አንድነት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመድኃኔዓለም ትምህርት ቤቶች ተከታትለዋል።
መጻሕፍት ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ
ይጫኑ
ተመዝግበው ከሆነ እዚህ
ይጫኑ
[
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ቋንቋ
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
]
[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com