[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
የኢትዮጵያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
አ
በ
ቨ
ገ
ደ
ጀ
ሀ
ወ
ዘ
ዠ
ሐ
ኀ
ጠ
ጨ
የ
ከ
ኸ
ለ
መ
ነ
ኘ
ሠ
ዐ
ፈ
ጸ
ፀ
ቀ
ረ
ሰ
ሸ
ተ
ቸ
ጰ
ፐ
ወደ ዋና ገጽ
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መብዐጽዮን ዐምዱ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መስፍን ኃይሉ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መንበረ ወልዴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መሰንቆ ድንግል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መሐመድ ይማም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መሠረት ስብሐት ለአብ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1920 - 1988]
መንግስቱ ገዳሙ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መንግሥቱ ገዳሙ በሲዳሞ ክፍለሀገር ተወልደው ከብት ሲጠብቁ ያደጉ የባላገር ልጅ ናቸው፡፡ በልጅነታቸው እባብ ነድፎዋቸው ለስድስት ሳምንታት ኀሊናቸውን ስተው ከሰነበቱ በኋላ ከሞት ተርፈዋል፡፡ ዕድሜያቸው ከፍ ሲል በወታደርነት ተቀጥረው ሠርተዋል።
ከወታደር ዓለም ወጥተው ፖስታ፣ ቴሌፎንና ቴሌግራፍ ሚኒስቴር ውስጥ ተቀጠሩ፡፡ በሥራቸው ጎበዝ ስለነበሩ በዕድገት ወደ ድሬደዋ ተዛወሩ፡፡ ባሕል አስከብራለሁ እያሉ በርኖስ እየለበሱ ቢሮ በመገባታቸው የሚታወቁት መንግሥቱ ገዳሙ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ከገቡ በኋላ “ሞገደኛ ጋዜጠኛ” የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በጋዜጣ የጀመሩት ጽሑፍ ደራሲ እንዲሆኑ ስለገፋፋቸው ሳይሆን አይቀርም ብዙ “ቤሳ” መጻሕፍት ጽፈዋል፡፡ የጻፉትን መጻሕፍ ይዘት ባብዛኛው አያስታውሱም፡፡ ካሳተሟቸው መጻሕፍት መካከል “ሶማሌው” በ፲፱፶፯ ዓ.ም. “መሰላል” በ፲፱፶፱ ዓ.ም. እና “አሳማና ድመት” በ፲፱፶፱ ዓ.ም. ተጠቃሾች ሲሆኑ ሌሎች ኢ ልብወለድ መጻሕፍትም በተለያዩ ጊዜዎች አሳትመዋል፡፡
የመንግሥቱ ገዳሙ ባህርይ አፈንጋጭ የሚሉት ዓይነት ነው፡፡ ሞገደኛው ጋዜጠኛ መንግሥቱ በተወለዱ በ48 ዓመታቸው ሐምሌ 18 ቀን በ፲፱፷፰ ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
መንግሥቱ ገዳሙ በሲዳሞ ክፍለሀገር ተወልደው ከብት ሲጠብቁ ያደጉ የባላገር ልጅ ናቸው፡፡ በልጅነታቸው እባብ ነድፎዋቸው ለስድስት ሳምንታት ኀሊናቸውን ስተው ከሰነበቱ በኋላ ከሞት ተርፈዋል፡፡ ዕድሜያቸው ከፍ ሲል በወታደርነት ተቀጥረው ሠርተዋል።
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
በበጎ ስራቸው "ኢትዮዽያዊው ዮሴፍ" የሚል ቅጽል ስም ያተረፉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተወለዱ። በልጅነታቸው የቤተክርስትያን ትምህርት በመከታተል ድቁናን ተቀብለዋል። በተፈሪ መኮንን የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለው በ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. በጥሩ ውጤት በማጠናቀቅ በጊዜው የላቀ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሚሰጠውን የውጪ አገር የትምህርት እድል አሸንፈው ወደ ህንድ አገር በመሄድ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከፑንጃብ[Punjab] ዩኒቨርሲቲ በ፲፱፻፵፭ ዓ.ም. እንዲሁም አሜሪካን አገር ከሚገኘው ክላርክ [Clark] ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዴግሪያቸውን በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. ተቀብለዋል።
መስፍን የውጪ አገር ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ወደሀገራቸው ከተመለሱ በሗላ በቀድሞው "ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ" ያሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ፲፬ አመታት ከ፲፱፻፶፩ እስከ ፲፱፻፷፭ ዓ.ም በመምህርነት እንዲሁም የጂኦግራፊ ትምህርት ክፍል ዋና ሀላፊ በመሆን ሠርተዋል። በ፲፱፻፸ዎቹ መጀመሪያ በድጋሚ ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሰው ለረጅም አመታት በጡረታ እስከተገለሉበት ጊዜ ድረስ በዩኒቨርሲቲው በመምህርነት አገልግለዋል።
በረዥም ጊዜ የአካዳሚክ ህይወታቸው በርከት ያሉ ጥናታዊ ጽሑፎችን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ጦማር/መጻሕፍት አሳትመዋል ጂኦግራፊ፣ኢኮኖሚ፣ታሪክ፣ፖለቲካ፣ ድርቅና ረሀብ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥበቃን በተመለከተ ምሁራዊ ሃሳባቸውን በመጽሐፎቻቸው እንዲሁም በየግዜው በተለያዩ መጽሔት እና ጋዜጦች ላይ በሚጽፏቸው መጣጥፎች ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር በተጋባዥነት በተሳተፉባቸው በተለያዩ አለምአቀፍ ጉባኤዎች ኢትዮዽያን በተመለከተ ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሁፎችን በማቅረብ ያላቸውን ፍልስፍና፣ ሃሳብና፣ አመለካከት በሰፊው አካፍለዋል።
ፕሮፌሰር የስነግጥም ተሰጥኦም እንዳላቸው በ፲፱፻፷፯ ዓ.ም ያሳተሙት ከ፴ በላይ ግጥሞችን ያካተተችው "እንጉርጉሮ" የተሰኘችው የግጥም መድብል ምስክር ሆናለች። እንጉርጉሮ የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮችን ተከትሎ በጊዜው ያቆጠቆጠውን የሞራል ውድቀት እያነሳች የአንባቢን ህሊና አጣብቂኝ ውስጥ ከታ ትኮረኩራለች።
ከብዙ በጥቂቱ ፕሮፌሰር መስፍን በእንግሊዘኛ ካሳተሞቸው መጻሕፍት The horn of Africa : conflict and poverty 1999, Somalia : the problem child of Africa 1977, Suffering under Gods environment 1991 ይጠቀሳሉ በአማርኛ "አገቱኒ ተምረን ወጣን"፣ "ሥልጣን ባህልና አገዛዝ ፖለቲካና ምርጫ"፣ እንዲሁም በቅርቡ ያሳተሙት "አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ"፣ ይገኙባቸዋል።
ፕሮፌሰርን ከሌሎች ኢትዮዽያውያን ምሁራን ልዩ የሚያደርጋቸው አስቸጋሪ ጊዜዎችን ሁሉ በመቋቋም ከሀገራቸው ሳይወጡ እድሜያቸውን ሙሉ ያላቸውን እውቀት፣ሀሳብና ምክር ለማካፈል አለመሰልቸታቸው ነው። በአሁኑም ወቅት በአዲሱ ትውልድ ጭምር ተወዳጅና አራያነታቸው ቀጥሏል። ከፍተኛ ተሰሚነት ካላቸው ኢትዮዽያ በ፷ አመት ውስት ካፈራቻቸው ምሁራን ውስጥ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይይዛሉ።
በበጎ ስራቸው "ኢትዮዽያዊው ዮሴፍ" የሚል ቅጽል ስም ያተረፉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተወለዱ።
ም/መቶ አለቃ መለሰልኝ አንለይ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መላኩ ደስታ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሊቀ ሊቃውንት መሐሪ ተረፈ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መስፍን ልሳኑ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መሸሻ ግዛው
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ወይዘሮ መቅደሰ ወርቅ ዘለቀ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መንግስቱ መኮንን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1916 - 1980]
መንግስቱ ለማ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
"ደማሙ ብእረኛ "
መንግስቱ ለማ ቀደምት የኢትዮዽያ ሊቃውንት ከነበሩት ከአለቃ ለማ ኃይሉ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ አልማዝ ይልማ ሰኔ 1 ቀን 1916 ዓ.ም ሐረር አደሬ ጢቆ በተባለ አካባቢ ተወለዱ።
መንግስቱ ገና በልጅነት ዕድሜያቸው በሊቁ አባታቸው እና በወቅቱ መምህራን ባህላዊውን የቤተ ክህነት ትምህርት ከዜማ እስከ ጾመ ድጓ እና የግዕዝ ቅኔን ጠንቅቀው "የልጅ ሊቅ" ተባሉ።
በኢጣሊያ ወረራ ወቅት 1929 -1933 በጣሊያን አገዛዝ ሥርዓት ትምህርት በ"ፓጃላ" ሦስት ዓመት፥ ከነፃነት በኋላም በአንድ ዓመት ተኩል እድሜ ውሰጥ 1934 - 1935 በሚሲዮናዊው ሙሴ እንቶን ጆነስ ትቤት እስከ አራተኛ ክፍል ዘመናዊውን ትምህርት አጠናቀዋል።
መንግስቱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለመከታተል በ1936 ዓ.ም. አዲስ አበባ መጡ። እስከ 1939 ዓ.ም. በኮተቤ ቀ.ኃ. ሥላሴ ት/ቤት ተከታተሉ።
በ1940 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ዕድል በማግኘት ወደ እንግሊዝ ሀገር የሄዱት መንግስቱ፥ በለንደን ለአንድ ዓመት በ"ሬጀንት ስትሪት ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ"፥ ቀጥሎም በእውቁ "ለንደን ስኩል ኦፍ ኤኮኖሚክስ" የሥነምጣኔ ትምህርታቸውን ተከታተትለዋል። መንግስቱ ምንም እንኳን ኋላ ጥናታቸውን ሳያጠናቅቁ በ1946 ዓ.ም. ወደ ሀገራቸው ቢመለሱም፥ በለንደን ቆይታቸው በ1941 ዓ.ም "በብሪታኒያ የኢትዮዽያ ተማሪዎች ማህበረሰብ"ን የመሰረቱ ንቁ የለውጥ መሪ ነበሩ፥ ማህበሩን በዋና ፀሐፊነት እና በፕሬዚዳንትነት የመሩ።
የሐዲስ ሐሳብና የለውጥ ልሳን የነበረውን የማህበሩን መጽሔት "እጓለ አንበሳ"
LION CUB
በመመሥረት ወጣት ኢትዮዽያውያን ምሁራን የለውጥ ሐዋርያዊ ተልእኮአቸውን በምን መልኩ መወጣት እንዳለባቸው በገናን ብእራቸው
The best system of Ideas
ድምፃቸውን ያሰሙ ፍቁረ ኢትዮዽያ ከነበሩት እውቅ እንግሊዛዊቷ ኢትዮዽያዊት ሲልቪያ ፓንክረስትን ከልጃቸው ከሪቻርድ ፓንክረስት ጋር ወዳጅነት የመሰረቱ፥ ይበልጡን ጊዜያቸውንም ታላላቆቹ የሳይንሳዊ ሶሻሊዝም ፈላስፎች ሥራዎች እና የቴአትር ድርሰት "በሰሎች"ን የእነበርናንድ ሾው፥ ኢብሰንን። ስትራገድበርግን፥ ጋል ስዌርቷን ወዘተ... የመሳሰሉ ፀሐፊ ተውኔት ሥራዎች በስፋትና በጥልቀት ያነበቡ፥ የተመራመሩ ነበሩ።
ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ በሲቪል አቪዬሽን 1940 -1950 በኃላፊነት፥ በሕንድ የኢትዮዽያ አምባሳደርነት 1950 -1955 እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በምርምር ማእከል ኃላፊነት 1955 -1962 ያገለገሉት መንግስቱ፥ በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ግዜ በተቋቋመው የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር "የብሔራዊ ቋንቋ መርሐ ልሣን" መሥራች እና ዋና ፀሐፊ 1962 -1967 ፥ የ"ብሔራዊ ቋንቋ አካዳሚ " ዋና ፀሐፊ 1967 -1971 በመሆን፥ ከ1971 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዕለት ሞታቸው በአ.አ ዩኒቨርሲቲ በቴአትር መምህርነት በማገልገል በአጠቃላይ - በኢትዮዽያ ዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ እድገት በአማርኛ ሥነ ግጥም ቅኔ እና በቴአትር ድርሰት "ተዋነይ"ነት በተመራማሪነት እና በመምህርነት ----- ግምባር ቀደም ሆነው ----- በነበሩ ኢትዮዽያዊ ባህልና በ"ውጪው"ዓለም አዳዲስ ሐሳብ "ተዋህዶ" ሥርዓት የኢትዮዽያን የሥነ ፅሑፍ ህዋ በብዕር ቀለም አድምቀውታል፤ አዳዲስ የቴአትር ጥበባት ባለሙያዎች አፍርተዋል።
መንግስቱ ለማ "የግጥም ጉባኤ" 1950፥ "ያባቶች ጨዋታ" 1953፥ "ባሻ አሸብር ባሜሪካ 1967" በተሰኙት የሥነ ግጥም ሥራዎቻቸው ለአማርኛ ሥነ ጽሑፍ አዳዲስ የግጥም ስልትና ዘይቤ የመሰረቱ፥ "ያላቻ ጋብቻ" 1956 እና "ጠልፎ በኪሴ" 1961 በተሰኙት ተውኔቶቻቸው ደግሞ "ለኢትዮዽያ ኮሜዲ ቴአትር በር ከፋች" "ኮሜዲያችን ዘመናዊ መልክ እንዲጎናፀፍ ያደረጉ የመጀመሪያው ኢትዮዽያዊ" የሚል ልዩ አክብሮት ያገኙ የሥነ ፅሑፍ ሰው ናቸው።
በኢትዮዽያ ሥነ ጥበባት አምባ "ደማሙ ብዕረኛ" የሚል ልዩ ስያሜ ስላገኙት እኚህ የዕደ ጥበብ ባለሙያ፥ ሠዓሊ፥ ባለቅኔ፥ ፀሐፌ ተውኔት መምህር እና ተመራማሪ የቀለም ሰው ቶማስ ኬን፥ ኡላን ዶርፍ፥ ሬዱልፍ ሞልቫር፥ ሪቻርድ ፓንክረስትና ወዘተ...የመሳሰሉ እውቅ የውጪ ፀሐፍት ታሪካቸውን በአድናቆት የዘከሩ ሲሆን፥ ዛሬም ድረስ እየተዘከሩ ነው።
በጠቅላላ መንፈሳቸው "የጥንታዊቷና የአዲሲቱ ኢትዮዽያ መገናኛ አንድ ድልድይ" እንደነበሩ የተመሰከረላቸው፥ በ1961 ዓ.ም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የስነ ጽሑፍ ሽልማት ተሸላሚ፥ በ1962 ዓ.ም ከካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ሥነ ጽሑፍ ተሸላሚ የነበሩት መንግስቱ ለማ ሐምሌ 21 ቀን 1980 ዓ.ም. አረፉ።
"ደማሙ ብእረኛ "
መንግስቱ ለማ ቀደምት የኢትዮዽያ ሊቃውንት ከነበሩት ከአለቃ ለማ ኃይሉ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ አልማዝ ይልማ ሰኔ 1 ቀን 1916 ዓ.ም ሐረር አደሬ ጢቆ በተባለ አካባቢ ተወለዱ።
መክብብ ደስታ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መኮንን አበበ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መኮንን ወርቅ አገኘሁ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መዝገቡ አባተ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1891 - 1971]
ብላታ መርስዔ ሐዘን ወልደ ቂርቆስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መርስዔ ኀዘን ወልደቂርቆስ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጅሩ ቆላ ውስጥ እምባጮ መግደላዊት በሚባል አካባቢ በ፲፰፻፺፩ ዓ.ም. ተወለዱ። ትምህርት የጀመሩት በልጅነታቸው ሲሆን በጊዜው ዳዊት ደግመዋል፡፡ ከዚያም የዜማ ትምህርት በመጀመር ጾመ ድጓና ድጓ አስኪደዋል፡፡ ቀጥሎም ቅኔ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ ፲፱፻፭ ዓ.ም. የመጀመሪያ ሥራቸውን የወንበር ፀሐፊ በመሆን እየሠሩ አገልግለዋል፡፡ የመጻሕፍተ ሐዲሳትን፣ የዮሐንስ አፈወርቅን ትርጓሜ፣ እንዲሁም የመቅድመ ወንጌልን ትርጓሜ ትምህትን አጠናቀዋል፡፡ እኝህ ታላቅ ሰው ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ሲመሠረት የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ፣ ቀጥለውም የተፈሪ መኮንን ት/ቤት የግዕዝና የአማርኛ አስተማሪ በመሆን ሠርተዋል፡፡ እንዲሁም ከ፲፱፴፫ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ፲፱፷፫ ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በልዩ ልዩ ኃላፊነቶችና በዲሬክተር ማዕረግ ሠርተዋል፡፡ ሥነ ጽሑፍንና ታሪክን በተመለከተ አሥራ ሦስት መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡ ሰባት መጻሕፍትን ተርጉመዋል፡፡ የተለያዩ ጽሑፎችን አሰባስበው አዘጋጅተዋል፡፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ሥራዎችን ከሊቃውንት ጋር በመሆን አዘጋጅተዋል፡፡ የአማርኛ ስዋስው መጽሐፍ ባለመዘጋጀቱ ተማሪዎች ተገቢውን የቋንቋ ትምህርት ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን በማየትም በ፲፱፴፭ ዓ.ም. “የአማርኛ ስዋስው” የተባለ መጽሐፍ አዘጋጅተው በማቅረብ ችግሩ እንዲቃለል አድርገዋል። መርስዔ ኀዘን በላቀ የሥነ ጽሑፍ ሥራቸው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሽልማት ድርጅት ተሸላሚ ናቸው፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
መርስዔ ኀዘን ወልደቂርቆስ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጅሩ ቆላ ውስጥ እምባጮ መግደላዊት በሚባል አካባቢ በ፲፰፻፺፩ ዓ.ም. ተወለዱ።
መሐሪ ትርፌ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መንክር መኮንን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መላኩ በጎሰው
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መላከ ኃይሉ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መላኩ አሻግሬ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መስፍን ሀብተማርያም ሞገስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መስፍን ሀ/ማርያም የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፴፮ ዓ.ም. በምሥራቅ ሸዋ ሞጆ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞጆ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃን በአንቦ ማዕርገ ሕይወት ት/ቤት አጠናቅቀዋል። የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአ.አ. ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ በቢ.ኤ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ በተጨማሪም ከብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ካናዳ በፈጠራ ድርሰቶች አጻጻፍ ኤም.ኤ. ዲግሪ ኤም.ኤፍ.ኤ ተቀብለዋል፡፡
“የቡና ቤት ሥዕሎችና ሌሎች ወጎች”፣ “ዓውዳመት”፣ “አዜብና ሌሎችም አጫጭር ልቦለዶች”፣ “የሌሊት ድምጾች” የሚሉ ልቦለድ ሥራዎችንና የወግ ጽሑፎችን ለንባብ አብቅተዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
መስፍን ሀ/ማርያም የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፴፮ ዓ.ም. በምሥራቅ ሸዋ ሞጆ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞጆ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃን በአንቦ ማዕርገ ሕይወት ት/ቤት አጠናቅቀዋል።
መርስዔ ሐዘን አበበ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መኮንን ዘውዴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መኮንን በሪ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መስፍን ዓለማየሁ ጠይቃቸው
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መስፍን ዓለማየሁ በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ጅጅጋ ከተማ መስከረም ፳፮ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ09#9 ዓ.ም.፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ09%1 ዓ.ም. አጠናቀቁ።
መስፍን ዓለማየሁ “የቴዎድሮስ ዕንባ”፣ “የቬኑሱ ነጋዴ”፣ የተሰኙ ተውኔቶችን “የሽዋስቲካ ምሥጢር”፣ “ካፖርቱ”፣“የመጨረሻዋ ቅጠል”፣ “ሽማግሌውና ባሕሩ”፣ በመባል የሚታወቁ ልቦለድ የትርጉም መጻሕፍት አሳትመው ለአንባብያን አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ግጥሞች፣ አጫጭር ልቦለዶች፣ በጋዜጦች፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ለሕዝብ አቅርበዋል፡፡
መስፍን ዓለማየሁ በሕይወት ዘመናቸው በቀድሞዋ ሶቪየት ኀብረት በሞስኮ 12ኛው የወጣቶች ፌስቲቫል በተከበረበት ወቅት በሶቭየት ደራስያን ማኀበር አዳራሽ በተካሄዱ የሥነ ጽሑፍ - ጉባኤዎች ላይ ማኀበራችንን ወክለው ተገኝተዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
መስፍን ዓለማየሁ በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ጅጅጋ ከተማ መስከረም ፳፮ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ09#9 ዓ.ም.፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ09%1 ዓ.ም. አጠናቀቁ።
መሃባ ጀማል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1883 - 1953]
ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው በሰሜን ሸዋ በተጉለት አውራጃ አዲስጌ በምትባል ቦታ በ በ1983 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በዳግማዊ ምኒልክ፣ በንግሥት ዘውዲቱ እና በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥታት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሀገራቸውን አገልግለዋል።
በሕይወት ዘመናቸው ከ2ዐ በላይ መጻሕፍት በመድረስ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ዕድገት የጎላ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ከሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸው ውስጥ የታተመው “አርሙኝ” የተባለው መጽሐፋቸው በብዙዎች ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ የሕይወት ታሪካቸውን ባጭሩ፣ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት የጻፏሕውን ድርሰቶችን ስለማይጮው ጦርነትና የዓለም ፖለቲካ በማካተት የጻፉት ነው፡፡ “የድሆች ከተማ” በ1933፣ “ሐሳብና ሰው” በ1933፣ “ሣልሳዊ ዳዊት” በ1933 “የፍቅር ጮራ” በ1939፣ ከጻፏቸው መጽሐፍት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው በሰሜን ሸዋ በተጉለት አውራጃ አዲስጌ በምትባል ቦታ በ በ1983 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በዳግማዊ ምኒልክ፣ በንግሥት ዘውዲቱ እና በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥታት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሀገራቸውን አገልግለዋል።
መኮንን ገብረእግዚ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መኮንን ገብረእግዚ የልቦለድ ደራሲ ነው፡፡ የተወለደው በአዲስ አበባ ሲሆን ዛሬ በስቶኮልም ስዊድን ይኖራል። ሁለት መፅሀፎቹ ዘመነ ደርግን መቸት አድርገው የተከሸኑ ናቸው።
ምንጭ:
ዊኪፒዲያ
መኮንን ገብረእግዚ የልቦለድ ደራሲ ነው፡፡ የተወለደው በአዲስ አበባ ሲሆን ዛሬ በስቶኮልም ስዊድን ይኖራል።
ዲ/ን መልአኩ አስማማው
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዲባቶ መስፍን አረጋ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዲባቶ
ዲባቶ።
ሙሉ ሰው ምትኩ አዣዥ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዶ/ር ሙራድ ካሚል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሙሐመድ ታጁቲን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሙሉጌታ ጉደታ አድማሱ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሙሉጌታ ጉደታ መስከረም ፳፫ ቀን ፲፱፵፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመድኃኔዓለም ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሊሴ ገ/ማርያም ተምረዋል። የከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በአ.አ. ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት በዲግሪ ተመርቀዋል፡፡
ሙሉጌታ ጉደታ “የአራዳ ልጆች”፣ “የተቀጠፈች ጽጌረዳ”፣ “የዕንባ ጠብታዎች”፣ “የተከፋፈለ ልብ”፣ “ጭምብል”፣ “ሰውና እስስት”፣ “ሞገደኛው”፣ “ሕልመኛው”፣ “ስደተኛው ፍቅር”፣ የተባሉ መተሕፍትን በአማርኛ፤ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ደግሞ “The Chillren of Poverty” የተሰኙ ልቦለዶችን አሳትመው ለንባብ አብቅተዋል፡፡ ከዚህ ተጨማሪም የእንግሊዝኛ/ አማርኛ መዝገበ ቃላት፣ የአማርኛ ዘይቤዎች መዝገበ ቃላት፣ የእንግሊዝኛ/ ፈረንሳይኛ ቋንቋ መማሪያ፣ ተግባራዊ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ፣ በሚሉ ርዕሶች የተዘጋጁ መጻሕፍትን አሳትመዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ሙሉጌታ ጉደታ መስከረም ፳፫ ቀን ፲፱፵፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመድኃኔዓለም ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሊሴ ገ/ማርያም ተምረዋል።
አባ ሚካኤል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አባ ሚናስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሚሊዮን ነቅንቅ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1912 - 1966]
ማህተመሥላሴ ወልደመስቀል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
የፈረንሳይ አገር የግብርና ተማሪ የነበሩት ብላቴን ማኀተመ ሥላሴ ለልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን ጸሐፊና የእርሻ ሚኒስቴር ምክትል ዋና ሚኒስትር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሕዝብ አገልግሎት ሚኒስቴርና የዘውድ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል። በታሪክ ፊት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውና አጠቃላዩን የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበዊና ፖለቲካዊ ገጽታ የሚዘክረውን “ዝክረ ነገር መጽሐፍ” በ1942 ዓ.ም. ለኀትመት አብቅተዋል፡፡
በተጨማሪም “የአባቶች ቅርስ” በ1943 ዓ.ም.፣ “አማርኛ ቅኔ ነጠላ” በ1948 ዓ.ም.፣ “እንቅልፍ ለምኔ” በ1950 ዓ.ም.፣ “ያገር ባህል” በ1960 ዓ.ም.፣ “ባለን እንወቅበት” በ1961 ዓ.ም. እና ሌሎች መጽሐፍት አሳትመዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ ።
የፈረንሳይ አገር የግብርና ተማሪ የነበሩት ብላቴን ማኀተመ ሥላሴ ለልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን ጸሐፊና የእርሻ ሚኒስቴር ምክትል ዋና ሚኒስትር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሕዝብ አገልግሎት ሚኒስቴርና የዘውድ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል።
ማርቆስ ዳውድ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ማቴዎስ በቀለ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1928 - 2004]
ማሞ ውድነህ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ማሞ ውድነህ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. በቀድሞ አጠራር በወሎ ክፍለ ሀገር በዋግ አውራጃ በዳህና ወረዳ አምደወርቅ ከተማ ተወለዱ፡፡ በቤተክህነት ትምህርት ዳዊት እስከመድገም ደርሰዋል፡፡ ከ፲፱፵ ዓ.ም. ጀምሮ በደሴ በንጉሥ ሚካኤል ትምህርት ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ትምህርት ቤቶች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተምረዋል፡፡
በመጀመሪያ በመምህርነት ቀጥሎም በውጭ ሀገር ኤምባሲዎች ሠርተዋል፡፡ በማስታወቂያ ሚኒስቴር በፖሊስ ሠራዊትና በቀድሞ ኤርትራ ክፍለ ሀገር በፕሬስ የሥራ ክፍሎች ውስጥ ሠርተዋል፡፡ ከ፲፱፹፭ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ፲፱፺፯ ዓ.ም. ድረስ የደራስያን ማህበርን በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል፡፡ ልብ ወለድ፣ አጫጭር ድርሰት፣ ግጥምና ቅኔ፣ የቲያትር መጻሕፍትን በመድረስና በመተርጎም ይታወቃሉ፡፡ ካሳተሟቸው 5ዐ ያህል መጻሕፍት መካከል ሁለተኛው የዓለም ጦርነት፣ የሴቷን ፈተና፣ ከወንጀለኞች አንዱ፣ ቬኒት ሙሶሎኒ፣ ዘጠና ደቂቃ በኢንተቤ እና ዕቁብተኞቹ ይገኛሉ፡፡ በቅርቡም "የደረስኩበት" በሚል ርዕስ ግለ ታሪካቸውን የተመለከተ 5ዐኛው መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጽ አሳትመዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ማሞ ውድነህ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. በቀድሞ አጠራር በወሎ ክፍለ ሀገር በዋግ አውራጃ በዳህና ወረዳ አምደወርቅ ከተማ ተወለዱ፡፡ በቤተክህነት ትምህርት ዳዊት እስከመድገም ደርሰዋል፡፡ ከ፲፱፵ ዓ.ም. ጀምሮ በደሴ በንጉሥ ሚካኤል ትምህርት ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ማሞ ለማ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሜሪ ጃዕፋር ሰይድ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሜሪ ጃዕፋር በቀድሞው ኢሊባቡር ጠ/ግዛት ጎሬ ከተማ ጥቅምት ፭ ቀን ፲፱፵፰ ዓ.ም. ተወለዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአቡነ ሚካኤል ት/ቤት ጎሬ፣ የሁለተኛ ደረጃን በቀዳማዊ ኃ.ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ጎሬ፣ አሥመራና ተፈሪ መኮንነ አጠቃላይ ት/ቤት አ.አ. አጠናቅቀዋል፡፡ ከአ.አ. ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡
ሜሪ ጃዕፋር ከ11 በላይ የሕጻናት መጻሕፍት፤ ከስድስት በላይ ሥዕላዊ መግለጫ ያላቸውን መጻሕፍትን ያሳተሙ ሲሆን ካቀረቧቸው የሕጻናት መጻሕፍት መካከል፣ “የፋጡማ ሕልም”፣ “ከወንጪ መልስ”፣ “ኢልሞሌ ይመለስ ይሆን?”፣ “ቦላቦ” “ሚጢ ሚጢጢ”፣ “ሰላሜ”፣ “የጦጢት መላ” ወዘተ… ይገኙባቸዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ሜሪ ጃዕፋር በቀድሞው ኢሊባቡር ጠ/ግዛት ጎሬ ከተማ ጥቅምት ፭ ቀን ፲፱፵፰ ዓ.ም. ተወለዱ።
ምናሴ የሥጋት
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ምክረ ሥላሴ ገብረ አማኑኤል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሞገስ እቁባጊዮርጊስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሞገስ ክፍሌ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መጻሕፍት ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ
ይጫኑ
ተመዝግበው ከሆነ እዚህ
ይጫኑ
[
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ቋንቋ
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
]
[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com