[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
የኢትዮጵያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
አ
በ
ቨ
ገ
ደ
ጀ
ሀ
ወ
ዘ
ዠ
ሐ
ኀ
ጠ
ጨ
የ
ከ
ኸ
ለ
መ
ነ
ኘ
ሠ
ዐ
ፈ
ጸ
ፀ
ቀ
ረ
ሰ
ሸ
ተ
ቸ
ጰ
ፐ
ወደ ዋና ገጽ
ተክለማርያም ኃይሌ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ አለነ አባተ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1876 - 1969]
ተክለሐዋርያት ተክለማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
በ1876 ዓ.ም በሰኔ ወር በሳያድብር ተወለዱ፡፡ ፊታውራሪ ተክለሃዋርያት በልጅነታቸው በወንድማቸው አማካኝነት ከሸዋ ወደ ሐረር ጠቅላይ ግዛት ተጉዘው እራስ መኮንን ቤት አደጉ፡፡ በልጅነታቸው አልቀርም በማለት 50 ጥይት ጎራሽ ጠመንዣ ታጥቀው ወደ አድዋ ዘመቱ። ከጦርነቱ መልስ እራስ መኮንን ቃል በማስገባት አጼ ሚኒሊክ እንዲፈቅዱላቸው በማድረግ ወደ ሩሲያ ሄደው ትምህርት ቤት ገቡ። በሩሲያ ተልኳቸው ዘመናዊ የጦር ትምህርት ለአራት አመታት ተከታትለዋል።
ከሩሲያ መልስ መጀመሪያ የልጅ እያሱ አማካሪ በሇላም የአፄ ኃይለሥላሴ አማካሪ በመሆን በተለያየ የስልጣን እርከን በመሾም አገራቸውን አገልግለዋል። ከአገልግሎታቸው ውስጥ የከተማ ህግ ማርቀቅ፣ ዘመናዊ እርሻን ማስተዋወቅ፣ ከተማ መመስረትን ይገኝበታል። በተለይ ፊታውራሪ አፄ ሚኒሊክ ማረፋቸው ከተገለፀ በሇላ በልጅ እያሱና በአፄ ኃይለሥላሴ መካከል በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ ከሸዋ መኳንንት ጋር በማበር ሐረር የእያሱ የግል አማካሪ በነበሩበት ጊዜ ያዩትን የሰሙትን የልጅ እያሱን ስህተቶች በመግለጥ እንዲሁም ሇላ ጦርነት ጭምር በመግጠምና ድል በማድረግ የሸዋን መኳንንት ተቀላቅለዋል።
ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት በአማርኛ ድርሰት ግሩም ችሎታ ነበራቸው፡፡ ከፃፏቸው መጽሐፍት መካከል ፋቡላ የአውሬዎች ተረት ተውኔት፣ ታሪክና ምሳሌ 1ኛ መጽሐፍ፣ ትንሽ የእርሻ መፈተኛ የሚሉት ሲታተሙላቸው አውሮፓ በነበሩበት ጊዜ የፃፉዋቸው መንቶች እና ምድራዊ ኑሮ የተሰኙ ድርሰቶችም አሏቸው፡፡ እራሳቸው የፃፉት ኦቶባዮግራፊያቸው ለአገራቸው ከአበረከቱት ታላላቅ አስተዋጾ በተጨማሪ በጊዜያቸው የነበረውን አስተዳደር ሁኔታ ችግሮቹን፤ የተደረጉ ጥረቶችን እንዲሁም በሀገሪቱ የተካሄዱ ታላላቅ ክስተቶችን፣ በልዩ ሁኔታ እንዲሁ በልጅነታቸው የዘመቱበትን የአድዋ ጦርነት ውሎ እና በሩሲያና አውሮዻ ቆይታቸው ያሳለፉትን ጊዜ በስፋት የሚዳስስ ሲሆን ለታሪክ ማጣቀሻ ሊሆን በሚችል መልኩ ልጃቸው ግርማቸው ተክለሐዋርያት አዘጋጅተው አሳትመውታል።
ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት የማያልፈውን ስራዎቻቸውን ትተውልን በ1969 ዓ.ም. አረፉ፡፡
ተጨማሪ፥
"ፊታውራሪ ተክለሃዋርያት ተክለማርያም - ኦቶባዮግራፊ"
አዲስ አበባ ዩኖቨርሲቲ ፕሬስ 1988ዓ.ም
የመጽሐፍ ግምገማ ኩችዬ kuchiye@gmail.com
በ1876 ዓ.ም በሰኔ ወር በሳያድብር ተወለዱ፡፡ ፊታውራሪ ተክለሃዋርያት በልጅነታቸው በወንድማቸው አማካኝነት ከሸዋ ወደ ሐረር ጠቅላይ ግዛት ተጉዘው እራስ መኮንን ቤት አደጉ፡፡ በልጅነታቸው አልቀርም በማለት 50 ጥይት ጎራሽ ጠመንዣ ታጥቀው ወደ አድዋ ዘመቱ።
[1906 - 1992]
ተክለጻድቅ መኩሪያ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተክለጻድቅ: መኩሪያ: ባ፲፱፻፮: ዓ.ም. : በተጉለትና: ቡልጋ: አውራጃ: አሳግርት: ልዩ: ስሙ: ሣር: አምባ: በተባለ: ሥፍራ: ተወለዱ።
ዕድሜያቸው: ለትምህርት: ሲደርስ: መዠመሪያ: ካ’ባታቸውና: ቀጥሎም: ባ’ጥቢያቸው: ባህላዊውን: ትምህርት: እስከ: ቅኔ: ያለውን: ቀስመዋል።
ከዚያም: ዐዲስ: አበባ: መጥተው: አሊያንስ: ፍራንሴዝና: ከተፈሪ: መኮንን: ት/ቤት: ገብተው: የጊዜውን: የትምህርት: ደረጃ: አጠናቀቅዋል።
ኢጣሊያ: አገራችንን: የወረረች: ጊዜም: በየካቲት: ፲፪: ቀን: ፲፱፻፳፱: ዓ.ም.: ፍጅት: ተይዘው: ወደ: ሶማሊያ: ደናኔ: ተግዘው: ለሦስት: ዓመታት: ታሥረዋል።
ከነጻነትም: መልስ: አገራቸውን: በተለያዩ: የኃላፊነት: ደረጃዎች: አገልግለዋል። መዠመሪያ: ተቀጥረው: ያገለገሉት: በትምህርትና: ሥነጥበብ: ሚኒስቴር: ነበር። እዚያም: እያሉ: ባነራችን: ሰው: የተጻፈ: የአገራችን: ታሪክ: አንድም: ባለመኖሩ: በቁጭትና: በመቆርቆር: ነበር: ‘መጻፍ: አለብኝ’: ብለው: በደንብ: ከሚታወቀው: ከቅርቡ: ጊዜ: በቅጡ: ወደማይታወቀው: የሩቁ: ዘመን: መጣፍ: የዠመሩት።: የመዠመሪያውን: መጽሐፍ: “የኢትዮጵያ: ታሪክ: ከዐፄ: ቴዎድሮስ: እስከ: ቀ.ኃ.ሥ.”: ባ፲፱፻፴፰: ዓ.ም.: አሳተሙ። ከጫፍ: እስከጫፍ: ጽፈው: የመጨረሻውን: መጣፍ: የታሪካችን: መዠመሪያ: የሚኾነውን: የኢትዮጵየ: ታሪክ: ኑብያ - አክሱም - ዛጉዬ: እስከ: ዐፄ: ይኩኖ: አምላክ: ዘመነ - መንግሥት: የሚለውን: ባ፱፻፶፩: ዓ.ም.: አቅርበዋል። እንህኑ: መጻሕፍት: ትምህርት: ሚኒስቴር: ታሪክ: ለማስተማሪያ: በትምህርት: ቤት: ተጠቅሞባቸዋል።
ተክለጻድቅ: ከታሪክ: ውጭ: የጻፉዋቸው: “የሰው: ጠባይና: ዐብሮ: የመኖር: ዘዴና: በሚዮቶሎዢያ: ላይ: ያተኮረ: ከጣዖት: አምልኮ: እስከ: ክርስትና”: የሚሉም: መጣፎች: አሏቸው።
ተክለተድቅ: በምድር: ባቡር: በዋና: ጸሐፊነት: በቤተመጽሐፍት: ወመዘክር: ዋና: ሥራ: አስኪያጅነት፤ እንዲሁም: በፈረንሣይ፣ በእስራኤል፣ በዩጎዝላቪያ: በዲፕሎማሲ: ሥራ: በመጨረሻም: የትምህርትና: የባህል: ሚኒስትር: ኾነው: አግልግለዋል። በፈቃዳቸው: ጡረታ: ከወጡም: በኋላ: በምርምር: የታገኑ: ሦስት: ታላላቅ: የታሪክ: ሥራዎችን: አቅርበዋል።
ተክለጻድቅ: ከረዥም: ያገልግሎት: ዘመን: በኋላ: በተወለዱ: በ፹፮: ዓመታቸው: ሐምሌ: ፲፮ቀን: ባ፲፱፻፺፪: ዓ.ም.: ዐርፈዋል።
ምንጭ:
ያሠርቱ: ምእት ፥ የብርእ: ምርት: ከ፲፻: እስከ: ፳፻: ድርሰት: ክፍል: ፩
ዻጉሜ: ፫: ቀን: ፲፱፻፺፱: ዓ.ም: በብርሃነመስቀል: ደጀኔ እና ጌታሁን: ሽብሩ።
ተክለጻድቅ: መኩሪያ: ባ፲፱፻፮: ዓ.ም. : በተጉለትና: ቡልጋ: አውራጃ: አሳግርት: ልዩ: ስሙ: ሣር: አምባ: በተባለ: ሥፍራ: ተወለዱ።
[1882 - 1952]
ተሰማ ሀብተሚካኤል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተሰማ ሀብተሚካኤል በሰሜን ሸዋ በሰላሌ አውራጃ ጎሐጽዮን በ፲፰፻፹፪ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ ተሰማ የአባይን ወንዝ አቋርጠው ወደ ጎጃም በመሄድ ዜማ፣ ትርጉም፣ ቅኔን በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ተከታትለዋል፡፡ በተለይ ዲማ ወደሚገኘው እውቅ ገዳም በመሄድ ዜማና ቅኔ ተምረዋል። የቤተክርስቲያን ከፍተኛ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ በኋላ በ፲፱፻፩ ዓ.ም. በመንግሥት ሥራ በመቀጠር ወደ ሐረርጌ ጠ/ግዛት ሄዱ፡፡ ተሰማ በጥሩ እጅ ጽሑፋቸውና በተለየ የፊደል አጣጣላቸው ይታወቁ ነበር፡፡ ብዙ የሃይማኖት መጻሕፍት እንዲገለብጡ ይታዘዙ የነበረውም ለዚህ ነው፡፡ በጡረታ እስከተገለሉበት ፲፱፻፭፬ ዓ.ም. ድረስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት እንዲያዘጋጁ በትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴር ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ሠርተዋል፡፡ “ከሣቴ ብርሃን” የተሰኘው ሥራቸው ጠንካራ፣ ዋነኛና ትልቁ ሥራቸው ነው፡፡ ከ9"7 እስከ ከ9#7 ዓ.ም. በዚህ መዝገበ ቃላት ዝግጅት ላይ እንደነበሩ ብዙ ችግሮችና መሰናክሎች ገጥመዋቸዋል፡፡ አማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ቢሆንም እግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ አደሪኛ እና ግዕዝ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ይህን የቋንቋ ዕውቀታቸውንም ሥራ ላይ አውለዋል፡፡ ጥንካሬያቸውንም “ከሣቴ ብርሃን” በተባለው መዝገበ ቃላት ዝግጅት ላይ ተገልጧል፡፡ በተለይ ይህንን መዝገበ ቃላት ለማዘጋጀት ያነሣሣቸው በመምህራን ማሠልጠኛ ተቋም ውስጥ ሲሠሩ በነበረበት ጊዜ ተማሪዎች ለቃላት ትክክለኛውን ትርጉም የመስጠት ችግር እንዳለባቸው በመረዳት፣ ብዙ የአማርኛ ቃላት በከተሞች አካባቢ በመረሳታቸውና እየጠፉ በመምጣታቸው ለተተኪው ትውልድ መዝግበው ለማስቀመጥ በማሰብ ነው፡፡ ከአሥር ዓመታት በኋላ ባለ 1,398 ገጾች መዝገበ ቃላት ሲያዘጋጁ፣ መዝገበ ቃላቱም 33,000 ድርሰቶች፣ አገባቦች እና 1,278 ሥዕሎች ሲኖሩት ከ12 ዓመታት በኋላ በገበያ ላይ ለመዋል በቅቷል፡፡ ስሙም ለደራሲው ክብር ሲባል “ከሣቴ ብርሃን ተሰማ” እንዲባል በትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴር ተመርጦ ተሰየመ፡፡ ይህም ለተሰማ ሀብተሚካኤል እንደ ሽልማት ተቆጠረ፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ተሰማ ሀብተሚካኤል በሰሜን ሸዋ በሰላሌ አውራጃ ጎሐጽዮን በ፲፰፻፹፪ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ ተሰማ የአባይን ወንዝ አቋርጠው ወደ ጎጃም በመሄድ ዜማ፣ ትርጉም፣ ቅኔን በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ተከታትለዋል፡፡ በተለይ ዲማ ወደሚገኘው እውቅ ገዳም በመሄድ ዜማና ቅኔ ተምረዋል።
ተድላ ዘዮሐንስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተክለማርያም ፋንታዬ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አዛዥ ተክለሥላሴ ጢኖ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተክለየሱስ ዋቅጅራ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ አበበ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተክሌ ደስታ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተሻለ አሰፋ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ አካሉ አበበ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ መኮንን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተፈራ ኃይለሥላሴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ መኮንን ባይለየኝ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ ብርሃኑ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተፈራ ደግፌ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተወልደ ትኩል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተሰማ ታኣና አሌሳንድሮ ትሪዩልዚ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተጫነ ጆብሬ መኰንን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ ሀብተማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተሰማ እሸቴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ ገ/ማርያም ኃይሉ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ ገ/ማርያም ነሐሴ ፩፮ ቀን ፲፱፵፪ ዓ.ም. በቀድሞ ወለጋ ክ/ሀገር ጊንቢ አውራጃ ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አሶሳ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ነቀምት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በሐረር መምህራን ማሠልጠኛና በአ.አ. ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡ ተስፋዬ ገ/ማርያም ቁጥራቸው የበዙ መተሕፍትን ለአንባብያን አበርክተዋል፡፡
ካበረከቷቸው መጻሕፍት መካከል “የግችሌ ሜዳ”፣ “በድሉ በረኛው”፣ “አደን ደኀና ሰንብት”፣ “ሽሽጉ ቀነኒ”፣ “እኮ ማን ያስከብራል”፣ “ቾምቤና ወፎቹ”፣ “ሽታዬ” እና ሌሎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ተስፋዬ ገ/ማርያም ነሐሴ ፩፮ ቀን ፲፱፵፪ ዓ.ም. በቀድሞ ወለጋ ክ/ሀገር ጊንቢ አውራጃ ተወለዱ።
ተሾመ ነጋሽ ካሣዬ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተሾመ ነጋሽ በቀድሞው አርሲ ክ/ሀገር የካቲት ፲፭ ቀን ፲፱፵፬ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርሲ በቆጂ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በራስ ዳርጌ ትምህርት ቤት ተከታትለው አጠናቅቀዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የወሰዱ ሲሆን በሥራ አመራር ማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚንስትሬሽን፤ ኤም.ቢ.ኤ፣ በድርጅታዊ ሥራ አመራር፤ ኦርጋናይዜሽናል ሊደር ሺፕ፣ በሥነ መለኮት የባችለር ዲግሪ አላቸው፡፡
ተሾመ ነጋሽ “እስከማድረስ?”፣ ቅጽ 1 እና 2፣ “ጋብቻና የትዳር ሕይወት”፣ “ይፈለግ መሪ”፣ “እንዲህ ቢሆን ኖሮ”፣ የተሰኙ መጻሕትን ለአንባቢያን አቅርበዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ተሾመ ነጋሽ በቀድሞው አርሲ ክ/ሀገር የካቲት ፲፭ ቀን ፲፱፵፬ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርሲ በቆጂ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በራስ ዳርጌ ትምህርት ቤት ተከታትለው አጠናቅቀዋል።
ተስፋዬ ገሰሰ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ ሐረርጌ ውስጥ ልዩ ስሙ ጎሮ ጉቱ በሚባል አካባቢ በ፲፱፳፱ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በልጅነታቸው ወላጆቻቸው በሞት ስለተለዩዋቸው አዲስ አበባ ዘመድ ቤት በመቀመጥ ትምህርታቸውን ተከታተሉ፡፡ የተፈሪ መኮንን ተማሪ በነበሩበት ወቅት ብዙ መጻሕፍት ከማንበብ ይልቅ እግር ኳስና ሌሎች ጨዋታዎችን ያዘወትሩ ነበር። በተለይ ግን የከበደ ሚካኤልን "የትንቢት ቀጠሮ" ተውኔት ይወዱ እንደነበር ይናገራሉ፡፡
በ፲፱፵፰ ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ገቡ፡፡ የፊልም ወይም የመድረክ ተዋናይ የመሆን ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም አጠቃላይ ጥበብ ጄኔራል አርትስ ሜጀር አድርገው የሕግ ትምህርት አጠኑ፡፡
የዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከተመረቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ሄደው ለሁለት ዓመታት ቆይተዋል፡፡
"የቴያትር ጥበብን በማጥናት በኢትዮጵያ ያለውን የቴያትር ባህል ለማሳደግ" በቆራጥነት የተነሱት አሜሪካ እያሉ ነበር፡፡ ቴያትር እንዲያጠኑ ሐሳቡን የጫሩባቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴያትር ባሳዩበት ወቅት በአተዋወን ብቃታቸው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተደስተው ሰዓት በመሸለም "ቴያትር" እንዲያጠኑ ከነገሯቸው በኋላ ነው፡፡
ከአሜሪካ በ፲፱፶፬ ዓ.ም. ከተመለሱ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴያትር ቤት በመቀጠር የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ሥራ የሆነውን "የሾህ አክሊል"ን በማዘጋጀትና የዋና ገፀባህሪውን በመወከል ተውነዋል፡፡ "የሺ" የሚል ተውኔት በመጻፍም ለመድረክ አብቅተዋል፡፡ በ፲፱፶፫ ዓ.ም. በእንግሊዝኛ ቋንቋ "ላቀችና ማሰሮዋ" የሚል ተውኔት ደርሰዋል፡፡
በርካታ ተውኔቶች ላይ የትወና ችሎታቸውን ያስመሰከሩ አጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞቻቸው በሩሲያኛ ተተርጉመው ሩሲያ ውስጥ ታትመዋል፡፡ የኡመር ካየምን መጽሐፍ "ሩብ አያት" በማለት ተርጉመው አሳትመዋል፡፡ በተጨማሪም በ፲፱፷፭ ዓ.ም. መተከዣ የሚል መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ተስፋዬ ሐረርጌ ውስጥ ልዩ ስሙ ጎሮ ጉቱ በሚባል አካባቢ በ፲፱፳፱ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በልጅነታቸው ወላጆቻቸው በሞት ስለተለዩዋቸው አዲስ አበባ ዘመድ ቤት በመቀመጥ ትምህርታቸውን ተከታተሉ፡፡ የተፈሪ መኮንን ተማሪ በነበሩበት ወቅት ብዙ መጻሕፍት ከማንበብ ይልቅ እግር ኳስና ሌሎች ጨዋታዎችን ያዘወትሩ ነበር።
ተስፋ ስንታየሁ ወርቅነህ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1902 - 1943]
ተመስገን ገብሬ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተመስገን ገብሬ የተወለዱት በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረማርቆስ ከተማ በ1902 ዓ.ም. ነው፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተ ክህነት ትምህርት ተከታትለዋል፡፡ ቤተሰባቸው ካህናት ከመሆናቸውም በላይ ጎበዝ ተማሪ ነበሩ። ጉብዝናቸው በዘመናዊ ትምህርት ሲከታተሉም ጎልቶ ወጥቷል፡፡ ከጎጃም አዲስ አበባም በመምጣት በሲውዲን ሚሽን ትምህርት ቤት ተማሩ በወቅቱ ሀገሪቱ ካፈራቻቸው ጎበዝ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ፡፡
ተመስገን በጋዜጠኝነት ሙያ ከመስራታቸውም በላይ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በኃላፊነት ቦታ ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በጣሊያን በተወረረችበት ወቅት በዐርበኝነት ከጠላት ጋር ተፋልመዋል፡፡ ሱዳን ተሰደው ገዳሪፍ ውስጥ እያሉ ኢትዮጵያዊያንን በልዩ ልዩ መልክ አስተምረዋል፡፡ ጣሊያን ከለቀቀች በኋላ የዘመናዊ አስተሳሰብና ዕድገት ዓላማዋ ዕውን እንዲሆን ፍፁም የለውጥ ዐርበኛ ሆነው ሠርተዋል፡፡
ተመስገን “የጉለሌ ሰካራም” በሚል አጭር ልብወለዳቸው የመጀመሪያ የአገራችን አጭር ልብወለድ ጸሐፊ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ የጉለሌው ሰካራም ከመታተሙ በፊት “የካቲት 12” እና “አለቃ እውነቱ” የተሰኙ ሁለት አጫጭር ልብወለዶችን በጋዜጣ ላይ አውጥተዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ተመስገን ገብሬ የተወለዱት በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረማርቆስ ከተማ በ1902 ዓ.ም. ነው፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተ ክህነት ትምህርት ተከታትለዋል፡፡ ቤተሰባቸው ካህናት ከመሆናቸውም በላይ ጎበዝ ተማሪ ነበሩ።
[1895 - 1992]
ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ቀኛዝማች ተስፋ በሰሜን ሸዋ በቡልጋና በረኸት ክታብ ወይራ አክርሚት ከተባለ ቀበሌ በ1895 ዓ.ም. ታህሣሥ 24 ቀን ተወለዱ።
በአባታቸው አማካኝነት በአራት ዓመት ከአራት ወር ከአራት ቀን ሲሞላቸው ፊደል ቆጠሩ፡፡ ቀጥሎም ንባብ፣ ዳዊትና ውዳሴ ማርያም መልክዓ ማርያምና መልክዓ ኢየሱስን አጠናቀው በመማር የዲቁና ማዕረግ ተቀብለዋል፡፡ ቀኛዝማች ተስፋ ቤተክርስቲያንን በዲቁና እያገለገሉ የወላጅ አባታቸውን አርአያ በመከተ የፍየል ቆዳ እየፋቁ በመድመፅ እየደመፁ፣ ብራና በማዘጋጀት፣ ቀለሙን ከልዩ ልዩ ዕፅዋት እያነጠሩ፣ በብዕር እየጻፉ የዘወትር ጸሎት ሰዓታት ዘሌሊት፣ መዝገበ ሐዋርያ ሌላም መጻሕፍትን እየጻፉ በማራባት አሰራጭተው ሕብረተሰቡ እንዲጠቀም አድርገዋል፡፡
በ1921 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ቄርሎስ በቤተ ክህነት ግቢ ቦታ ስለሰጧቸው በሰው ኃይል የሚሠራ የማተሚያ ማሽን ገዝተው ከፊደል ገበታ ጀምሮ ያሉትን የንባብ መማሪያ፣ የጸሎትና የሃይማኖት መጻሕፍትና በራሳቸው የተደረሱ መጻሕፍት ግጥምን ሌሎች ጽሑፎችን ያትሙ ነበር፡፡ በተጨማሪ የዩፍታሔ ንጉሤና የሌሎች ታዋቂ ደራስያንን ሥራ አትመዋል፡፡ በዚህም ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ዕድገት አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ በተለይ ግን ያዘጋጃቸው በነበሩት ልዩ ልዩ የፊደል ገበታዎች ያልተማረ ኢትዮጵያዊ የለም ማለት ይቻላል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ቀኛዝማች ተስፋ በሰሜን ሸዋ በቡልጋና በረኸት ክታብ ወይራ አክርሚት ከተባለ ቀበሌ በ1895 ዓ.ም. ታህሣሥ 24 ቀን ተወለዱ።
ታረቀኝ ጎጄ] ዓለሙ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደሰ ገብሩ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታዬ ገብረማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታዴዮስ ታንቱ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደሰ ሊበን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
በጻፏቸው አጫጭር ልብ ወለዶች የሚታወቁት ታደሰ ሊበን በ፲፱፳፫ ዓ.ም. ወለጋ ውስጥ ደንቢዶሎ ተወለዱ። ገና የስድስት ዓመት ልጅ እያሉ አባታቸው ሞተውባቸዋል። እናታቸው ጥሩ ጥሩ ተረቶች እየተረኩላቸው ያደጉት ታደሰ ሊበን የልብወለድ ፍቅር ያደረባቸው በዚያን ጊዜ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡
ከመንግሥቱ ለማ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው፡፡ ነገር ግን በ፲፱፵፱ ዓ.ም. “መስከረም” እና በ፲፱፶፪ ዓ.ም. “ሌላው መንገድ” በሚል ርዕስ የአጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ ካሳተሙ በኋላ ሌላ መጽሐፍ ባለማሳተማቸው ከመንግሥቱ ለማ ጋር ተቀያይመዋል፡፡
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአጭር ልብወለድ የመጀመሪያው ጸሐፊ በመባል ይታወቁ ነበር፡፡ ነገር ግን “የጉለሌው ሰካራም” ጸሐፊ ተመስገን ገብሬ የመጀመሪያው የአጭር ልብወለድ ጸሐፊ መሆናቸው ከታወቀ በኋላ ቀድሞ የነበረው አስተሳሰብ ቢቀየርም በሥነ ጽሑፍ እድገት ላይ ያደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ግን የሚዘነጋ አይደለም፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
በጻፏቸው አጫጭር ልብ ወለዶች የሚታወቁት ታደሰ ሊበን በ፲፱፳፫ ዓ.ም. ወለጋ ውስጥ ደንቢዶሎ ተወለዱ።
ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታዬ ገብረ ማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደሰ ዘውዴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደሰ ሜጫ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታምራት አማኑኤል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታምራት ይገዙ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደሰ ቴሌ ሳልቫኖ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታቦር ዋሚ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዶ/ር ታደሰ ወልደጊዮርጊስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታክሎ ተሾመ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደሰ ዘወልዴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ቀኛዝማች ታደሰ ዘወልዴ በ1895 ዓ.ም ተወለዱ። ዘመናዊ ትምህርታቸውን ዳግማዊ ምኒሊክ ትምህርተ ቤት ተማሩ።
በ1919 ዓ.ም. ወደ ግብፅ አገር ሄደው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ከተመረጡት ሃያ አንድ ተማሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ። በዚህም መሠረት እስክንድሪያ ከተማ ሊሴ ፍራንሴስ ትምህርት ቤት ገቡ።
ከዚያም ወደ ፈረንሳይ አገር ተሻግረው የቴሌኮሚኒኬሽን ልዩ ትምህርት ሲማሩ ቆዩ።
ኾኖም በ1928 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ላይ የፋሺስት ወረራ ስለደረሰ የክተቱን አዋጅ በወዶዘማችነት በመቀበል ከፓሪስ ወደ ማይጨው ዘመቱ።
ቀኛዝማች ታደሰ ዘወልዴ በ1895 ዓ.ም ተወለዱ።
ታደለ ብጡል ክብረት
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደለ ብጡል ኢንጂነር ታኀሣሥ ፩ ቀን ፲፱፳ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተወለዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀ.ኃ.ሥ. ኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በተባበሩት አሜሪካ በ”ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዊስ ካንሰንና ቺካጎ” የተከታተሉ ሲሆን በስዊድን ስቶክሆልም ስትራክቸራል ዲዛይን ሲሆን፤ የሲቪል ምሕንድስና ባለሙያም ናቸው፡፡
ታደለ ብጡል “ማራዠት” በሚል ርዕስ የግጥም መድብል አንደኛ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ በተጨማሪም “ሦስትዮሽ” የግጥም መድብል፣ እንዲሁም “ውይይት” በሚል ርዕስ ሌሎች ሥራዎችንና ወጎችን ከክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ጋር አቅርበዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ታደለ ብጡል ኢንጂነር ታኀሣሥ ፩ ቀን ፲፱፳ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተወለዱ።
ታደለ ገድሌ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደለ ገብረሕይወት
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደለ ገ/ሕይወት ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፲፱፴፰ ዓ.ም. በግዮን አምቦ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞው ቀ.ኃ.ሥ. ኮከበ ጽባሕ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ተምረው በፖለቲካል ሳይንስና ሥነ-መንግሥት ትምህርት በዲፕሎማ ተመርቀዋል።
ታደለ ገ/ሕይወት “ማነው ኢትዮጵያዊ?”፣ “ኢትዮጵያ ትቅደም”፣ “ከርሞ ዘማች” “ተራማጅ ጥቅሶች”፣ “ለቀዩ አበባ”፣ “ብቀላ” የተሰኙ የፈጠራና የትርጉም ሥራዎችን በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ታደለ ገ/ሕይወት ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፲፱፴፰ ዓ.ም. በግዮን አምቦ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞው ቀ.ኃ.ሥ. ኮከበ ጽባሕ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ተምረው በፖለቲካል ሳይንስና ሥነ-መንግሥት ትምህርት በዲፕሎማ ተመርቀዋል።
[1404 - 1406]
ዐፄ ቴዎድሮስ ፩ኛ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አቡነ ቴዎፍሎስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ቴዎድሮስ ጸጋዬ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ትኩእ ባህታ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መጻሕፍት ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ
ይጫኑ
ተመዝግበው ከሆነ እዚህ
ይጫኑ
[
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ቋንቋ
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
]
[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com